Go to full page →

የመወያያ ጥያቄዎች ክየመ 61

1. እውነተኛ የደቀ መዝሙርነት ፈተና ምንድን ነው? ዮሐ 14፡15 ን ይመልከቱ።
2. ከክርስቶስ ጋር ያለን ግንኙነት እያደገ በሄደ ቁጥር በህይወታችን ውስጥ አንዳንድ ባህሪያት ጎልተው መታየት ይጀምራሉ፡፡ ከነዚህ ባህሪያት ውስጥ ጥቂቶቹን ይጥቀሱ፡፡ ገላ 5:22-23 ን ይመልከቱ፡፡
3. የአንድ ሰው ባህርይ በአጋጣሚዎች ገሀድ የሚወጣ ሳይሆን ነገር ግን በህይወት ዝንባሌዎችና ልምምዶች የሚገለጽ ነው:: የህይወትዎ ዝንባሌና ልምምድዎት ስለ እርስዎ ባህርይ ምን ይገልጻል ?
4. «በክርስቶስ የተቆጠረልን ፅድቅ ብቸኛው የተስፋችን መሰረት ነው፤በእርሱም መንፈሱ በእኛ ውስጥና ከእኛ ጋር ይሰራል» የሚለውን አረፍተ ነገር ይወያዩበት። ክየመ 61.3