በትክክል የሚራመድ በእርግጠኝነት ይራመዳል መጽሐፍ ቅዱስ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያላደረገበት ምንም ዓይነት ሕጋዊ የሆነ የሥራ ዘርፍ የለም፡፡ የትጋት የታማኝነት የቁጠባ፣ በምግብና መጠጥ ጥንቁቅ ስለመሆን እና የልብ ንጽህና መርሆች የእውነተኛ ስኬት ምስጢሮች ናቸው፡፡ እነኝህ መሠረታዊ ሐሳቦች በመጽሐፈ ምሳሌ ውስጥ ተካትተው የተግባር ጥበብ መዝገብ ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ ነጋዴው የእጅ ጥበብ ባለሙያው ወይም በአንድ መሥሪያ ቤት ውስጥ የሥራ ኃላፊ የሆነው ሰው ለራሱም ሆነ እሱ ለሚያሠራቸው ቅጥር ሠራተኞች በዚህ የጠቢቡ ሰው ቃላት ውስጥ ከሚገኙ መሠረታዊ ፍሬ ሐሳቦች ውጪ የተሻለ ሊያገኝ የሚችለው ከየት ነው? EDA 148.1
«በሥራው የቀጠረ ሰውን አይተሃልን? በነገሥታት ፊት
ይቆማል በተዋረዱ ሰዎች ፊትም አይቆምም፡፡»
ምሳ 22፡29
«በድካም ሁሉ ልምላሜ ይገኛል ብዙ ነገር በሚናገር
ከንፈር ግን ድህነት ብቻ አለ፡፡»
ምሳ 24፡23
«የታካች ሰው ነፍስ ትመኛለች አንዳችም አታገኝም፡፡»
«ሰካራምና ሆዳም ይደኸያሉና፡፡ የእንቅልፍም ብዛት
የተቦጫጨቀ ጨርቅ ያስለብሳልና፡፡»
ምሳ 13፡4 ፣ 23፣21
«ዘዋሪ ሐሜተኛ ምስጢርን ይገልጣል፡፡ ከንፈሩን
የሚያሞጠሙጥ ሰው አትገናኘው፡፡»
ምሳ 20፡19
«ጥቂት ቃልን የሚናገር አዋቂ ነው፡፡» ነገር ግን «ሰነፍ
ቃሉ ግን እንዲህ ባለ ነገር ይጣመራል፡፡»
ምሳ 17፡27 ፣ 20፡3
«በኃጥአን መንገድ አትግባ» «በፍም ላይ የሚሄድ
እግሮቹስ የማይቃጠሉ ማነው?»
ምሳ 4፡14 ፣ 6፡28 EDA 148.2
«ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፡፡
ምሳ 13፡20
«ብዙ ወዳጆች ያሉት ሰው ይጠፋል ነገር ግን
ከወንድም አብልጦ የሚጠጋጋ ወዳጅ አለ፡፡»
ምሳ 18፡24
በአጠቃላይ እትስ በራሳችን የሚኖርብን ግዴታ ዞሮ ዞሮ
በክርስቶስ ቃል ተጠቃልሏል፡፡ «እንግዲህ ሰዎች
ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፡፡»
ማቴ 7፡12
በቅዱስ መጽሐፍት ውስጥ ዘወትር በጥብቅ
ተደጋግመው ለተሰጡት ማስጠንቀቂያዎች ተገቢውን ትኩረት
ያላደረገ ነገር ግን ኪሳራ ሳይደርስበት ያመለጠ ስንት ሰው
ነው? ባለጠጋ ለመሆን የሚቸኩል ግን ሳይቀጣ አይቀርም፡፡»
ምሳ 28፡20
«በችኮላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች ጥቂት በጥቂት
የተከማቸች ግን ትበዛለች፡፡»
ምሳ 13፡11
«በሀሰተኛ ምላስ መዝገብ ማከማቸት የሚበን ጉም ነው፡፡»
ምሳ 21፡6
«ተበዳሪም የአበዳሪው ባሪያ ነው፡፡»
ምሳ 22፡7
«ለማያውቅ የሚዋስ ክፉ መከራን ይቀበላል፡፡
ዋስነትን የሚጠላ ግን ይድናል፡፡»
ምሳ 11፡15
«የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ ወደ
ድሃ አደጐች እርሻ አትግባ ታዳጊአቸው ጽኑ ነውና፡፡
እሱም ፍርዳቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳልና፡፡» «ለራሱ ጥቅም
ለመጨመር ሲል ድሀን የሚጐዳ ባለጠጋም የሚሰጥ እርሱ
ወደ ድህነት ይወድቃል፡፡» «ጉድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፡፡
ድንጋይን የሚያንከባልል ይገለጥበታል፡፡»
ምሳ 23፡10‚11 ፣ 22፡16፣ 26፡27 EDA 149.1
እንግዲህ የሕብረተሰብ ደህንነት የዓለማዊውና የመንፈሳዊውን ማህበረሰቦች ሁሉ ባንድ ላይ የታሰሩባቸው መሠረታዊ ሀሳቦች እነኝህ ናቸው፡፡ ለንብረትና ለሕይወት መከበር ማረጋገጫ የሚሰጡት እነኝሁ መሠረታዊ ሀሳቦች ናቸው፡፡ እምነትና ትብብርን እስካስገኘ ድረስ በቃሉ ውስጥ እንደተሰጠና አሁንም ፈለጉን መከተለ እንደሚቻለው በተበላሹ መስመሮች ክፉኛ በተበከሉ በሰው ልቦች ውስጥ እንኳ ዓለም የእግዚአብሔር ሕግ ውለታ አለባት፡፡ EDA 149.2
የባለመዝሙሩ ቃላት «ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል፡፡» መዝ 119፡72 ሲል በሃይማኖታዊ አመለካከት በስተቀር በሌላ እውን ሊሆን የማይቻለውን እውነታ ያብራራል፡፡ እነኝህ ቃላት ፍፁም እና በሥራ ዓለም ውስጥ የታወቀውን ጉዳይ ይገልፃሉ፡፡ በዚህ ገንዘብ የማግኘት ፍላጐት እጅግ ከፍተኛ በሆነበትና እሽቅድድሙም በጦፈበት የማግኘት ዘዴውም ይሉኝታና ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌለበት ሆኖ በተፋፋመበት ባሁኑ ሰዓት እንኳ ኑሮውን ለሚጀምር ወጣት መረጋጋት ትጋት በምግብና መጠጥ ራስን መጠበቅ የልብ ንጽህና እና የተስተካከለ ቁጠባ ልክ የሌለው ገንዘብ ብቻ ከማጋበስ ይልቅ እጅግ የተሻለ ካፒታልና የሚመሰገን ሥራም ነው፡፡ የእነኝህን የጥራት መመዘኛዎች ከሚያደንቁና መጽሐፍ ቅዱስን እንደምንጭ አድርገው ከሚጠቀሙበት ሰዎች መካከል ይኸንኑ የሚያምኑበትን መሠረተ-ሐሳብ እንኳ በውል የሚገነዘቡ ጥቂቶች ብቻ ናቸው፡፡ EDA 150.1
በሥራ ክንውንና በእውነተኛ ስኬታማነት መሠረት ውስጥ መቀመጥ ያለበት የእግዚአብሔርን ባለቤትነት የመገንዘብ ዕውቀት ነው፡፡ የነገሮች ሁሉ ፈጣሪ የመጀመሪያው ባለቤት ጌታ እሱ ነው፡፡ እኛ አገልጋይ ሠራተኞቹ ነን፡፡ ያለን ሁሉ ከእርሱ የተሰጠን ነው፡፡ በእርሱ መመሪያ መሠረትም ልንመራበት ይገባል፡፡ EDA 150.2
ይህ በእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር ላይ የወደቀ ግዳጅ ነው፡፡ የሰው ልጅ በሚያከናውነው ማናቸውም ዓይነት የሥራ እንቅስቃሴ ሁሉ ውስጥ የሚኖር ነው፡፡ ተገነዘብነውም አልተገነዘብነውም እኛ ከእግዚአብሔር በተሰጠን መክሊቶች እና ልዩ ልዩ ችሎታዎች በዚህ ዓለም ላይ እርሱ በሚመድበን ቦታና እርሱ ለመረጠን አገልጋዮቹ ነን፡፡ EDA 150.3
ለእያንዳንዱ «እንደሥራው» ችሎታዎቹ ወደሚመሩት ለራሱና ለወገኖቹ ጥቅም ለእግዚአብሔርም ታላቅ ክብር የሚያስገኙለት ሥራዎች ተሰጥቶታል፡፡ EDA 151.1
ስለዚህም እኛ የምንሠራው ሥራ ወይም የተጠራንበት ጉዳይ የእግዚአብሔር ታላቅ እቅድ አንዱ አካል ነው፡፡ በእርሱ ፈቃድ መሠረት እስከተመራን ድረስ ለውጤቶቹ ኃላፊ የሚሆነው እሱ ራሱ ነው፡፡ ‹ከእኛ ጋር የሚሠራ› 1ኛ ቆሮን 3፡9 በእኛ በኩል የሚፈለገው ከእርሱ መመሪያዎች ጋር መተባበር ብቻ ነው፡፡ ለኑሮ መጨነቅ ቦታ አይኖረውም፡፡ ትጋት ታማኝነት ጥንቁቅ መሆን በልክ ቆጣቢ መሆንና ነገሮችን በጠንቃቄ መለየት ተፈላጊ ነገሮች ናቸው፡፡ እያንደንዱ ክህሎታችን አስከመጨረሻ ጣራው ድረስ ሥራ ላይ መዋል አለበት፡፡ ነገር ግን መተማመን ያለብን በሚሳካልን ውጤት ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ነው፡፡ ያ እስራኤሎችን በበረሃ ውስጥ የመገበው ቃል ዛሬም ኃይል አለው፡፡ «ምን እንበላለን ምንስ እንጠጣለን ብላችሁ አትጨነቁ ... አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ሌላው ነገር ሁሉ ይጨመርላችኋል፡፡» ማቴ 6፡31-33 EDA 151.2
ሰዎች ሐብት እንዲያገኙና እንዲከብሩ ኃይል የሚሰጣቸው አምላክ በስጦታው ውስጥ ግዴታም ጨምሯል፡፡ እርሱ የሚፈልግብን ከምናገኘው ነገር ሀሉ የተወሰነ ብቻ ለእርሱ ከፍለን እንድንሰጥ ብቻ ነው፡፡ አሥራት መክፈል ለጌታ ነው፡፡ » የምድርም አሥራት ወይም የምድር ዘር ወይም የዛፍ ፍሬ... የበግም የፍየልም አሥራት ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፡፡» ዘለ 27፡30-32 ያዕቆብ በቤቴል ያደረገው ልመና ግዳጅ ማለት እስከምን ድረስ እንደሆነ ያሳያል፡፡ «አንተ ከሰጠኸኝ ሁሉ» «ከአሥር አንድ ለአንተ እሰጣለሁ፡፡» ዘፍ 28፡22 EDA 151.3
የእግዚአብሔር ትዕዛዝ የሚለው «አሥራትን ሁሉ ወደጐተራ አገቡ፡፡» ነው፡፡ ሚል 3፡10 የተራድኦ ገንዘብ ለማሰባሰብ የሚደረግ የምስጋናም ሆነ የልግስና ጥያቄ አይደለም፡፡ የታማኝነት ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ አሥራት የጌታ ነው፡፡ የራሱ ከሆነው ውስጥ ለእርሱ እንድንሰጥ አስቀምጦልናል፡፡ EDA 152.1
«በመጋቢዎች ዘንድ የታመነ ሆኖ መገኘት ይፈለጋል፡፡» 1ኛ ቆሮ 4፡2 ታማኘት በሥራ ዓለም ውስጥ ዋናው መሠረታዊ ሐሳብ ከሆነ ለእግዚአብሔር የሚኖርብን ግዴታ የሌላው ነገር ሁሉ መሠረት የሆነውን ግዴታ መገንዘብ የለምንምን? EDA 152.2
መጋቢ አገልጋይ በተባሉት ቃላት ለእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን ለሰውም በአንድ ግዴታ ውስጥ እንደገባን ያመለክታል፡፡ ለታዳጊአችን መድህን ወሰን የሌለው ፍቅር እያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር ለተሰጠው ሕይወት ውለታ አለበት፡፡ ምግባችን ልብሳችን መጠለያችን፣ ሰውነት አእምሮና ነፍስ ሁሉ በእርሱ ደም የተገዙ ናቸው፡፡ ስለዚህም በታዘዝነው የምስጋናና የአገልግሎት ግዴታ ክርስቶስ ከወገኖቻችን ጋር አስተሳሰሮናል፡፡ «በፍቅር እርስ በራሳችሁ እንደባሪያ ሁኑ፡፡» ገላ 5፡13 በማለት ትዕዛዝ ሰጥቶናል፡፡ «እውነት እላችሏለሁ ከሁሉ ከሚያንሱ ከአነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት፡፡» ማቴ 25፡40 EDA 152.3
«እዳ አለብኝ» ይላል ጳውሎስ ሲናገር «ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩማ፣ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም፡፡» ሮሜ፡ 1፡14 ለእኛም እንዲሁ ነው፡፡ ሕይወታችንን ከሌሎች የተሻለ አድርጐ ለባረከን ልንጠቅም ለምንችለው ሰው ሁሉ ግዴታ አለብን፡፡ EDA 152.4
እነኝህ እውነቶች ደሳሳ ጐጆ ላለው ሰው የሆኑትን ያክል ብዙ ክፍሎች ለሚቆጥረውም የተለዩ አይደሉም፡፡ ያሉን ዕቃ ንብረቶች የእኛ አይደሉም፡፡ ይህ እውነታም ከአዕምሮአችን ነን፡፡ ለእግዚአብሔርና ለሰው ባለብን ግዴታም ለወገኖቻችን ደህንነትና ለአሁኑም ሆነ ለሚመጣው የሕይወት ግባችን በምንሠራው ላይ የሚመሠረት ይሆናል፡፡ EDA 153.1
«ያለውንየሚበትን አንዳንዱ ሰው አለ ይጨመርለታ
ልም፡፡ ያለቅጥ የሚነፍግ ሰውም አለ ይደኸያልም፡፡» EDA 153.2
«እንጀራህን በውኃ ላይ ጣለው ከብዙ ቀን በኋላ ታገኘዋለህና፡፡» EDA 153.3
«ባለጠጋ ለመሆን አትድከም፡፡ የገዛ ራስህን ማስተዋል ተው፡፡ በርሱ ላይ አይነህን
ብታዘወትርበት ይጠፋል ባለጠግነት ወደሰማይ እንደሚበርር እንደ
ንሥር ለራሱ ክንፍ ያበጃል፡፡» ምሳ 23፡4-5 EDA 153.4
«ሰጡ ይሰጣችሁማል፡፡ በምትሠፍሩበት መሥፈሪያ
ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፡፡ የተጨቆነና የተነቀነቀ
የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ
ይሰጣችኋል፡፡» ሉቃ 6፡38
EDA 153.5
«እግዚአብሔርን ከሀብትህ አክብር ከፍሬህም ሁሉ በኩራት ጐተራህም እህልን
ይሞላል፡፡ መጥመቂያህም በወይን ጠጅ
ሞልታ ትትረፈረፋለች፡፡» ምሳ 3፡9-10 EDA 153.6
«በቤት ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጐተራ አግቡ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ በረከትንም አትረፍርፌ ባለፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለእናንተ ነቀዙን እገስፃለሁ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም፡፡ በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፡፡ የተድላ ምድር ትሆናላችሁና አህዛብ ሁሉ ብፁአን ብለው ይጠሯችኋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር» ሚል 3፡10-12 «በሥርዓቱ ብትሄዱ ትዕዛዛቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉትም ዝናባችሁን በወቅቱ አዘንባለሁ፣ ምድሪቱመ እህሏን ትሰጣለች የሜዳው ዛፎችም ፍሬአቸውን የሰጣሉ፡፡ የእህሉም ማበራየት በእናንተ ዘንድ እስከወይኑ መቆረጥ ይደርሳል፡፡ እስከትጠግቡም ድረስ እንጀራችሁን ትበላላችሁ በምድራችሁም ላይ ሰላምን እሰጣለሁ፤ ማንም ሳያስፈራችሁ ትተኛላችሁ፡፡» ዘለዋ 26፡3-6 «ፍርድን ፈልጉ የተገፋውን አድኑ ለድሀ አደጉ ፍረዱለት ስለ መበላቲቱም ተምዋገቱ፡፡» «ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል፡፡ እግዚአብሔር ይጠብቀዋል ሕያውም ያደርገዋል በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፡፡ በጠላቶቹም እጅ አያሳልፈውም፡፡» «ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፡፡ በጐነቱንም መልሶ ይከፍለዋል፡፡» ኢሳ 1፡17 መዝ41፡12 ምሳ 19፡17 EDA 153.7
ንብረቱን ሁሉ በዚህ ላይ የሚያፈስስ ሰው እጥፍ ድርብ መዝገብ ያገኛል፡፡ በተጨማሪም በጥበብ ከተሻሻለው ሌላ ለዘለዓለም የማያልቅ ሐብት ያን በምድርም ሆነ በሰማይ እጅግ ድንቅ የሆነውን ንብረት ወይም የባህሪ መዝገብ ያካብታል፡፡ EDA 154.1