ሥጋ መመገብ የተወ ሰው ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑና ምግብን እንዲበላ የሚረዱ ፍረፍሬ፣ ጥራጥሬና ቅጠላቅጠል በሥጋ ፋንታ መመገብ አለበት፡፡ CLAmh 65.4
በተለይ ደካማ ለሆኑትና ብዙ አድካሚ ሥራ ለሚያከናውኑት ነገሩ በጣም አስፈላጊ ነው፡፤ አንዳንድ ድኅነት ባጠቃቸው አገሮች ዘንድ ሥጋ ከምግቡ ሁሉ በርካሽ ዋጋ ይገኛል፡፡ በዚህ ሁኔታ የምግብ ቅያሬ ማድረግ ቢያዳግትም እንደምንም ይቻላል፡፡ CLAmh 65.5
የሰዎችን ይዞታና በዕድሜ ሙሉ አብሮ ያደገን ልምድ በማየት ትክክለኛ አሳብ ቢኖረንም በአንድ ጊዜ ተቀባይነት እንዲያገኝ መታገል የለብንም፡፡ CLAmh 65.6
ድንገተኛ ለውጥ እንዲቀበል ማንንም መገፋፋት አያስፈልግም፡፡ CLAmh 65.7
በሥጋ ፋንታ ውድ ያልሆኑ ለጤና ተስማሚ የሆኑ የምግብ ዓይነቶች መመገብ ይቻላል፡፡ በዚህ በኩል የምግቡ ጠቃሚነት በአብሳይዋ ይወሰናል፡፡ በሚገባ ከተዘጋጁ የአትክልት ምግቦች ለሰውነት ጠቃሚና ለአፍም ጣፋጭ ናቸው፡፡ ስለዚህም የሥጋ ወኪል ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ CLAmh 66.1
በሕሊናችሁ ከተመራችሁ፤ ፈቃዳችሁን ካጠነከራችሁ መልካምና ለጤና ተስማሚ የሆኑ የምግብ ዓይነቶች ከተመገባችሁ ለውጥ ይመጣል፤ የሥጋ አምሮታችሁም ይጠፋል፡፡ CLAmh 66.2
ዘመኑ ሥጋን ከመመገብ ሁሉም የሚታቀብበት ጊዜ አይደለም እንዴ? ንጹሐን ለመሆን የሚሹ፤ ቅዱሳን የተለዩ ሆነው ከሰማይ መላእክት ጋር ለመጎዳኘት የሚፈልጉ እንዴት ለአካል፣ ለአእምሮና ለነፍስ ጉዳትን የሚያመጣ የምግብ ዓይነት እያወቁ ይመገባሉ? ሥጋቸውን በመብላት ለመደሰት እንዴት የእግዚአብሔርን ፍጥረት ይገድላሉ? CLAmh 66.3
በዚህ ፋንታ ሁሉም መመሪያ አምላክ ወደፈቀደለት ጤና ሰጭ የምግብ ዓይነት ይመለሳል፤ አምላክ ያስገዛልንን የማይናገሩ እንስሳት ከማሰቃየት ራሳቸው ተቆጥበው ልጆቻቸውንም ምሕረት ያስተምሩ፡፡ CLAmh 66.4