Go to full page →

ኑዛዜ ለማን ሊደረግ ይገባል፡፡ CCh 122

ኃጢአታቸውን ለማመኻኘት ወይም ለመሠወር የሚጥሩና ሳይናዘዙበትና ይቅርታ ሳያገኙ በሰማይ መጻሕፍት ውስጥ እንዲቀር የሚፈቅዱት በሰይጣን ይሸነፋሉ፡፡ CCh 122.6

በስም የያዙት ኃይማኖት እጅግ ከፍ እንደ ማለቱና ማዕረጋቸው እጅግ የከበረ እንደ መሆኑ መጠን እርምጃቸው በአምላክ ፊት እጅግ የሚያሳዝነና ታላቁ ባላጋራቸው ድል የሚነሳቸው መሆኑ በጣም የተረጋገጠ ነው፡፡ ለአምላክ ቀን ዝግጅት ማድረግን የሚያዘገዩ በመከራ ጊዜ ወይም በማናቸውም ተከታይ ጊዜ ውስጥ ሊያገኙት አይችሉም፡፡ እንዲህ ያሉ ሁኔታቸው ሁሉ ተስፋቢስ ነው፡፡ ፮6GC620; CCh 123.1

ኃጢአትህንና ስህተቶችህን ለማያውቁ እንድትናዘዝ አይፈልግብህም፡፡ የማያምኑት እንዲያሸንፉ የሚመራቸውን ኑዛዜ መናዘዝ ተግባርህ አይደለም፤ ነገር ግን ለሚገባው ስህተትህን ለማያባብሰው እንደ እግዚአብሔር ቃል ተናዘዝ እነሱም ይጸልዩልህ፤ እግዚአብሔርም ሥራህን ይቀበላል፤ ይፈውስሃልም፡፡ ለነፍስህ ስትል ለዘልዓለማዊነት ፍጹም የሆነ ሥራ ታደርግ ዘንድ ትለመናለህ፡ ትዕቢትህን፤ ከንቱነትህን ወዲያ ጣል፤ የቀና ሥራ ስራ ወደ መንጋ እንደገና ተመለስ፡፡ እረኛው ሊቀበልህ በመጠባበቅ ላይ ነው፡፡ ንስሐ ግባ የመጀመሪያ ሥራህንም አድርግ ወደ አምላክም ሞገሥ እንደገና ና፡፡ ፯72T296; CCh 123.2

ክርስቶስ አዳኝህ ነው የትህትና ኑዛዜህን ችላ አይልም፡፡ የግል ጠባይህ የሚያይልብህ ኃጢአት ካለብህ፤ በአምላክና በሰው በኻከል አማላጅ ለሆነው ለክርስቴስ ተናዘዝ፡፡ ‹ከላንትም ማንም ኃጢአት ቢሰራ ከአብ ዘንድ አማላጅ አለን የሱስ ክርስቶስ ጻድቅ›፡፡ 1ዮሐ. መል.2.1፡፡ አሥራቱንና ሥጦታዎቹን ከአምላክ በማስቀረት ኃጢአት አድርገህ እንደሆን በደልህን ለአምላክና ለቤተ ክርስቲያን ተናዘዝ፤ ‹አሥራቱን ሁሉ ወደ ጐደራዬ አግቡ› ሲል የሰጠኸን ቃል ተቀበል፡፡ ሚልክ ፫፡፲፡፡ ፰8CH374; CCh 123.3

የእግዚአብሔር ሕዝብ በስተዋል መራመድ አለባቸው፡፡ የታወቀውን ኃጢአት ሁሉ እስኪናዘዙ ድረስ የተደሰቱ መሆን የለባቸውም፡፡ እንግዲህ የሱስ እንደሚቀበላቸው ያምኑ ዘንድ መብታቸውና ተግባራቸው ነው፡፡ ሌሎች በጨለማ ውስጥ ዳክረው ይደሰቱ ዘንድ ለነሱ ድል መንሳትን እንዲያገኙላቸው ሊጠባበቁዋቸው አይገባም፡፡ እንዲህ የለ መደሰት የጸሎት ስብሰባው እስኪያበቃ ብቻ የሚቆይ ነው፡፡ ነገር ግን አምላክ በስሜት ፈንታ በፕሪንስፐል ሊገለገል ይገባል፡፡ ጧትና ማታ በቤተሰቦችሁ ውስጥ ለራሳችሁ ድልን አግኙ፡፡ የዕለት ሥራችሁ ከዚህ አያግዳችሁ፡፡ ለመጸለይ ጊዜ ውሰዱ ስትጸልዩም እግዚአብሔር እንደሚሰማችሁ እመኑ፡፡ ከጸሎታችሁ ጋር የተቀላቀለ ኃይማኖት ይኑራችሁ፡፡ ወዲያ ያን ጊዜ ነው ኃይማኖት የሚተነው፡፡ ፱91X167; CCh 123.4