Go to full page →

ምዕራፍ ፳፫—መንፈስ ቅዱስ፡፡ CCh 160

መጠባበቅ ብቻ ሳይሆን ግን የጌታችን የየሱስ ክርስቶስን መምጣት ማፋጠን የክርስቲያን ሁሉ መብት ነው፡፡ ስሙን የያዙ ሁሉ ለክብሩ ፍሬ ቢያፈሩ ኑሮ ዓለም በወንጌል ዘር ምንኛ በተሎ ይዘራ ነበር፡፡ የመጨረሻው መከር በተሎ በስሎ ክርስቶስም የከበረውን (ተወዳጅ) እህሉን ለመሰብሰብ በመጣ ነበር፡፡ CCh 160.1

ወንድሞቼና እህቶቼ ለመንፈስ ቅዱስ ለምኑ፡፡ እግዚአብሔር ከሰጠን ተስፋ ሁሉ በስተኋላ ይቆማል፡፡ መጽሐፍ ቅዱሶቻችሁን በእጆቻችሁ ይዛችሁ ‹‹እንዳልኸኝ አድርጌያለሁ ተስፋህንም አቀርባለሁ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋልም እሹ ታገኙማላችሁ፡፡ ደጅ ምቱ ይከፈትላችኋልም›› ያልኸውንም ተስፋህን አቀርባለሁ በሉ ክርስቶስ እንዲህ ይናገራል ‹‹በጸሎት የምትለምኑን ሁሉ እመኑ እንድታገኙት ይሆንላችኋልም››፡፡ ‹‹በስሜም የለመናችሁትን ሁሉ ይህነን አደርጋለሁ አባት በልጅ ይመሰገን ዘንድ›› (ማቴ ( ( ማርቆስ (( (( ዮሐንስ (( (()፡፡ CCh 160.2

ክርስቶስ ፈቃዱነ ለአገልጋዮቹ ይናገር ዘንድ መልእክተኞቹን ወደ ግዛቱ ክፍል ሁሉ ይልካቸዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያኖቹ መኻከል ይሔዳል፡፡ ተከታዮቹንም ለመቀደስ ከፍ ሊያደርግና ሊያስከብራቸው ይፈልጋል፡፡ በርሱ የሚያምኑ አርአያቸው በዓለም ውስጥ ከሕይወት ወደ ሕይወት የጣመ ይሆናል፡፡ ክርስቶስ ኮከቦችን በቀኝ እጁ ይይዛል ብርሃኑም በነሱ አማካይነት ለዓለም እንዲበራ ለማድረግ ሐሳቡ ነው፡፡ በእንዲህ በላይኛዋ ቤተ ክርስቲያን ላለው ከፍ ላለው አገልግሎት ሕዝቡን ያዘጋጅ ዘንድ ይፈልጋል፡፡ የምናደርግ ታላቅ ሥራ ሰጥቶናል፡፡ በታማኝነት እንድናደርገው መለኮታዊ ጸጋ ለሰው ምን ሊያደርግ እንደሚችል በሕይወታችን እናሳይ፡፡ 18T2223; CCh 160.3