Go to full page →

ክርስቶስ የአምላክ ልጆች ይሆኑ ዘንድ ለሰዎች ኃይል ይሰጣል፡፡ CCh 136

ክርስቶስ ከስቅለቱ በፊት ሌሊቱን በላይኛው ክፍል የተናገራቸውን ቃላት እናጥና፡፡ የፈተናው ሰዓት ቀርቦ ነበር በኃይል የሚፈተኑትንና የሚሞክሩትን ደቀመዛሙርቱን ሊያጽናና ፈለገ፡፡ CCh 136.1

ደቀ መዛሙርት ከእግዚአብሔር ጋር ስላለው ዝምድና የተናገራቸውን የክርስቶስን ቃላት ገና አላስተዋሉመ ነበር፡፡ ያስተማራቸው አብዛናው ትምህርት ገና ለነሱ ጨለማ ነበር፡፡ እግዚአብሄር ከነሱ ጋር ስላለው ዝምድናና ስለ አሁኑና ስለ ወደፊቱ ጥቅማቸው አለማወቃቸውን የገለጹባቸውን ብዙዎች ጥያቄዎች ጠይቀው ነበር፡፡ ክርስቶስም በጣም በተብራራና ግልጽ በሆነው አኳኋን ስለ አምላክ እንዲያውቁ ፈለጋቸው፡፡ CCh 136.2

በጴንጤቆስጤ ቀን መንፈስ ቅዱስ በደቀመዛሙርቱ ላይ በፈሰሰ ጊዜ ክርስቶስ በምሳሌዎች የተናገራቸውን እውነት አስተዋሉ፡፡ ለነሱ ምሥጢሮች የነበሩ ትምህርቶች ተገለጹላቸው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ ያገኙት ማስተዋል ስለ ልብ ወለድ ሐሳባቸው እንዲያፍሩ አደረጋቸው፡፡ አሁን ከተቀበሉት ሰማያዊ ነገሮች ጋር ሲመዛዘኑ ሐሳቦቻቸውና ትርጓሜያቸው ሞኝነት ሆኑባቸው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ተመሩ አንድ ጊዜም ጨልሞባቸው በነበረው ማስተዋላቸው ውስጥ ብርሃን በራ፡፡ CCh 136.3

ደቀ መዛሙርት ስለ ክርስቶስ ተስፋ ፍጹም የሆነ ፍጻሜ ገና አላገኙም ነበር፡፡ ሊያገኙ የተቻላቸውን ያምላክን ዕውቀት ሁሉ አገኙ ነገር ግን ክርስቶስ አብን በግልጽ የሚያሳያቸው መሆኑን የሰጣቸው የተስፋው አፈጻጸም ገና የሚሆንላቸው ነው፡፡ ዛሬም እንደዚሁ ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔር የምናውቀው ዕውቀታችን በከፊልና ፍጹምነት የሌለው ነው፡፡ ተጋድሎው ሲፈጸምና ሰው የሆነው ክርስቶስ የሱስ የታመኑትን ሠራተኞቹን በኃጢአት ዓለም ለርሱ እውነተኛ ምስክርነት ያቀረቡትን በአባቱ ፊት ሲያስታውቅ፣ አሁን ለነሱ ምሥጢሮች የሆኑትን በግልጽ ያስተውላሉ፡፡ CCh 136.4

ክርስቶስ ከርሱ ጋር ወደ ሰማያዊ ግቢዎች የተከበረውን ተስቢዕትነቱን ወሰደ፡፡ ለሚቀበሉት ያምላክ ልጆች ይሆኑ ዘንድ ኃይል ይሰጣል፣ በመጨረሻ እግዚብሔር ለዘላለም ከርሱ ጋር እንዲኖሩ የራሱ አድርጎ ይቀበላቸው ዘንድ፡፡ በዚህ ሕይወት ለእግዚአብሔር ታዛዦች (ዕሙኖች) ቢሆኑ በመጨረሻ ‹‹ፊቱን ያያሉ ስሙም በግንባሮቻቸው ይሆናል››፡፡ (ራእይ ((፣()፡፡ አምላክን ከማየት በቀር የሰማይ ደስታ ምንድን ነው( ያምላክን ፊት ከማየትና አባታችን መሆኑን እሱን ከማወቅ የበለጠ ለሚያድነው ኃጢአተኛ ምን ትልቅ ደስታ ሊሆንለት ይቻላል( CCh 136.5