ለአንድ ሕፃን የመጀመሪያ አስተማሪው እናቱ ናት፡፡ ትምህርቱን በተመለከተ በቀላሉ አመለካከቱ ሊጎዳ ወይም እጅግ ከፍተኛ እድገት ሊያሳይ የሚችልበት እድል በአመዛኙ በርሷ እጅ ውስጥ ነው፡፡ የልጁን ባህሪይ በክፉውም ሆነ በደጉ መጀመሪያ ለመቅረጽ እድል ተሰጥቷታል፡፡ ይህ ያገኘችው እድል ምን ያክል ዋጋ ያለው እንደ ሆነ ማስተዋል አለባት፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ስለሚኖራት ስልጠና ብዙ ጊዜ አይታሰብበትም፡፡ በትምህርት ላይ የሚኖራት ተጽዕኖ ሰፊ ሆኖ ሳለ የሚደረግላት ርዳታና ትብብር በሥርዓት የተቀነባበረ አይደለም፡፡ EDA 307.1
ሕፃን ልጅ የመንከባከብ ኃላፊነት ያለባቸው ብዙ እናቶች ለአካላቱ ግንባታ የሚያስፈልገውን ነገር ብዙ ጊዜ አያውቁም፡፡ የጤና ሕጎችን ወይም፣ ስለ አጠቃላይ የዕድገት መሠረታዊ ሐሳቦች የሚያውቁት በትንሹ ነው፡፡ ስለሕሊናና ስለመንፈስ መዳበርም ቢሆን በተሻለ መልኩ ያውቃሉ የሚባሉ አይደሉም፡፡ ሥራ ለመምራት ወይም በሕብረተሰቡ ውስጥ ጎላ ብለው ለመታየት ይችሉ ይሆናል፡፡ በሥነ-ጽሁፍና በሣይንስ መስክ ዋጋ ያለው አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ስለ ሕፃን አስተዳደግ የሚኖራቸው እውቀት አናሳ ነው፡፡ ዋናው ነገር በአሁኑ ወቅት የሰው ልጅ ዘር ውስጥ በአመዛኙ ሕፃናት የሚያልቁበት ምክንያት እናቶች ይኸንን እውቀት በማጣታቸውና በተለይም በመጀመሪያ የልጅነት ዓመታት እድሜአቸው አካላዊ እድገታቸውን በቸልታ ስለሚመለከቱት ነው፡፡ ልጆቹ እንደምንም ብለው እጎልማሳነት የእድሜ ደረጃ ላይ ከሚደርሱት መካከልም እንኳ ብዙዎች ሕይወት ሸክም ይሆንባቸዋል፡፡ EDA 307.2
ለሕፃኑ የጧትና የወደኋላ ዓመታት የትምህርት ጊዜ በእናቶች ላይ የሚኖረውን ያክል በአባቶች ላይም ኃላፊነት ወድቆባቸዋል፡፡ እናም ለሁለቱም ወላጆች ጥንቃቄ የተሞላበት የአስተዳደግ ቅድመ ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል፡፡ አባትና እናት የመሆንን ኃላፊነት ከመሸከማቸው በፊት ወንዶችና ሴቶች ለአካላዊ እድገት አስፈላጊ ከሆኑት ሕጎች ከአካላዊና አጠቃላይ የንጽህና ትምህርት (ሃይጅን) ጋር ከወላድነት ምሳሌ የፍቅር ስበት ጋር፣ በሽታዎችን ከማከም ዘዴዎች ጋር መተዋወቅና የሕሊና እድገት ሕጎችንና የሥነ ምግባርን ሥልጠና ማስተዋል አለባቸው፡፡ EDA 309.1
ይህ የትምህርት ሥራ ወሰን የሌለው አምላክ እናት እንድትሆን ለታሰበችው ሴት ከዙፋኑ ሆኖ መልዕክተኛ በመላክ መልስ ትሰጥ ዘንድ በመጠየቅ እጅግ በጣም ከፍተኛ ጉዳይ መሆኑን አመልክቷል፡፡ ‹‹ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? አለው›› መሣ 13፡12 ለአባትየውም ስለዚህ ተስፋ ስለ ተጣለበት ልጅ ጉዳይ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡ EDA 309.2
የወላጆቹ ሥራ አስፈላጊነት ሙሉ ለሙሉ ግንዛቤ እስከሚያገኝና ለተቀደሰው ኃላፊነታቸውም ሥልጠና እስከሚወስዱ ድረስ ትምህርት የታለመለትን አላማ በአንድ ጊዜ ሊያሟላ አይችልም፡፡ EDA 309.3
የዝግጅት ሥልጠና አስፈላጊነት በመላው ፍጥረተዓለም ተቀባይነት ያገኘ ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን እግጅ አስፈላጊ የሆነውን የዝግጅት ባሕሪይ የሚገነዘቡ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ወጣቶችን በማሰልጠን ሥራ ውስጥ ያለውን ኃላፊነት በደስታ የሚቀበል ሰው በሣይንስና በቀለም ትምህርት ዘርፎች የሚገኝ ትምህርት በቂ አለመሆኑን ይገነዘባል፡፡ መምህሩ መጽሐፍትን በማጥናት ከሚገኘው የበለጠ አጠቃላይ እውቀት ሊኖረው ይገባል፡፡ የአእምሮ ብርታት ብቻ ሣይሆን ሰፋ ያለ አስተሳሰብም ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡ አንድ ወጥ አቋም ያለው ብቻ ሣይሆን ልበ ሰፊም መሆን አለበት፡፡ EDA 309.4
አእምሮን የፈጠረና ሕግጋቱን የቀባ አምላክ አስፈላጊነቱን ወይም እድገቱን በትክክል ማስተዋል የሚችለው እርሱ ፈጣሪ ብቻ ነው፡፡ እርሱ የሰጠን የትምህርት መርሆች እንደ መለከያ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች እነሱ ብቻ ናቸው እያንዳንዱ መምህር የሚያስፈልገው የሙያ ብቃት፤ እነዚህን መሠረታዊ ሐሳቦችን ማግኘትን አምኖ መቀበል ሕይወቱን የሚቆጣጠሩለት የርሱ ኃይሎች ያደርጋቸዋል፡፡ EDA 310.1
በተግባራዊ ሕይወት ውስጥ ልምድን ማካበት የማይቀር የማይነጠል ጉዳይ ነው፡፡ በወጣቶች ዘንድ በጣም ብዙ ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች የሚታዩ ስለሆነ መምህሩ የሚናገራቸው ቃላት፤ ዝንባሌውና ምግባሩ ሁሉ እውነት የሆነውንና የላይኛውን አምላክ የሚወክል መሆን አለበት፡፡ ልጆች ፍቅርን ወይም ሌላ ጉድለትንና ድክመትን ለመረዳት በጣም ፈጣኖች ናቸው፡፡ ስለዚህ መምህሩ ሊያስተምራቸው የሚሻውን የድንቅ ነገሮች መሠረተ ሐሳቦች በራሱ ባህሪይ ውስጥ ካልተገለፁ በቀር የተማሪዎቹን ከበሬታ በምንም ሌላ መንገድ አያገኝም፡፡ ወደ በጎ አቅጣጫ ሊስባቸው የሚችለው ከነርሱ ጋር በሚኖረው የቀን ተቀን ማህበራዊ ግንኙነት ይኸንን ሲፈጽም ብቻ ነው፡፡ EDA 310.2
ለመምህሩ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ከሚያደርጉለት ሌሎች የብቃት ዓይነቶች ሁሉ አንደኛው አካላዊ ብርታቱ ነው፡፡ ጤናማ በሆነ መጠን ሥራውም ደህና ይሆንለታል፡፡ EDA 310.3
ስለዚህ ብርታቱንና ንቃቱን ጠብቆ ለማቆየት በርሱ በኩል የሚጠበቅበት ልዩ የሆነ ጥረት ለማከናወን የሚኖርበት ኃላፊነት በጣም አድካሚ ነው፡፡ በድካም ወደ መፍዘዝ፤ ወደ ቀዝቃዘዛነት፤ ወይም ብስጩነት ዘወትርም የልብና የአእምሮ ድካም ያጋጥመዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎችና አዝማሚያዎችን መቋቋም ብቻ ሣይሆን መነሻ ምክንያታቸውን ማስወገድም የርሱ ተግባር ነው፡፡ ልቡን ንፁህ፤ አስደሳች፤ የሚተመንና ሩህሩህ አድርጎ መጠበቅ አለበት፡፡ ሁልጊዜ ጥብቅ ጨዋና ተጫዋች ሆኖ ለመቆየት የአዕምሮና የነርቮቹን ብርታት መጠበቅ መቻል አለበት፡፡ EDA 311.1
በሥራው ውስጥ ከብዛት ይልቅ ጥራት በጣም አስፈላጊ ከመጠን በላይ መሥራትን በራሱ የስራ መሥመርም ቢሆን በአንድ ጊዜ እጅግ ብዙ ነገር ለመሥራት ለመሞከር ለሥራው ተገቢ ያልሆነ ሌላ ተጨማሪ የሥራ ኃላፊነት ከመቀበል መንፈስን ከማደስ ይልቅ አድካሚ የሚሆኑ፤ በደስታ፣ በፈንጠዝያና በሌሎችም ማህበራዊ ጭፈራዎች ውስጥ ራሱን ከማስገባት መጠበቅ አለበት፡፡ EDA 311.2
ከቤት ውጪ የሚደረግ እንቅስቃሴ ሁሉ በተለይም ጠቃሚ በሆኑ ሥራ ላይ አካልንና አእምሮን ለማዝናናት ዋነኛ መንገድ ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱ የመምህሩ ዝንባሌም ተማሪዎች ለጉልበት ሥራም የሚኖራቸውን ከበሬታና ፍላጎት ያነሳሳል፡፡ EDA 311.3
መምህሩ በማንኛውም ረገድ የጤናን መሠረተ ሃሣቦች ከልቡ በጥንቃቄ አንዲት ነገር እንኳ ሳያልፍ መከታተል አለበት፡፡ ይኸንን ማድረግ የሚገባው በርሱ ማንነት ላይ ምልክት ስለሚኖረው ብቻ ሳይሆን በተማሪዎቹ ላይም ተጽዕኖ ስለሚያሳድር ነው፡፡ በሁሉም ነገር ቁጥብ መሆን አለበት፡፡ በምግብና በመጠጥ፤ በአለባበስ፤ በሥራ፤ በመዝናኛ ሁሉ ምሳሌ መሆን አለበት፡፡ EDA 311.4
ከፍተኛ የቀለም ትምህርት እውቀት ከአካላዊ ጤንነትና ከባህሪይ ትክክለኛነት ጋር መቀናጀት አለበት፡፡ መምህሩ እውነተኛ የሆነ ብዙ እውቀት በኖረው መጠን ሥራው ይበልጥ የተቃና ይሆንለታል፡፡ አንድ የመማሪያ ክፍል ላይ ላዩን ብቻ የሚጋለብበት የሥራ ቦታ አይደለም፡፡ ግልብ በሆነ እውቀት የሚረካ መምህር ከፍተኛ የሥራ ብቃት ሊያሳይ አይችልም፡፡ EDA 312.1
በርግጥ የአንድ መምህር ጠቃሚነት የሚመሠረተው በተማሪው እውቀቱ መጠን ላይ ሣይሆን ዓላማው አድርጎ በአስቀመጠው የግብ ደረጃ ላይ ነው፡፡ እውነተኛ መምህር ደደብነት በተሞላበት አስተሳሰብ፤ በፈዛዛ አእምሮ ወይም የማስታወስ ችሎታው ደካማ ዝንጉ በሆነ ተማሪ የሚሰላች አይደለም፡፡ የተሻሉ ዘዴዎችን ያለ ማቋረጥ በመሞከር ከፍተኛ ውጤት ለማግኘት ይፈልጋል እንጅ፡፡ ሕይወቱ በሙሉ ሁልጊዜ እድገት የሚታይበት ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት መምህር ሥራ ውስጥ ተማሪዎቹን ከበሬታ ካላገኘና ተማሪዎቹ በርሱ ላይ የሚተማመኑ ካልሆኑ ጥረቱ ሁሉ ከንቱ ነው፡፡ EDA 312.2
መልካም የሆነውን ነገር ለመሥራት የሚያስችሉ እድሎችን ሁሉ ፈጥነው ለማሻሻል የሚችሉ መምህራን እጅግ ይወደዳሉ፡፡ እውነትንና ክብርን ከቅልጥፍና ጋር ያዋሃዱ፤ ራሳቸውን መቆጣጠር የሚችሉና ‹‹ጠንቃቃና ብቁ›› መምህራን ሐሳብን በመንፈስ ማነቃቃት፤ ኃይልን ማነሳሳት ድፍረትና ሕይወትን ማካፈል የሚችሉ መምህራን እጅግ ይፈለጋሉ፡፡ EDA 312.3
አንድ መምህር የሚያገኛቸው ጥቅሞች ውስን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የሚፈልገውን ያክል ከፍተኛ የቀለም ትምህርት ደረጃ ላይ አልደረሰ ይሆናል፡፡ ይሁንና ስለ ሰው ልጅ አፈጣጠር ትክክለኛ አመለካከት ያለው ከሆነ ሥራውን ከልቡ የሚያፈቅረው ከሆነ፤ የሥራውን ስፋት በአድናቆት የሚመለከት ከሆነ፤ ለማሻሻልም ቁርጠኛ አቋም ያለው ከሆነ፤ በቀና ልቦናና በቁጠባ ለመሥራት ፈቃደኛ ከሆነ የተማሪዎችን ፍላጎት የሚያስተውል ይሆናል፡፡ እናም ሁልጊዜ እድገት በሚያሳየው መንፈሱ እርሱ በሚፈልገው ዓይነት እንዲከተሉትና በእድገት ደረጃ ወደ ላይ ከፍ እያደረገ ሊመራቸው ይችላል፡፡ EDA 313.1
በመምህሩ ሥር ሆነው የሚመሩት ልጆትና ወጣቶች በተፈጥሮ ችሎታና በልምድ በስልጠናም ይለያያሉ፡፡ አንዳንዶች የተወሰነ ዓላማ ወይም የፀና መሠረታዊ ሐሳብ የላቸውም፡፡ ስለሚኖርባቸው ኃላፊነትና ስለሚኖሯቸው እድሎችም እንዲያውቁ መደረግ አለበት፡፡ ጥቂት ልጆች በቤታቸው ውስጥ በሚገባ ስልጥነው ይመጣሉ፡፡ ጥቂቶች ደግሞ የየቤቱ ጉደኞች ይሆናሉ፡፡ ትምህርታቸው ሁሉ ላይ ላዩን ለይስሙላ ብቻ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ሁኔታዎችን እንዲከተሉ ሲፈቀድላቸውና ኃላፊነትን እንዲወጡና ከባድ ሸክም እንዲቀበሉ ሲደረግ ጽናት፤ ቻይነትና ራስን መካድ ይሳናቸዋል፡፡ እንደ እነዚህ ዓይነት ልጆች የሥነ ሥርዓት ደንቦችን ሁሉ አስፈላጊ ያልሆኑ ገደቦች እንደሆኑ አድርገው ያስባሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ የተከለከሉና ተሸማቅቀው ተስፋ የቆረጡ ይኖራሉ፡፡ ሕገ ወጥ ቁጥጥርና የጭካኔ ርምጃ በውስጣቸው የሃይለኝነት የእምቢተኝነት ፀባይ እንዲያሳዩ ያደርጋቸዋል፡፡ እነዚህ የተጣመሙ ባህሪያት እንዲስተካከሉ ካስፈለገ፣ ሥራው በብዙ ሁኔታዎች ላይ በመምህሩ መከናወን ይኖርበታል፡፡ በተሳካ መልኩም ይፈፀም ዘንድ መምህሩ በተማሪዎች ላይ የሚታዩ ግድፈቶችና ስህተቶች መነሻቸው ምን እንደሆነ ጠለቅ ብሎ ለማየት የሚረዳው ርህራሄና ውስጡን የማየት ችሎታ ያስፈለገዋል፡፡ በተማሪም ለእያንዳንዱ በጣም እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ለሚያወላውሉና ኑሮ ሁልጊዜ ቀላል እንዲሆንላቸው ብቻ ለሚፈልጉ እንዲህ ዓይነት ማበረታታትና እርዳታም ተማሪው ሙሉ ኃይሉን ሥራ ላይ እንዲያውል የሚያነቃቃ፣ ተስፋ ለቆረጡት ርህራሄ በልባቸው ውስጥ መተማመንን የሚፈጥርላቸውና ለጥረት የሚያነሳሳቸውም ይሆን ዘንድ ዘዴ እውቀት ትዕግሥትና ጥብቅነት ሊኖረው ይገባል፡፡ EDA 313.2
መምህራን ብዙ ጊዜ ከተማሪዎቻቸው ጋር ማህበራዊ ግንኙነት መፍጠር ይሳናቸዋል፡፡ አብኛውን ጊዜ ርህራሄና ገርነት የሚያሳዩት በትንሹ ሲሆን አዘውትረው የቀጭን ጌታ(ዳኛ) ዓይነት ክብር የመፈለግ ሁኔታ ይታይባቸዋል፡፡ EDA 314.1
በምንም ዓይነት ምክንያት ቢሆን መምህሩ ምንጊዜም አድልዎ መፈፀም የለበትም፡፡ ጎበዝና ትኩረት የሚስበውን ልጅ ብቻ በመውደድና መበረታታት እርዳታና እንክብካቤ በእጅጉ የሚያስፈልጋቸውን ልጆች መተቸት፤ እነሱ ላይ ሲደርስ ትዕግሥት ማጣት፤ ወይም ርህራሄ አለማሳየት አጠቃላይ የመምህርነትን ምግባር አለመረዳትን መግለጽ ነው፡፡ የመምህሩ ባህሪይ የሚፈተነውና ለያዘው ቦታ ብቁ መሆኑ የሚረጋገጠው ለእነኝህ ስህተት ለሚወድቁና ለሚነሱ ልጆች በሚኖረው አያያዝ ነው፡፡ EDA 314.2
የሰው ነፍስን ያክል ነገር የሚመሩ ሰዎች ከባድ ኃላፊነት ወድቆባቸዋል፡፡ እውነተኛ አባትና እናት ምን ጊዜም የማይለቃቸውን የራሳቸውን ድርሻ እንደ መተማመኛ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ የልጅ ሕይወት ከህፃንነት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ቀን ድረስ ከወላጆቹ አስተያየት አንኳ ልጁን ወደ ጎን ወይም ወደ ክፉ በመለወጥ ይቀርጹታል፡፡ መምህሩም ከዚህ ኃላፊነት ይካፈላል፡፡ የዚህን ጉዳይ ቅዱስነትም ሊገነዘብና የሥራውን ዓላማም ያለ ማቋረጥ ሊጠብቅ ይገባዋል፡፡ ቀጣሪውን ክፍል ለማስደሰትና የትምህርት ቤቱን አቋም ለመጠበቅ፣ የቀን ተቀን ግዳጁን የሚፈጽም ብቻ ሣይሆን ለተማሪዎቹ እንደ ግለሰብነታቸው ከፍተኛውን መልካም ነገር ሊያስብላቸው፤ ሕይወት በእነርሱ ላይ የምትፈልግባቸውን ሥራ፤ ይህም የሚጠይቀውን ግልጋሎት ለዚህም የሚያስፈልገውን ዝግጅት እንዲሟላላቸው ከፍተኛውን መልካም ነገር ሊያስብላቸው ይገባል፡፡ ቀን በቀን የሚፈጽመው ሥራ ተማሪዎቹና በእነርሱም በኩል አልፎ በሌሎች ላይ እስከ ዘመን ፍፃሜ ድረስ የሚስፋፋና የሚያበረታታ፤ የማይለቅቅ ስበት ይኖረዋል፡፡ በዚያ ታላቅ ቀን እያንዳንዱ ቃና ተግባር በእግዚአብሔር ፊት በሚቀርብበት ዕለት የሥራውን ፍሬዎች ያገኛቸዋል፡፡ EDA 314.3
ይኽንን የሚገነዘብ መምህር በልቦናው ቀርጾ በቃሉ የያዘውን ትምህርት ዕለታዊ ሥራ ሲያከናውን ለጊዜው ተማሪዎቹ ከርሱ ቀጥተኛ እንክብካቤ ወጥተው ሲለቀቁ ሥራውን እንዳጠናቀቀ አድርጎ አይመለከትም፡፡ እነዚህን ልጆችና ወጣቶች በልቡ ውስጥ ይዟቸው ወደ ቤቱ ይሄዳል፡፡ እጅግ ክቡር ከሆነው ደረጃ ላይ ሊደርሱ የሚችሉበትን መንገድ ማመቻቸት የዘወትር ጥረቱ ይሆናል፡፡ EDA 315.1
እርሱ የሚሠራው ሥራ የሚያስገኘውን ዕድልና ጥቅሞች ለይቶ የሚያውቅ መምህር ራስን ለማሻሻል በሚደረግ ልባዊ የጥረት ጎዳና ላይ አንድም እንቅፋት እንዲኖረው አይፈቅድም፡፡ ምርጥ ከሆነው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ ማንኛውንም ስቃይ (መስዋዕትነት) ይችላል፡፡ ተማሪዎቹ እንዲሆኑለት ለሚመኘው ነገር ሁሉ ራሱም እንደዚያ ሆኖ ለመገኘት ይጥራል፡፡ EDA 315.2
የኃላፊነት ስሜት በጥልቅ በተሰማውና ራስን ለማሻሻል ጥረቱ ልባዊ በሆነ መጠን፣ መምህሩ ራስ ወዳድ አለመሆንን የሚያደናቅፉ ጉድለቶችን በግልጽ ማስተዋልና በእነርሱም ላይ በፍጥነት የሚፀፀት ይሆናል፡፡ የሥራውን ስፋት በውል በተገናዘበና፤ ችግሮቹንና የሚኖሩትንም መልካም እድሎች ሲረዳ ከልቡ እንዲህ በማለት ይጮሃል፡፡ ‹‹ለእነኝህ ሁሉ ነገሮች ብቃት የሚኖረው ማን ነው» EDA 315.3
ውድ መምህር ሆይ ብርታትና አመራር እንደሚያስፈልግህ ስትረዳ፤ የሰው ልጅ ሊያቀርብልህ የማይችለውን፣ ፍላጎት፣ ግሩም ድንቅ መካሪ፤ የሆነውን የርሱን የተስፋ ቃል እንድታስብ አደራ እልሃለሁ፡፡ EDA 316.1
«እነሆ» ይላል ‹‹በአንተ ፊት የተከፈተ በር ሰጥቼሃለሁ ማንም ሊዘጋው አይችልም፡፡›› ራዕ 3፡8 EDA 316.2
‹‹ወደ እኔ ጩኸ እኔም እመልስልሃለሁ፡፡›› ‹‹እመራሃለሁ በምትሄድበት መንገድ አስተምርሃለሁ፡፡ በዐይኔ እመራሃለሁ፡፡›› ኤር 33፡3 መዝ 32፡8 ‹‹እኔ እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናተን ጋር ነኝ፡፡›› ማቲ 28፡20 EDA 316.3
ለሥራህ ከፍተኛ ዝግጅት እንዲረዳህ የመምህራን ልዑል ወደተናገራቸው፤ ወደኖረው ሕይወትና፣ ወደተጠቀመባቸው ዘዴዎች እናመለክትሃለን፡፡ እርሱን አመዛዝነህ እያሰብህ እንድትይዘው አጥብቀን እናስታወስሃለን፡፡ እውነተኛ፣ ከፍተኛውና ድንቅ ሃሳብህ እዚህ ላይ ይሁን፡፡ የመለኮታዊው መምህር መንፈስ የልብህና የሕይወትህ ባለቤት እስከሚሆን ድረስ ይኽንን አጥብቀህ ያዝ፣ በርሱ ላይ እረፍ፡፡ EDA 316.4
‹‹የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን›› ‹‹ያንን መልክ እንመስል ዘንድ . . . እንለወጣለን፡፡›› 2ኛ ቆሮ 3፡18 EDA 316.5
መምህር ሆይ በተማሪዎችህ ላይ የሚኖረው የኃይል ምስጢር ይህ ነው፡፡ ሁልጊዜ እርሱን ጠይቀው፡፡ EDA 316.6