Go to full page →

ጳውሎስ ለምክር (ለትምህርት) ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ጽፎ አመለከተ፡፡ CCh 104

ብዙዎች በዓለም ከታወቁት ተከታዮቹ ጋር ነክነት ሳይኖራቸው ለተቀበሉት ብርሃንና ሁኔታ ለክርስቶስ ብቻ ኃላፊዎች እንደሆኑ ሐሳብ አላቸው ነገር ግን በውነቱ የሱስ ለምክራችን በሰጠን በትምህርቶቹና በምሳሌዎቹ ይህ የተነቀፈ ነው፡፡ እዚህ ጳውሎስ የሱስ እጅግ ጠቃሚ ለሆነው ሥራ ተገቢ የሚያደርገው ለርሱ የተመረጠ ዕቃ የሚሆን በየሱስ ፊት በቀጥታ ቀርቦነበር ሆኖም እርሱ የእውነትን ትምህርቶች አያስተምረውም፡፡ እርምጃውን ያግድና ያስረዳዋል እርሱም ‹‹ምን ትሻለህ አደርግ ዘንድ›› ሲል ሲጠይቀውም መድኃኒታችን በቀጥታ የሚነግረው አይደለም ነገር ግን ከቤተ ክርስቲያኑ ጋር ያገናኘዋል፡፡ ምን ልታደርግ እንደሚገባ እነሱ ይነግሩሃል፡፡ የሱስ የኃጢአተና ወዳጅ ነው ልቡ ዘወትር ግልጥ (ክፍት) ነው ዘወትርም በሰው ወዮታ ይነካል፤ እርሱ በሰማይና በምድር ኃይል ሁሉ አለው ነገር ግን ለሰዎች ማብራሪያና ደኅንነት ያዘዘባቸውን አማካዮች (ዘዴዎች) ያከብራል፡፡ ሳውልን ወደ ቤተ ክርስቲያን ያመለክተዋል በዚህም ለዓለም የብርሃን መገናኚያ አድርጎ ያጎናጸፉትንም ሥልጣን ማስታወቁነው፡፡ በምድር የተቋቋመች የክርስቶስ አካል ናት ለሥርዓቶቹም ከበሬታ መስጥ አስፈላጊ ነው፡፡ በሳውል ነገር ረገድ ሐናኒያ የሚመስለው በክርስቶስ ነው እርሱም በክርስቶስ ፈንታ ለመሥራት በምድር በተሾሙት በክርስቶስ ሰባኮች ደግሞ ይመሰላል፡፡ CCh 104.3

በጳውሎስ መመለስ በሐሳባችን ዘወትር ልንይዝ የሚገባን ጠቃሚ ደንቦች (ፕሪንሲፕሎች) ተሰጥተውናል፡፡ የዓለም መድኅን ቤተ ክርስቲያኑ ካለችበት ሥፍራ ከተቋቋመችውና ከታወቀችው ቤተ ክርስቲያኑ ተነጥሎ (ነክነት ሳይኖረው) በሃይማኖታዊ ነገሮች (ጉዳዮች) ያለውን ሁኔታና አድራጎት የሚያፀድቀው አይደለም፡፡ CCh 105.1

የግዚአብሔር ልጅ ከተቋቋመችው የቤተ ክርስቲያኑ ሥራና ሥልጣን ጋር ራሱነ አንድ አደረገ፡፡ የርሱ በረከቶች እርሱ ባዘዛቸው ወኪሎች አማካይነት እንዲወርዱ ነበር፡፡ ጳውሎ ጻድቃንን በማሳደድ ያደረገውን ሥራ አጥብቆ ሕሊናው ሲወቅሰው የጭከና ሥራውን ማወቁ በእግዚአብሔር መንፈስ ሲታሰበው በደል የሌለበት አያደርገውም፡፡ የደቀመዛሙርት ተማሪ መሆን ይኖርበታል፡፡ 83T432, 433; CCh 105.2

የቤተ ክርስቲያን አባሎች ሁሉ የእግዚአብሔር ወንዶችም ሴቶችም በዓለም ውስጥ ብርሃናት ለመሆን ከመቻላቸው በፊት የሥርዓት (የዲሲፕሊን) አመራር ሊኖራቸው ይገባል፡፡ እግዚአብሔር ወንዶችም ሴቶችም በጨለማ ውስጥ እንዲሁ እንዳሉ ሆነው በመቅረታቸው ደስ እያላቸው ከብርሃን ምንጭ ጋር ግንኙነት ያደርጉ ዘንድ ምንም የተለየ ጥረት የማያደርጉትን የብርሃን መገናኛዎች አያደርጋቸውም፡፡ የገዛ ፍላጎታቸው የሚሰማቸውና በታለቅ ትጋት ጸንተው ወደ መጸለይና ወደ መሥራት ሐሳብ ራሳቸውን የሚያነቃቁ መለኮታዊ እርዳታ ያገኛሉ፡፡ እያንዳንዱ ስለ ራሱ በብዙ እንደ መማሩ መጠን የማይማረውም ብዙ ነገር አለ፡፡ የጥንት ዓመሎችና ልማዶች መወገድ አለባቸው እነዚህንም ስህተቶች ለማረም በታላቅ ተጋድሎና ፕሪንሲፕሉን በማካሔድ ረገድ በእግዚአብር ጸጋ ድልን ለማግኘት እንዲቻል እውነትን በምሉ መቀበል ብቻ ነው፡፡ 94T485, 486; CCh 105.3