Go to full page →

ዓመታዊ ስብሰባዎች፡፡ CCh 111

ወደ እግዚአብሄር ሕዝብ ጉባዔ ለመሔድ በብዙ ጥረት አድርጉ፡፡ ወንድሞቼና እህቶቼ እግዚአብሔር ለእናንተ ያለውን መልእክት የመስማት ምቹ ጊዜ ችላ ከማለት ሥራችሁ እንዲሰቃይ ማድረግ በጣም ይሻላችኋል፡፡ በተቻላችሁ ሁሉ መንፈሳዊ ጥቅምን ሁሉ ከማግኘት ለሚያግዳችሁ ምክንያት (ማመኻኛ) አትስጡ፡፡ የብርሃን ጮራ ሁሉ ያስፈልጋችኋል፡፡ በውስጣችሁ ስላለው ተስፋ ምክንያቱን በገርነትና በፍርሃት ትሰጡ ዘንድ የሠለጠናችሁ መሆን ያስፈልጋችኋል፡፡ እንዲህ ያለውን እድል (መብት) ማጣት የለባችሁም፡፡ CCh 111.3

ሰባኮቹ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ሠራተኞች የጸሎት ስብሰባውን በረከት እንዲያደርጉልን በነሱ ላይ እየታመን ማንኛችንም ወደ ሠፈር (ዓመታዊ) ስብሰባ መሔድ የለብንም፡፡ እግዚአብሔር ክብደታቸውን በሰባኪው ላይ እንዲያንጠለጥል ሕዝቡን አይፈልግም፡፡ ለዕርዳታ በሰብዓዊ ፍጥረቶች ላይ በመታመን እንዲዳከሙ አይፈልጋቸውም፡፡ ረዳት እንደሌላቸው ልጆች ለድጋፍ በሌላው ላይ መመርኮዝ የለባቸውም፡፡ የእግዚአብሄር ጸጋ መጋቢ ሆኖ የቤተ ክርስቲያን አባል ሁሉ በራሱ ውስጥ ሕይወትና ሥር እንዲኖረው የግል ኃላፊነት የተጣለበት መሆኑን ሊሰማው አለበት፡፡ የስብሰባው ክንውን መንፈስ ቅዱስ አብሮት በመሆኑና በኃይሉ ላይ የሚታመን ነው፡፡ የእውነትን ጉዳይ አፍቃሪ የሆነ ሁሉ ለመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ መጸለይ አለበት፡፡ በተቻለን ኃይል ሁሉ ለሥራው እንቅፋት የሆነውን ሁሉ ማስወገድ ይኖርብናል፡፡ በቤተ ክርስቲያን አባሎች መለያየትና የእርስበርስ መማረር ሲወደድ መንፈስ ቅዱስ ከቶውን ለመፍሰስ አይቻልም፡፡ ቅናት ምቀኝነት ክፉ ሐሳብና ክፉ ንግግር ከሰይጣን ናቸው እነሱም በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ላይ መንገድን ጨርሰው የሚዘጉ ናቸው፡፡ CCh 111.4

በዚህ ዓለም እንደ ቤተ ክርስቲያኑ ለአምላክ እጅግ ተወዳጅ የሆነ ሌላ ነገር የለም፡፡ በእንዲህ ያለ የመቅናት (የትጋት) ጥንቃቄ በርሱ የሚጠበቅ ምንም ሌላ ነገር የለም፡፡ አገልግሎቱን የሚያደርጉትን ስሜታቸውን የሚጎዳውን አድራጎት እንደማድረግ ያለ አምላክን የሚያቀይመው ነገር የለም፡፡ በመንቀፍና ተስፋ በማቆረጥ (በማስፈራራት) በሥራው ሰይጣንን የሚረዱትን ሁሉ ይቆጣጠራቸዋል፡፡ 136T39-42, CCh 112.1