እግዚአብሐርን ለሚያፈቅሩ «እንደ አሳቡም ለተጠሩት» ሰዎች በሚያሳዝን ሕይወት ውስጥ ያገለገሉ ሰዎች ታሪክ ገና ከፍተኛ ትምህርት ያቀርብላቸዋል፡፡ (ሮሜ 8፡28) «እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር እኔም አምላክ ነኝ፡፡» ኢሳ 43፡12 እርሱ ቸር እንደሆነ ቸርነቱም ታላቅ እንደሆነ ይመስክራሉ፡፡ «ለዓለም ለመላዕክትም ለሰዎችም መጫዎቻ ሆነናልና፡፡» ሮሜ 4፡9፡፡ EDA 170.2
ራስን አለመውደድ የእግዚአብሔር መንግሥት መሠረተ ሐሳብ ነው፡፡ ሰይጣንም በጣም የሚጠላውና አስከመኖሩም የሚክደው ይኸንን መሠረተ ሐሳብ ነው፡፡ ከታላቁ ተጋድሎ መጀመሪያ አንስቶ የእግዚአብሔር የተግባር መመሪያ ራሱን በመውደድ ላይ የተመሠረተ እንደሆነ ለማስመሰል ብዙ ጥረት ከማደረጉም በላይ ለእግዚአብሔር የሚያገለግሉ ሰዎችንም የሚቀርበው እንደዚሁ እያለ ነው፡፡ ሰይጣን የሚለውን ነገር ፋርሽ ወይም ውድቅ ማድረግ ደግሞ የክርስቶስና የርሱን ስም የያዙ ሰዎች ሥራ ነው፡፡ EDA 170.3
የሱስ፣ ራሱን የራስን አለመውደድ መግለጫ አድርጐ ለመስጠት ነው በሰብዓዊነት መልክ የመጣው፡፡ ይኸንን መርህ የሚቀበሉ ሁሉ ከእርሱ ጋር ይኸንኑ በተግባራዊ ሕይወት የሚገልፁ ሠራተኞች እንዲሆኑ ነው፡፡ ትክክል ስለሆነ ትክክለኛውን መምረጥ፤ በማንኛውም ስቃይና መስዋዕትነት ፀንቶ መቆም «የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፡፡ ጽድቃቸውም ከእኛ ዘንድ ነው ይላል እግዚአብሔር፡፡» ኢሳ 54፡17 EDA 171.1
በዓለም ታሪክ መጀመሪያ አካባቢ ከሰይጣን ጋር ትልቅ ተጋድሎ ያደረገ ሰው ታሪክ ተመዝግቧል፡፡ EDA 171.2
ስለ ኢዮብ፡፡ የኡዝ አለቃ ስለነበረው ኢዮብ ልቦችን መርማሪ የሆነው ጌታ የሰጠው ምስክርነት «በምድር ላይ እንደ እርሱ ፍፁምና ቅን እግዚአብሔርን የሚፈራ፡፡» የሚል ነበር፡፡ EDA 171.3
ይኸንን ሰው በመቃወም ነበር ሰይጣን ንቀት የተሞላበት ክስ ያቀረበው፡፡ «በውኑ ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራ በከንቱ ነውን? እርሱንና ቤቱን በዙሪያውም ያሉትን ሁሉ አላጠርክለትምን?... እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ዳብስ በእውነት በፊትህ ይሰድብናል፡፡» EDA 171.4
ጌታም ለሰይጣን መልሶ እንዲህ አለው፡፡ «እነሆ እርሱ ያለው ሁሉ በእጅህ ነው፡፡ ነገር ግን በእርሱ ላይ እጅህን አትዘርጋ አለው፡፡» EDA 171.5
እንዲ ስለተፈቀደለትም ሰይጣን የኢዮብን ሀብት በሙሉ ወሰደ፡፡ ፍየሎቹንም፣ በጐቹንም፣ ወንድና ሴት አገልጋዮቹንም ወንድና ሴት ልጆቹንም ወሰደበት፡፡ ከዚያ በኋላ ሰይጣን ኢዮብን «ከእግሩ ጫማ ጀምሮ እስከ እናቱ ድረስ በክፉ ቁስል መታው፡፡» ኢዮ 1፡8-12፣2፡5-7 EDA 171.6
አሁንም በጽዋው ላይ ሌላ መራራ ተጨመረበት፡፡ ጓደኞቹ ይኸንን መጥፎ እጣ እና አጋጣሚ እያዩ በተመታና ሸክም በበዛበት መንፈስ ላይ እንደወንጀለኛ ይከስሱት ጀመረ፡፡ EDA 172.1
በሰማይም በምድርም ሁሉም የሸሸው ይመስል ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ላይ የፀና ነበር፡፡ ሕሊናውም የተረጋጋና ሐሳቡም የተሰባሰበለት ጥብቅ ሰው ስለነበረ እንደዚያ በስቃይና በቀውጢ ውስጥ እያለ እንዲህ እያለ ይጮህ ነበር፡፡ EDA 172.2
«ነፍሴ ሕይወቴን ሰለቸቻት፡፡»
«በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ
ቁጣህ እስከሚያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ
ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ፡፡
አዮብ 10፡1፤14፡13፡፡
«እነሆ፣ ስለተደረገብኝ ግፍ ብጮህ ማንም
አይመልስለኝም፡፡
አሰምቸም ብጠራ ፍርድ የለኝም፡፡...
ክብሬንም ገፈፈኝ ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወሰደ፡፡
ወንደሞቼን ከእኔ ዘንድ አራቀ የሚያውቁኝም
አጥብቀው ተለዩኝ... ወዳጆቼም ረሱኝ
እኔ የምወዳቸው በላየ ተገለበጡ፡፡ እናንተ
ወዳጆቼ ሆይ ማሩኝ የእግዚአብሔር እጅ
መትታኛለችና ማሩኝ»
«እርሱን ወዴት እንዳገኘው ምነው ባወቅሁ ወደ
ተቀመጠበትስ ስፍራ ምነው
በደረስሁ፡፡ እነሆ ወደፊት እሄዳለሁ እርሱም የለም፡፡
ወደ ኋላም እሄዳለሁ እኔም አላስተውለውም፡፡
ወደሚሠራበት ወደ ግራ ብሄድ አልመለከተውም፡፡
በቀኝም ይሰወራል አላየውምም፡፡ የምሄድበትን መንገድ
ያውቃል ከፈተነኝም በኋላ እንደወርቅ እወጣለሁ፡፡»
«ቢገድለኝ እንኳ እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፡፡» «እኔ ግን የሚቤዤኝ ሕያው እንደሆነ በመጨረሻም
ዘመን በምድር ላይ እንዲቆም፡፡ ይህ ቁርበቴም ከጠፋ
በኋላ በዚያን ጊዜ ከሥጋየ ተለይቼ እግዚአብሔርን
እንዳይ አውቃለሁ፡፡ እኔ ራሴ አየዋለሁ፡፡ ዐይኖቼም
ይመለከቱታል፡፡ ከእኔም ሌላ አይደለም፡፡» ኢዮብ 19፡7-21፣23፡3-10፣13፡15፣19፡25-27 EDA 172.3
ለኢዮብ እንደእምነቱ ሆነለት፡፡ «ከፈተነኝ በኋላም፡፡» አለ ኢዮብ «እንደወርቅ እወጣለሁ» ኢዮብ 23፡10፡፡ እንደዚያ ሆነ፡፡ በትዕግሥት በመቆየት የራሱን ባህሪ ጥንካሬ አረጋገጠ፡፡ በዚሁም እርሱ የወከለውንም ባህሪ ጭምር፡፡ «ኢዮብም ስለወዳጆቹ በፀለየ ጊዜ እግዚአብሔርም ቀድሞ በነበረው ፈንታ ሁለት እጥፍ አድርጐ ለኢዮብ ሰጠው፡፡» ኢዮብ 42፡10-12 EDA 173.1
ራስን አሳልፎ በመስጠት መስዋዕትነት መክፈል ከክርስቶስ ጋር ወዳጅነት ከያዙ ሰዎች አንድ በሀዲስ ኪዳን አንድ ደግሞ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ተመዝግበዋል፡፡ ስማቸውም ዮናታንና ዮሐንስ መጥምቁ ይባላሉ፡፡ EDA 173.2
ዮናታን በልደት የዙፋን ውርስ የሚገባው ሰው ሆኖ ሳለ በመለኮት አዋጅ ወደጐን የተተወ መሆኑን ያወቀ ለተቀናቃኙ ገርና ታማኝ ጓደኛ የነበረ፤ ራሱን አደጋ ላይ እስከሚጥል ድረስ ለዳዊት ሕይወት የመከተ፣ ኃይሉ እየቀሰ በመጣ ጊዜ በእነኛ የጨለማ ቀናት ከአባቱ ጐን ፀንቶ የቆመ እናም በመጨረሻም ከጐ የወደቀ የዮናታን ስም በሰማይ የተመዘገበ፤ በምድርም ራስን ባለመውደድ ፍቅር ህልውናና ኃይል በምስክርነት የሚቆም ነው፡፡ EDA 173.3
ዮሐንስ መጥምቁ የመሲህን መምጣት አዋጅ ነጋሪ በሆነው ገጽታው አገሬውን በሙሉ ቀሰቀሰው፡፡ ከቦታ ወደ ቦታ በሚዘዋወርበት ሁሉ በእየርምጃዎቹ ትልቁም ትንሹም ባለሥልጣኖችም ሳይቀሩ ብዙ ሕዝብ ይከተለው ነበር፡፡ እርሱ ይመሰክርለት የነበረው በመጣ ጊዜ ግን ሁሉም ነገር ተለወጠ፡፡ ሕዝቡ የሱስን ይከተል ጀመር፡፡ የዮሐንስ ሥራም እየተጠናቀቀ ሄደ፡፡ ይሁንና ከእምነቱ ወዲያና ወዲህም አልተነቃነቀመ፡፡»እርሱ ሲልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል፡፡» አለ ዮሐ 3፡30 EDA 173.4
ዘመን እያለፈ ሄደ ዮሐንስ በአርግጠኝነት የጠበቀው መንግሥት ግን አልተቋቋመም፡፡ በሄሮድስ ምድር ቤት ታሥሮ ሕይወት ከሚሰጥ አየርም እንኳ ታግዶና የበረሃው ነፃነትም ቀርቶበት በመጠባበቅ ቆየ፡፡ EDA 174.1
የጦር ኃይል አልታየም የእሥር ቤቱ በሮች የከፈለ ነገርም የለም፡፡ ነገር ግን የበሽተኞች መፈወስ፣ የወንጌል መስበክ፣ የሰዎች ነፍስ መነሳሳት የክርስቶስን ተልዕኮ መሠከረ፡፡ EDA 174.2
በእስር ቤት ውስጥ ብቻውን ሆኖ ወደ የትኛውም አቅጣጫ መንገድ ማየት በማይችልበት ሁኔታ እንደ ጌታው ሁሉ በገርነት ዮሐንስ እምነትንና የክርስቶስን ወዳጅነት መስዋዕትነት እስከመቃብሩ ድረስ ተከተሉት፡፡ በዩኒቨርስ ላይ ያሉ የወደቁና ያልወደቁም ጭምር ራሱን የማይወድ ቅን አገልጋይ መሆኑን መሠከሩለት፡፡ EDA 174.3
ከዚያ ጊዜ ጀምሮም ባለፉት ትውልዶች ሁሉ ላይ ስቃይ ያጋጠማቸው ነፍሳት በዮሐንስ ሕይወት ምስክርነት ተጽናንተው ቀጥለዋል፡፡ በእስር ቤት፣ ለስቅላት በተዘጋጀው መድረክ ላይ፣ በእሳት ነበልባል ላይ ክርስቶስ «እውነት እላችኋለሁ ከሴቶች ከተወለዱ መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሳም» ማቴ11፡11 በማለት ጌታ በመሰከረለት በዚህ ሰው ትዝታ ብዙ ሴቶችና ወንዶች በበርካታ የጨለማ ምዕተ ዓመታት ውስጥ ተበረታትተውበታል፡፡ EDA 174.4
«እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጊዲዮንና ስለ ባራቅ ስለ ሳምሶንም ስለ ዮፍታሄም... ስለ ሣሙኤልም ስለ ነቢያትም... እነሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሱ፡፡ ጽድቅን አደረጉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፣ የአንበሶችን አፍ ዘጉ የእንስሳትን ኃይል አጠፉ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው በረቱ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ የባዕድ ጭፍሮች አባረሩ፡፡ EDA 175.1
«ሴቶች ሙታናቸውን በትንሳኤ ተቀበሉ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከሞት ድረስ ተደበደቡ፡፡ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወህኒ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ ተፈተኑ በመጋዝ ተሰነጠቁ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፡፡ ሁሉ እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፡፡ ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ ዞሩ፡፡ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ፡፡ EDA 175.2
እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም ያለ እኛ ፍፁማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገር አስቀድሞ አይቶ ነበር፡፡» ዕብ 11፡32-40 EDA 175.3