አለባበስን በማመለከት ትክክለኛ የሆነውን መሠረተ ሐሳብ የማያስቀምጥ ማንኛውም ትምህርት የተሟላ ሊሆን አይችልም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ትምህርት ከሌለበት የትምህርት ሥራ አብዛኛውም ጊዜ ይጓተትና ወደ ተሳሳተ አጠቃቀም ይዞራል፡፡ የልብስ ፍቅርና ለዘመን አመጣሽ /ፋሽን/ አለባበስ ከልብ ተመስጦ መስጠት ለመምህሩ ዋና ተቀናቃኝና ጐጂ መሰናክሎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡ EDA 276.1
ዘመን አፈራሽ አለባበስ እንደ ብረት በጠነከረ ክንድ የምትገዛ የሴት ባለሥልጣን ዓይነት ናት፡፡ በብዙ ሴቶች ውስጥ የወላጆችን የልጆችን ጉልበት ግዜና ትኩረት ሁሉ ወደራሷ የምትስብ ነች፡፡ ሐብታሞች ምኞታቸው ስለሆነ ዘወትር ከሚለዋወጠው የእሷ ዘይቤ ጋር ይስማማሉ፡፡ መካከለኛውና የድሃው መደብ አባላት ከእነሱ በላይ የሆኑ መድበው ወደ አስቀመጡት ደረጃ ለመቅረብ ይታገላሉ፡፡ አቅሙና ጉልበቱ ውስን በማሆንበት ቦታ የትልቅ ሰውነት ምኞትም ከፍተኛ በሚሆንበት ጊዜ ሸክሙ ጭራሽ ድጋፍ የሌለው ይሆናል፡፡ EDA 276.2
ብዙዎች አንድ ልብስ ምንም ቢመስል ወይም ቢያምርም ባያምርም እንኳ ግድ የላቸውም፡፡ ብቻ ፋሽኑ ይለወጥ እንደገና ይሰፋል ወይም ወዲያ ይጥሉታል፡፡ የቤተሰቡ አባላት ረፍት የለሽ ግዳጅ ወድቆባቸዋል፡፡ ልጆችን ለማሰልጠን ጊዜ የላቸውም፤ ለፀሎት ወይም መጽሐፍ ቅዱስ ለማነበብ ጊዜ የላቸውም ትንንሾች ከእግዚአብሔር ጋር በሥራው ይተዋወቁ ዘንድ ለመርዳት ጊዜ የለም፡፡ EDA 276.3
ለበጐ አድራጐት ጊዜውም ገንዘቡም የለም፡፡ የቤቱ ማዕድም ውሱን ከመሆኑም በላይ እንደ ነገሩ ተለቃቅሞ የተዘጋጀ ነው፡፡ ተፈጥሮዎች የሚጠይቁተ ጥያቄዎችም የሚሟሉት በከፊል ነው፡፡ ውጤቱም በሽታ የሚያስከትል አመጋገብን ለመቆጣጠር ወደ አለመቻል የሚያመራ የተሳሳተ የአመጋገብ ልምድ ማካበት ነው፡፡ EDA 277.1
እዩኝ፣ እዩኝ ማለትን መውደድ ብኩንነትን ያስከትላል፡ በብዙ ወጣቶች ዘንድ የተከበረ ሕይወት ያለው ትልቅ ሰው የመሆንን መንፈስ ይገድልባቸዋል፡፡ ትምህርትን በመፈለግ ፈንታ የልብስ ፍላጐታቸውን ለማርካት ገንዘብ ሊያስገኝላቸው በሚችል በማንኛውም ሥራ ይጠመዳሉ፡፡ በዚህ ዓይነት ዝንባሌ ብዙ ወጣት ልጃገረዶች የሚያስደስት መስሏቸው ጠፉ፡፡ EDA 277.2
የስግደት የአገልግሎት ቀኖችም እንኳ የፋሽን ተጽእኖ ሊያመልጡ አልቻሉም፡፡ እንዲያውም የሷ ኃይል ይበልጥ የሚገለጽበት እድል ይሰጣሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያንም የትዕይንት ጉባአ የማካሄድበት ቦታ እይሆነ ነው፡፡ ከስብከት ቅዳሴ ይልቅ ፋሽኖች የሚጠኑበት ስፍራ ሆኗል፡፡ ድሆች ይህ ወግ የሚጠይቀውን ማሟላት ስለሚሳናቸው ከነጭራሹ ወደ ቤተ ክርስቲያን መምጣቱንም ትተዋል፡፡ የእረፍት ቀንም በቀልድና ዘበት ያልፋል፡፡ በወጣቶች ዘንድ ደግሞ ቅስም ከማሰብሩ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ መንገድ ይባክናል፡፡ EDA 277.3
በትምህርት ቤት ውስጥ ልጃገረዶች በማይስማሙና በማይመቹ ልብሶች ተወጣጥረው ትምህርት ለመከታተልም ሆነ ለመዝናናት የማይችሉ ያደርጋቸዋል፡፡ አእምሮአቸው በቅድሚያ በሌላ ነገር ስለተሞላ መምህሩ የትምህርት ፍላጐታቸውን ለማነቃቃት ከባድ ችግር ይገጥመዋል፡፡ EDA 277.4
መምህሩ የፋሽንን አለባበስ ፍቅር ለማስወገድ ዘወትር ከተፈጥሮ ጋር ከመገናኘት ሌላ የተሻለ መፍትሔ ሆኖ የሚያገኘው ዘዴ የለም፡፡ ተማሪዎች ሁልጊዜ በወንዝ በሐይቅ በባህር ዳርቻ የሚገኘውን ደስታ ያጣጥሙ፡፡ ወደ ተራሮች ይውጡ፤ የፀሐይ ግብን ግርማ ሞገስ ይመልከቱ የጫካ ውስጥና በመስክ ጉብኝት የሚገኙትን መዝገቦች ያስሉ አትክልቶችንና አበባዎችን በመንከባከብ የሚገኘውን ደስታ ይማሩ፡፡ በዚህ ጊዜ ተጨማሪው ጌጣ ጌጥ ወይም በራስ ላይ በወገብና በሌላም ክፍል ላይ ሁሉ የሚጨመሩ ማሸብረቂያዎች ሁሉ ወደ አላስፈላጊነት ያዘቅጣሉ፡፡ EDA 278.1
በወጣቶች በአለባበስና በአመጋገብ ላይ የሚኖር ቀላል የአኗኗር ዘዴ ከከፍተኛ አስተሳሰብ ጋር የማይነጣጠል መሆኑን እንደመለከቱ ምሯቸው፡፡ ገና ስንትና ስንት መጠናትና መሠራት ያለበት ብዙ ነገር ያለ መሆኑን እንዲያዩ አድርጓቸው፡፡ ለሕይወት ሥራ የመዘጋጃ ጊዜ የሆኑት ቀናት ምን ያክል ውድና ድንቅ እንደሆኑ እንዲያዩ አድርጓቸው፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በተፈጥሮ መጽሐፍነት ውስጥ ክቡር ስለሆኑ ሕይወቶች የተፃፉ ታሪኮች ውስጥ ምን ዓይነት መዝገቦች እንዳሉ ያዩ ዘንድ እርዷቸው፡፡ EDA 278.2
አዕምሮአቸው መልሶ ሊወቅሳቸው ወደሚችሉበት ስቃይ ያምራ /ያስታውስ/፡፡ አባካኝ ልጅ ለመታየት ሲል ብቻ የሚያጠፋው እያንዳንዱ ብር ለተራቡ ምግብ ለተረዙ ልብስ በሐዘን ለተጐዱ ማጽናኛ እንዲሆን ሊሰጥ ይችል የነበረውን አንድ ብር አጣ ማለት መሆኑን ያዩ ዘንድ እርዷቸው፡፡ EDA 278.3
መሠረት ለሌለው ነገር ታዛዥ ለመሆን ሲሉ ብቻ አእምሮአቸውን የሚያንጫጫ ጤናቸውን የሚጐዳና ደሰታቸውን የሚያበላሽ ለምቾት ይሆናል ወይም ይማርካል ለማይባል ነገር የሕይወትን ግርማ ሞገስ የሚሰጡ ዕድሎችን ዝም ብለው ማጣት የለባቸውም፡፡ EDA 278.4
በዚሁም ላይ ወጣቱ የተፈጥሮን ትምህርት መገንዘብን መማር አለበት፡፡»ሁሉን በጊዜው ውብ አድርጐ ሠራው፡፡» መክብ 3፡11 በአለባበስና በሌሎችም ነገሮች ሁሉ ፈጣሪአችንን ማክበር ለእኛ መልካም ዕድል እርሱም በአለባበሳችን ንፁህና ጤናማ እንድንሆን ብቻ ሣይሆን በአግባቡ የተስተካከለና ለእኛ ተገቢ የሚሆነንን እንድንለብስ ይፈልጋል፡፡ EDA 279.1
የአንድ ሰው ባህሪይ በአለባበሱ ይገመታል፡፡ ጥሩ የአለባበስ ፍላጐት የተኮተኮተ አዕምሮ ቀላልና በአግባቡ የተስፋ ልብስ መምረጥ በመቻላችን ይገለጣል፡፡ ቀላል ቅጥልጥል ያልበዛበት አለባበስ ከጥሩ አቀራረብ ጋር ሲቀናጅ ለሴት ልጅ ከብዙ ሺህ ጥፋቶች እንደ ጋሻ ተከላክሎ በተቀደሰ አገልግሎተ የተከበበ አየር ይፈጥርላታል፡፡ EDA 279.2
ልጃገረዶች የጥሩ አለባበስ ጥበብ የራሳቸውን ልብስ መስፋት መቻልን ጭምር እንደሚያጠቃልል ይማሩ፡፡ ይህ እያንዳንዱዋ ልጃገረድ ልትወድደውና ለትጓጓለት የሚገባ መልካም ምኞት ነው፡፡ ሊያመልጣት የማይገባ የጠቃሚነትና በሙሉ ነፃነት የሚሠራበት መንገድ ነው፡፡ EDA 279.3
ውበትን ማፍቀርና መመኘት ተገቢ ነው፡፡ እግዚአብሐር ግን መጀመሪያ እጅግ ከፍተኛ የሆነውንና ለዘለዓለም የማይጠፋውን ውበት እንድናፈቅርና እንድንከታተል ይፈልግብናል፡፡ የሰው ልጅ ባለው ችሎታ ተጠቅሞ ምንም ዓይነት ድንቅ ነገሮችን መምረጥ ቢችልም እንኳ ከዚያ የባህሪይ ውበት ጋር ሊወዳደር የሚችል በርሱ ፊት «ታላቅ ዋጋ» ያለው ውበት በራሱ ሊይዝ አይችልም፡፡ EDA 279.4
ወጣቶችና ትንንሽ ልጆች በሰማይ የልብስ ማዘጋጃ ስፌት ቤት የተሠራውን ቀሚስ «ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ» ራዕይ 19፡8 ለራሳቸው ይመርጡ ዘንድ አስተምሯቸው፡፡ አንድ ነጥብ ስህተት የሌለበት የክርስቶስ ባህሪይ ለእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር በነፃ የተሰጠ ነው፡፡ የሚቀበሉት ሁሉ ግን እዚሁ ለብሱታል፡፡ EDA 279.5
ልጆች አዕምሮአቸውን በንጽህና አፍቃሪ ሐሳቦች ክፍት በሚያደርጉበት ጊዜና አፍቃሪና ጠቃሚ የሆኑ ተግባራት ሲፈጽሙ ራሳቸውን በርሱ የሚያምር የባህሪይ መጐናፀፊያ እያለበሱ መሆናቸውን ይማሩ፡፡ ይህ ጥያቄ በዚህ ዓለም እያሉ የሚያምሩና የሚወደዱ ያደርጋቸዋል፡፡ ከዙህ በኂላም በንጉሡ ቤት ተቀባይነትን የሚያገኙበት መጠሪያቸው ይሆናል፡፡ እርሱም የገባልን ቃል፡፡ EDA 280.1
«... ነገር ግን ልብሳቸውን ያላረከሱ .... የተገባቸውም ስለሆኑ ነጭ ልብስ ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ፡፡» ራዕይ 3፡4 EDA 280.2