Go to full page →

በተፈተናችሁ ጊዜ እቃገ 29

በሰዎች ሁሉ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም፤
እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ
እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን
በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣
መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።
1 ቆሮ 10፡13

ልጆች ሆይ! እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ፤
እነርሱንም አሸንፋችኋል፤ ምክንያቱም
በእናንተ ውስጥ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣል፡፡
1 ዮሐ 4፡4

ምንም ያህል ጠንካራ ሲሆን ማንኛውንም ክፉ አመል ለመለወጥ፣ እያንዳንዱንም ፈተና ለመቋቋም የሚያስችል ጸጋ በክርስቶስ በኩል ሊሰጠን እግዚአብሔር ቃል ገብቷል፡፡ ሰዎች በእርሱ ላይ ባላቸው እምነት በኩል ሊያገኙ የማይችሉትን ባህርይ ኢየሱስ በምድር ላይ በሥጋ በኖረው ሕይወት አላሳየም፡፡ ምንም አይነት ኃይልም አልገለጠም፡፡ እርሱ ለአባቱ ሙሉ በሙሉ ራሱን እንዳስረከበው ተከታዮቹም እንደዚያው ቢያደርጉ፣ የእርሱን ፍጹም ስብእና ሊቀዳጁ ይችላሉ፡፡ እቃገ 29.1

ያለ ማቋረጥ በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ እንደሚያስፈልጋቸው ያላስተዋሉ ሁሉ በፈተና ይሸነፋሉ፡፡ እግሮቻችን ጸንተው የቆሙና ምንም ሊያናውጠን እንደማይችል ሆኖ ሊሰማን ይችላል፡፡ በታላቅ መተማመን “ያመንሁትን አውቃለሁ” ብለን ልንናገር እንችላለን፡፡ ነገር ግን ሰይጣን በውልደት የወረስነውንና በልምምድ ያዳበርናቸውን ባህሪያት በመጠቀም የሚያስፈልገንን ነገር እንዳናይ ጉድለታችንንም እንዳናስተውል ሊያሳውረን ያቅዳል፡፡ ድካማችንን በማስተዋልና ዓይናችንን በኢየሱስ ላይ በማተኮር ብቻ ነው በደህንነት መራመድ የምንችለው:: እቃገ 29.2

የአብ ሀልዎት (መገኘት) ኢየሱስን ከብቦት የነበረ ሲሆን ወሰን የለሽ ፍቅሩ ለዓለም በረከትን ያመጣ ዘንድ ከሚፈቅደው ውጭ በእርሱ ላይ የመጣ አንዳች ነገር አልነበረም፡፡ ይህም ለእርሱ መጽናኛው ነበር፡፡ ለእናም እንደዚያው ነው፡፡ የክርስቶስ መንፈስ በውስጡ የሚኖር ሰው እርሱም በክርስቶስ ውስጥ ይኖራል፡፡ በእርሱ ላይ የሚያነጣጥር ነገር ሁሉ ዙሪያውን በከበበው ሰአዳኙም ላይ ያርፋል፡፡ በእርሱ ላይ የሚደርሰው ሁሉ የሚመጣው ከክርስቶስ ነው፡፡ በራሱ ብርታት ክፉን መቋቋም አያስፈልገውም፤ ክርስቶስ መከታው ነውና፡፡ በጌታችን ፈቃድ ካልሆነ በስተቀር አንዳች ነገር አይነካውም፡፡ እቃገ 30.1

ክርስቶስ የሞተላቸውን ነፍሳት ፈጽሞ አይተዋቸውም፡፡ እኛ እርሱን ልንተወው፣ ሰፈተናም ተስሰን ልንወሰድ እንችል ይሆናል፡፡ ክርስቶስ ግን የገዛ ህይወቱን ዋጋ አድርጎ ከከፈለላት ነፍስ ፊቱን ፈጽሞ አያዞርም፡፡ ባዶነቷን ተገንዝባ ሰአዳኙ መልካምነት ላይ የተደገፈች ነፍስ ስትታይ ምስኪን ብትመስልም፣ ሊቋቋማት የሚችል ማንም የለም፡፡ እንዲህ ያለችውን ነፍስ በምንም እንዳትሸነፍ ይረዷት ዘንድ እግዚአብሔር በሰማይ ያሉትን መላእክት ሁሉ ይልካል፡፡ እቃገ 30.2

ወደ አማኙ ዘንድ ማንኛውም መከራ ከመምጣቱ በፊት በሰማይ ያለው አባታችን መከራውን ይለካዋል፤ ይመዝነዋልም በእግዚአብሔር ፈተና ውስጥ የሚያልፈውን ሰው ጥንካሬና የፈታኝ ሁኔታዎችን ኃይል ሰማነጻጸር ይመዝናል፡፡ ከዚያም ለመቋቋም ከሚችለው አቅም በላይ የሆነውን ፈተና ወደዚያ ሰው እንዲደርስ ፈጽሞ አይፈቅድም፡፡ እቃገ 30.3

ክርስቶስ አማኞችን በውጊያው ሜዳ ብቻቸውን ፈጽሞ አይተዋቸውም፡፡ አማኙም የተስፋውን ቃል በእምነት በመያዝ ጠላትን በጌታ ስም ሌጋፈጥ ይገባል፡፡ እንዲህ ባለ ሁኔታሲመላለስ ውድቀት የሚባል ነገር ፍጹም አይነካውም፡፡ እቃገ 31.1

መንፈሳዊ ዓይናችን ቢበራልን ነፍሳት በብዙ ጫና ስር ሆነው መሪር ሃዘን አንብጧቸው ማየት በቻልን ነበር፡፡ ... እንዲሁም መላእክት እነዚህን በፈተና ውስጥ ያሉትን ለመርዳት የከበቧቸውን የክፉ ኀይላት ለመበተንና እግሮቻቸውን በጽኑ መሠረት ላይ ለማጽናት እየፈጠኑ ሲበሩ ማየት በቻልን ነበር። እቃገ 31.2