አእምሮና የፍቅር ስሜቶች መሰልጠን አለባቸው።--እግዚአብሔር የማገናዘብ ችሎታንና የአእምሮን የሚያስቡ ኃይሎች ሰጥቶናል፤ ነገር ግን እነዚህ ኃይሎች ትምህርትና ስልጠና ሳይሰጣቸው በራሳቸው መንገድ እንዲሄዱ ቢተዉ ሰውን በጨካኝ አህዛብ ሁኔታ ውስጥ ይተዉታል። አእምሮና የፍቅር ስሜቶች ከመምህራን ትምህርትና መመሪያ ያስፈልጋቸዋል። ሰብአዊው የግብረገብ ወኪል ከእግዚአብሔር ጋር ተባብሮ እንዲሰራ መምራትና ማስተማር መስመር በመስመር፣ ጥቅስ በጥቅስ መሆን አለበት። እግዚአብሔር በሰብአዊ ወኪል ውስጥ መስራት የሚችለው በራሱ የእውነት ብርሃን ነው።የእውነትን ብርሃን ያገኘ አእምሮ እውነትን ከስህተት ለይቶ ያያል።--Lt 135, 1898. {1MCP 350.1} 1MCPAmh 286.1
ከፍ ያለ የአእምሮ ስልጠና ከእግዚአብሔር ሙሉ ማረጋገጫ ያገኛል።--ሰብአዊ አእምሮ ከፍተኛ የሆነ ስልጠና የሚያስፈልገው ነው። ለእግዚአብሔር የተሰጠ ሕይወት የድንቁርና ሕይወት መሆን የለበትም። ኢየሱስ ወንጌሉን እንዲሰብኩ ያልተማሩ ዓሣ አጥማጆችን ስለመረጠ ብዙዎች ትምህርትን በመቃወም ይናገራሉ። ከተማሩት ይልቅ ያልተማሩትን ስለመምረጡ ማረጋገጫ ይሰጣሉ። የተማሩና የተከበሩ ብዙ ሰዎች በእርሱ ትምህርት አምነው ነበር። እነዚህ ሰዎች ህሊናቸው ያመነውን ነገር ሳይፈሩ ታዘው ቢሆን ኖሮ እርሱን ይከተሉት ነበር። ችሎታዎቻቸውን ለእርሱ ሰጥተው ቢሆን ኖሮ በክርስቶስ አገልግሎት ውስጥ ተቀባይነት አግኝተው ሥራ ላይ ይውሉ ነበር። ነገር ግን ኮስታራ በሆኑ ካህናትና ቀናተኛ በነበሩ ገዥዎች ፊት በክርስቶስ እንደሚያምኑ ለመናገርና ተራ ከሆኑ ገሊላውያን ጋር ግንኙነት በመፍጠር ክብራቸውን አደጋ ውስጥ ለመጣል የግብረገብ ኃይል አልነበራቸውም።. . . {1MCP 350.2} 1MCPAmh 286.2
ኢየሱስ ትምህርትን አልናቀም። ከፍተኛ የሆነ የአእምሮ ስልጠና፣ በእግዚአብሔር ፍቅርና ፍርሃት ከተቀደሰ፣ ከእርሱ ሙሉ ማረጋገጫ ያገኛል። ክርስቶስ የመረጣቸው ተራ ሰዎች የሰማይ ንጉስ በነበረው ተጽእኖ ሥር ሆነው ከክርስቶስ ጋር ለሶስት ዓመት አብረው ነበሩ። ክርስቶስ እስካሁን ዓለም ካወቃቸው ምሁራን ሁሉ ትልቁ መምህር ነበር። {1MCP 351.1} 1MCPAmh 286.3
ወጣቶች ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ቀድሰው የሚሰጡ ከሆነ እርሱ ከመክሊቶቻቸውና ከፍቅር ሀብታቸው ጋር ይቀበላቸዋል። የእውቀት ጫፍ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ፤ ይህ ከኃማኖታዊ መርህ ጋር ሚዛኑን ከጠበቀ ክርስቶስ ለማድረግ ከሰማይ የመጣበትን ሥራ ወደ ፊት እንዲቀጥል ማድረግ ይችላሉ፣ ይህን በማድረጋቸውም ከጌታ ጋር አብረው ሰራተኞች ይሆናሉ።--RH, June 21, 1877. (FE 47, 48.) {1MCP 351.2} 1MCPAmh 286.4
በሁለተኛ ደረጃ ሥራ አይረኩም።--እውነተኛ መምህር በሁለተኛ ደረጃ ሥራ አይረካም። ተማሪዎቹ ሊደርሱ ከሚችሉበት ከፍተኛ መስፈርት ዝቅ ወዳለ ቦታ በመምራት አይረካም። የሙያ እውቀት ብቻ በመስጠት፣ የተዋጣላቸው የሂሳብ አያያዝና የዕደ ጥበብ ባለሙያዎች እና የተሳካላቸው ነጋዴዎች በማድረግ ብቻ ሊረካ አይችልም። በውስጣቸው ሕብረተሰብን ለማረጋጋትና ካሉበት ዝቅተኛ ኑሮ ከፍ ለማድረግ አዎንታዊ ኃይል እንዲሆኑ የሚያደርጉአቸውን የእውነት መርሆዎች፣ መታዘዝን፣ ክብርን፣ ታማኝነትን እና ንጽህናን በውስጣቸው እንዲፈጠር ማድረግ የእርሱ ፍላጎት ነው። ከሁሉም በላይ የሕይወት ታላቅ ትምህርት የሆነውን ከራስ ወዳድነት የጸዳ አገልግሎት እንዲማሩ ይፈልጋል። --Ed 29, 30 (1903). {1MCP 351.3} 1MCPAmh 287.1
አእምሮን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለመውሰድ።--የተማሪዎቻችንን አእምሮ፣ አሁን ሊደርስ የሚችለው እስከዚህ ድረስ ነው ተብሎ ከሚታሰብበት አልፎ ከፍ ወዳለ ደረጃ እንድንወስድ መመሪያ ተሰጥቶኛል። ልብና አእምሮ ለየዕለቱ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ከዘላለማዊ እውነት ምንጭ በመቀበል ንጽህናቸውን እንዲጠብቁ መሰልጠን አለባቸው። በዘመናት ሁሉ መለኮታዊ አእምሮና እጅ የፍጥረትን መዝገብ በንጽህናው ጠብቀውታል። ስለ ዓለማችን አፈጠጣር እውነተኛ የሆነ መረጃ የሚሰጠን የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው። ይህ ቃል በትምህርት ቤቶቻችን ዋና ጥናት መሆን አለበት። በዚህ ቦታ ከአባቶችና ከነቢያት ጋር ልንነጋገር እንችላለን፤ በዚህ ቦታ የእኛ መቤዠት፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ከአብ ጋር እኩል የሆነውንና ሕዝቦች ከእያንዳንዱ ተራ እና ምድራዊ ነገር ድነውና በእግዚአብሔር አምሳል ታድሰው በፊቱ መቆም እንዲችሉ፣ ያስከፈለውን ዋጋ መማር ይችላሉ።--Lt 64, 1909. {1MCP 351.4} 1MCPAmh 287.2
እውነተኛ ትምህርት የአእምሮና የግብረገብ እውቀትን ያጣምራል።--መምህራኖቻችን እርሱ በሰጣቸው ብርሃን እንዲሄዱ እግዚአብሔር ሲጠብቃቸው ነበር። ክርስቶስ የእግዚአብሔርን የግብረገብ ምስል እንዲመልስ ራስን ዝቅ የማድረግ አስፈላጊነት አለ። የሚሰጠው ትምህርት ለተቋሞቻችን ትክክለኛ ቅርጽ ከመስጠቱ በፊት የሚሰጠው ትምህርት ባህርይ መለወጥ አለበት። ትምህርትን ከሚፈለገው ግብ ለማድረስ ወደ እግዚአብሔር ቃል መስፈርት መድረስ የሚቻለው የአእምሮና የግብረገብ ኃይሎች ሲዋሃዱ ብቻ ነው።-- RH, Sept 3. 1908. (FE 527.) {1MCP 352.1} 1MCPAmh 287.3
እውነተኛ ኃይማኖተኛነት ከፍ ያደርጋል፣ ይሞርዳልም።--በሁሉም ቦታ ያለው ሕዝባችን አእምሮአቸው ዝቅ እንዲልና ጠባብ እይታ እንዲኖረው ይፈቅዳሉ። የክርስቶስ እቅድና መንፈስ እንዲመራቸው ከመፍቀድ ይልቅ የዓለማዊ ወኪሎች እቅዶች እንዲመሩአቸውና ዓለማዊ መንፈስ እንዲቀርጻቸው ይፈቅዳሉ። ለሕዝባችን ከምድራዊው ይልቅ ሰማያዊውን ተመልከቱ ብዬ እንድነግራቸው መመሪያ ተሰጥቶኛል። ቁጥር የስኬት ማረጋገጫ አይደለም፤ ቢሆን ኖሮ ሰይጣን የበለጠ ስኬት እንዳለው መናገር ይችል ነበር። የስኬት ማረጋገጫ መሆን የሚችለው በተቋሞቻችን፣ በትምህርት ቤቶቻችን እና በቤተ ክርስቲያኖቻችን ውስጥ የሞራል ኃይል ተስፋፍቶ የሚገኝበት ደረጃ ነው። ክርስቶስን በሚመስል ጠባይ ክርስቶስን መወከል ከትንሽ እስከ ትልቅ ድረስ የሁሉም ደስታ መሆን አለበት። እውነተኛ ኃይማኖተኛነትና እግዚአብሔርን በመታዘዝ የሚታይ ፍቅር ከፍ እንደሚያደርግና እንደሚሞርድ መምህራኖቻችን ሁሉ ይማሩ።--Lt 316, 1908. {1MCP 352.2} 1MCPAmh 287.4
ጥብቅነት አስፈላጊ ነው።--በባህርይ ግንባታ ሥራ ስኬት ለማግኘት ጥብቅነት አስፈላጊ ነው። የግንበኞች አለቃን ዕቅዶች ለመፈጸም ልባዊ የሆነ ፍላጎት መኖር አለበት። ጥቅም ላይ የሚውሉ ጣውላዎች ጠንካራ መሆን አለባቸው፤ ግድ የለሽነት ያለበትና ተአማኒነት የሌለው ሥራ ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም፤ ሕንጻውን ያበላሻል። በዚህ ሥራ ውስጥ መላው አካል መግባት አለበት። ሥራው ጥንካሬንና ጉልበትን ይሻል፤ በማያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ የሚባክን መጠባበቂያ የለም። ከመለኮታዊ ሰራተኛ ጋር በመተባበር በዚህ ሥራ ውስጥ መሰማራት ያለበት ቁርጠኛ ሰብአዊ ኃይል ያስፈልጋል። ከዓለም ወጎች፣ አባባሎችና ሕብረቶች ለመለየት ልባዊ የሆነና ትጋት ያለበት ሰብአዊ ጥረት መኖር አለበት። ጥልቅ የሆነ አስተሳሰብ፣ የዓላማ ጽናት፣ የማያወላውል ታማኝነት አስፈላጊ ናቸው። ሥራ ፈትነት መኖር የለበትም። ሕይወት ቅዱስ ሀላፊነት ስለሆነ እያንዳንዷ ደቂቃ በጥበብ መሻሻል አለባት።--YI, Feb 19, 1903. (HC 84.) {1MCP 352.3} 1MCPAmh 288.1
የማይረቡ ነገሮች አእምሮን ያደክማሉ።--በእግዚአብሔር ቃል ሰፊ መርሆዎች ፈንታ ተራ የሆኑ ሀሳቦችን የሚቀበልና ጊዜና ትኩረት ተራ በሆኑ፣ የማይረቡ ነገሮች ላይ እንዲያዝ የሚፈቅድ ተማሪ አእምሮው ቀጭጮና ደካማ ሆኖ ያገኘዋል፤ የእድገት ኃይልን ያጣል። አእምሮ ዘላለማዊ ሕይወትን የሚመለከቱ አስፈላጊ እውነቶችን እንዲረዳ መሰልጠን አለበት። --Lt 64, 1909. {1MCP 353.1} 1MCPAmh 288.2
ዓለማዊ (ምድራዊ) ጉዳዮች ችላ መባል የለባቸውም።--ሕይወት በዓለማዊና ምድራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲወሰድ ለማድረግ፣ ከዘላለማዊ ፍላጎት ጋር ግንኙነት ካላቸው ነገሮች ጋር ሲነጻጸር ኢምንት ለሆኑ ነገሮች በመጨነቅና በመስጋት አሰልቺ የሆነ ዕለታዊ ተግባርን ለማከናወን፣ ዝም ማለት እስከማንችል ድረስ እጅግ ክቡር ነው። ነገር ግን እግዚአብሔር በሕይወት ዓለማዊ ጉዳዮች ውስጥ እንድናገለግል ጠርቶናል። በዚህ ሥራ ውስጥ ትጋት እንደ አምልኮ ሁሉ የእውነተኛ ኃይማኖት አካል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ለሥራ ፈትነት ፈቃድ አይሰጥም። ይህ ዓለማችንን እያሰቃየ ያለ ታላቁ እርግማን ነው። በእውነት የተለወጠ እያንዳንዱ ወንድና ሴት ትጉህ ሰራተኛ ይሆናል። --COL 343 (1900). {1MCP 353.2} 1MCPAmh 288.3
ለማስተማር የተጠሩ ሰዎች ጥራት። [ምዕራፍ 22 ‹‹ትምህርት ቤትና መምህር›› የሚለውን ይመልከቱ]።--የእግዚአብሔር ሥራ ከፍተኛ የሆነ የግብረገብ ብቃቶች ያሉአቸውን እና ሌሎችን ለማስተማር ሊታመኑ የሚችሉትን፣ በእምነታቸው ጤናማ የሆኑና ብልሃትና ትዕግስት ያላቸውን፣ ከእግዚአብሔር ጋር አብረው የሚጓዙና ክፉ ካለበት የማይገኙትን፣ የብርሃን መተላለፊያዎች መሆን እንዲችሉ ከእግዚአብሔር ጋር እጅግ የቀረበ ግንኙነት ያላቸውን--በአጭሩ የተቀቡ ክርስቲያኖችን ይሻል። እነዚህ የፈጠሩአቸው መልካም አሻራዎች በፍጹም ስለማይጠፉ በዚህ ሁኔታ የተሰጠ ስልጠና ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል። በዚህ የስልጠና ሂደት ችላ የተባለ ነገር ሳይሰራ ሊቀር ይችላል። ይህን ሥራ ለመስራት ቃል የሚገባው ማን ነው? {1MCP 353.3} 1MCPAmh 289.1
በእውነት ላይ ሥር የሰደዱና የተመሰረቱ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ሕያው ግንኙነት ያላቸው ጠንካራ ወጣቶች፣ አንጋፋ በሆኑ ወንድሞች ተመክረው ለትምህርትና ለምልከታ ሰፊ መስክ ወደሚያገኙባቸው በአገራችን ወዳሉት ከፍተኛ ኮሌጆች እንዲገቡ እንፈልጋለን። የተለያየ አመለካከት ካላቸው ክፍሎች ጋር ሕብረት መፍጠር፣ ታዋቂ ከሆኑ የትምህርት ዘዴዎች ጋር መተዋወቅ፣ እና መሪ በሆኑ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ትምህርት እንደሚሰጠው የስነ-መለኮት ትምህርት እውቀት ማግኘት እንደ እነዚህ ዓይነቶቹን ሰራተኞች ምሁር ለሆኑ ክፍሎች እንዲሰሩ በማዘጋጀትና በዘመናችን ገንነው የሚታዩትን ስህተቶች መጋፈጥ እንዲችሉ ለማዘጋጀት ትልቅ ዋጋ ይኖረዋል። የጥንቶቹ ዋልደንሶች የተከተሉት መንገድ የዚህ ዓይነት መንገድ ነበር፤ የእኛ ወጣቶች፣ እንደ እነርሱ ወጣቶች፣ ለእግዚአብሔር ታማኝ ቢሆኑ ኖሮ ገና በትምህርት ላይ እያሉ እንኳን የእውነትን ዘሮች በሌሎች አእምሮዎች ውስጥ በመዝራት ጥሩ ሥራ መስራት ይችሉ ነበር።--5T 583, 584 (1885). {1MCP 354.1} 1MCPAmh 289.2
ትክክለኛ ልማዶች በባሕርይ ላይ አሻራ ይተዋሉ።--ትክክለኛ የሆኑ ልምዶችን መመስረት ልጆች ትክክለኛ መንገድን እንዲለማመዱ በአእምሮና በባህርይ ላይ አሻራውን ይተዋል። እነዚህን ልጆች በእግዚአብሔር ምክርና ተግሳጽ በማሰልጠንና በመግራት በእግዚአብሔር መንፈስ ቀጥተኛ ተጽእኖ ሥር ማድረግ ትልቅ ነገር ነው። ትክክለኛ ልማዶችን መመስረት፣ ትክክለኛ የሆነ መንፈስን ማሳየት፣ በኢየሱስ ስምና ብርታት ልባዊ የሆነ ጥረት እንዲደረግ ይሻል። መምህሩ እነዚህን ልጆች በራሱ በተገለጸው በኢየሱስ ፍቅር ከልቡ ጋር በማስተሳሰር፣ መከራን በመቀበልና በትዕግስት፣ በርኅራኄና በፍቅር፣ መስመር በመስመር፣ ጥቅስ በጥቅስ፣ ጥቂት እዚህ ጥቂት እዚያ በመስጠት ሳይሰለች ማስተማር አለበት። --CEd 153 (1893). (FE 268.) {1MCP 354.2} 1MCPAmh 289.3
ባሕርይ በአንድ ቅርጽ አይመሰረትም።--መምህራን እየሰሩ ያሉት ከመላእክት ጋር ሳይሆን ልክ እንደ እነርሱ ሁሉ ስሜቶች ካሉአቸው ሰብአዊ ፍጡራን ጋር እንደሆነ መገንዘብ አለባቸው። ባሕርይ በአንድ ቅርጽ አይሰራም። ልጆች እንደ ውርስ የሚቀበሉት እያንዳንዱ የባሕርይ ክፍል አለ። በባሕርይ ውስጥ ያሉ ጉድለቶችና መልካም ባህርያት ይገለጣሉ። እያንዳንዱ መምህር ይህን ጉዳይ ከግምት ውስጥ ያስገባ። በውርስ የመጣውንና በሂደት ያደገውን የሰብአዊ ባሕርይ መጣመም፣ እንደ ባሕርይ ውበት ሁሉ፣ መጋፈጥ ያስፈልጋል፤ በስህተት ውስጥ ያሉት፣ ለአሁንና ለዘላለም እንዴት መልካም እንደሚሆንላቸው ለማወቅ በመምህሩ ውስጥ ብዙ ጸጋ ማደግ አለበት። ስሜት፣ ትዕግስት ማጣት፣ ኩራት፣ ራስ ወዳድነት፣ ለራስ ከፍተኛ ቦታ መስጠት፣ ከተንከባከቡአቸው ነፍስ ወደ ኋላ ማፈግፈግ የምትችልበት ጥበብ ሳይኖራት ወደ ሰይጣን የጦር ሜዳ በመወርወር ትልቅ ጉዳት ያደርሳል፤ ነገር ግን ጉዳት እስኪደርስበት ድረስ በሰይጣን ፈተናዎች ወዲህና ወዲያ የመላጋት አደጋ አለ። በራሱ ባልተቀደሱ ባሕርያት አማካይነት ሰይጣን ነፍሳትን ለማጥፋት እንደ ራሱ ወኪል አድርጎ እንዳይጠቀምበት እያንዳንዱ መምህር ነቅቶ የሚጠብቅበት የራሱ የሆኑ ልዩ ባሕርያት አሉት።--Lt 50, 1893. (FE 277, 278.) {1MCP 354.3} 1MCPAmh 290.1
ከአእምሮዎች ጋር ስንሰራ ክርስቶስን መምሰል አለብን።--ሥራ ላይ መዋል ያለበት ዕለታዊው የሥራ ወኪል፣ በፍቅር የሚሰራና የምሁሩን ነፍስ የሚያነጻ እምነት ነው። የተገለጠው የእግዚአብሔር ፈቃድ የአንተ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሆኖ ተቀምጦአልን? የክብር ተስፋ የሆነው ክርስቶስ በውስጥ ተመስርቶ ከሆነ የእርሱ ለዋጭ ወኪል በተለወጠ ባሕርይ እንዲገለጥ የእግዚአብሔር እውነት በተፈጥሮ ፀባይህ ላይ ይሰራል፣ ይህ ሲሆን ባልተቀደሰ ልብና ግልፍተኛ ፀባይ መገለጦች ተጽእኖ አማካይነት በተማሪዎችህ ፊት የእግዚአብሔርን እውነት ወደ ውሸት መለወጥ አትችልም፤ ከሰብአዊ አእምሮ ጋር በምትሰራበት ጊዜ ራስ ወዳድና ትዕግስት የለሽ የሆነ፣ ክርስቶስን የማይመስል ጠባይ በማሳየት የክርስቶስ ፀጋ ሁል ጊዜ እና በሁሉም ቦታ በቂ መሆኑን ማሳየት አትችልም። ስለዚህ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ያለው ሥልጣን ዝም ብሎ በስም ብቻ ሳይሆን በትክክልና በእውነት መሆኑን ታሳያለህ። ለእውነተኛ አማኝ ምንም ያህል ከባድ ቢሆን ከማይገባ ወይም ክርስቶስን ከማይመስል ነገር ሁሉ መለየት ያስፈልጋል። --CEd 148 (1893). (FE 263, 264.) {1MCP 355.1} 1MCPAmh 290.2
የማያቋርጥ ተግሳጽ ልጅን ግራ ያጋባል።--ሰማይ በልጅ ውስጥ የሚመለከተው ያላደገ ወንድንና ሴትን፣ በሰማያዊ ጥበብ በትክክል ቢመራና ቢያድግ ኖሮ ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ ሰራተኛ እንዲሆን መለኮታዊ ተጽእኖዎች በእርሱ አማካይነት መተባባር የሚችሉበት ሰብአዊ ወኪል እንደሚሆን ነው። የተሳሉ ቃላትና የማያቋርጥ ተግሳጽ ልጅን ግራ ከማጋባት በቀር በፍጹም አያድሱትም። ያንን ትዕግስት የለሽ ቃል አትናገር፤ የራስህን መንፈስ በኢየሱስ ክርስቶስ እርምት ሥር አድርግ፤ ያኔ በአንተ ተጽእኖ ሥር ለሆኑት እንዴት እንደምታዝንና ርኅራኄ እንደምታሳይ ትማራለህ። ትዕግስት የለሽነትንና ጭካኔን አታሳይ፣ እነዚህ ልጆች መማር ባያስፈልጋቸው ኖሮ የትምህርት ቤት ጥቅሞችንም አይፈልጉም ነበር። እውቀትን ለማግኘት በእድገት መሰላል ላይ ደረጃ በደረጃ እንዲወጡ በትዕግስት፣ በደግነትና በፍቅር ማደግ አለባቸው።--CEd 147 (1893). (FE 263.) {1MCP 356.1} 1MCPAmh 291.1
ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት በማገድ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ።--ተማሪዎችን ከትምህርት ቤት በማገድ መስመር ስለምታደርጉት ነገር ጥንቃቄ አድርጉ። ይህ ከባድ ጉዳይ ነው። የዚህ ዓይነት እርምት የሚያስፈልገው እጅግ ከባድ ስህተት መሆን አለበት። {1MCP 356.2} 1MCPAmh 291.2
ከጉዳዩ ጋር የተገናኙትን ሁኔታዎች ሁሉ በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል። ከቤታቸው አጭር ርቀት ወይም ረዥም ርቀት፣ በሺሆች የሚቆጠሩ ማይሎችን፣ ርቀው ያሉ ተማሪዎች ከቤት የሚያገኙአቸውን ጥቅሞች ያጡ ሲሆን ከትምህርት ቤት ሲባረሩ ደግሞ ከትምህርት ቤት ማግኘት ያለባቸውን ጥቅሞች እየተነፈጉ ናቸው። በእነዚህ ተማሪዎች ላይ የሚወጣው ወጪ ሁሉ የሚሸፈነው ገንዘባቸው በከንቱ እየወጣ እንዳልሆነ በተማሪዎቹ ላይ እምነትና ተስፋ ባላቸው ሰዎች ነው። ተማሪው ስህተት ውስጥ ሊገባ ወይም በፈተና ሊወድቅ ስለሚችል ለስህተቱ እርምት ያስፈልጋል። መረጃው እንደተበላሸበትና በትምህርት ሕይወቱ በሚያገኘው ሥልጠና ተጽእኖ ስለ እርሱ የወጣውን ወጪ ሁሉ መክፈል የሚችለውን መልካም ባሕርይ እንዲያጎለበት የተማመኑበትን ተስፋ እንዳስቆረጣቸው በትክክል ይሰማዋል። {1MCP 356.3} 1MCPAmh 291.3
ነገር ግን ከትምህርት ቤት የታገደው ከራሱ የሞኝነት እርምጃ የተነሣ ነው። ምን ያደርጋል? ድፍረት እጅግ ወርዶአል፣ ድፍረትና ቆራጥነት እየታየ አይደለም። ውድ ጊዜ ስለባከነ ለእርሱ ኪሳራ ነው። የእነዚህ ነፍሳት ሸክም የሚሰማው ገርና ደግ ሰው ማን ነው? ሰይጣን እነዚህን ሁኔታዎች እንደ መልካም አጋጣሚ መጠቀሙ ምን ያስደንቃል። ወደ ሰይጣን የጦር ሜዳ ስለተወረወሩ በሰብአዊ ልብ ውስጥ ያሉ እጅግ አስከፊ ስሜቶች ይንቀሳቀሱና ይጠናከራሉ፣ ይጸናሉም። --Lt 50, 1893. {1MCP 356.4} 1MCPAmh 291.4
የኢፍትሃዊነትን ስሜቶች ከመፍጠር ራቅ።--የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይማኖት በሌላቸው ግን እንዳላቸው በሚናገሩ ሰዎች ከሚታዩ ነገሮች ጋር ስትጋፋ ሳለ ክርስቲያን መሆንህን አትርሳ። ራስህን መቆጣጠር ሲያቅትህና ያለ አግባብ እንደያዝካቸው እንዲያስቡ ዕድል ስትሰጣቸው በከፍተኛ ደረጃ ተጽእኖህን ዝቅ ከማድረግህም በላይ የራስህን ክርስቲያናዊ ልምምድ ታበላሻለህ። ላለመፍጠር የሚቻልህ ከሆነ ይህን አሻራ በአእምሮአቸው አታስቀምጥ። በዚህ የአመክሮ ጊዜ ውስጥ ለወደፊቱ ዘላለማዊ ሕይወት ባሕርያችንን እየመሰረትን ነን፤ ነገር ግን ማድረግ ያለብን ይህን ብቻ ስላልሆነ በዚህ ባሕርይን የመገንባት ሂደት ውስጥ ሌሎች እኛ በሰጠናቸው ምሳሌ መሰረት ስለሚገነቡ እንዴት እንደምንገነባ በጣም ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። --Lt 20, 1892. (MM 209.) {1MCP 357.1} 1MCPAmh 292.1
አእምሮ ንጹህ ምግብ መመገብ አለበት።--አእምሮ ጤናና ብርታት እንዲኖረው እንደ አካል ሁሉ ንጹህ ምግብ መመገብ አለበት። ለልጆቻችሁ እንዲያስቡበት ከእነርሱ በላይና ውጭ የሆነ ነገር ስጡአቸው። በንጹህና ቅዱስ ከባቢ አየር ውስጥ የሚኖር አእምሮ ከንቱ፣ አስተሳሰቡ ትንሽ፣ የማይረባና ራስ ወዳድ አይሆንም።-Lt 27, 1890 {1MCP 357.2} 1MCPAmh 292.2
ውሸት የሆነና ጥልቀት የሌለው ነገር ሁሉ እርግጠኛ፣ ተፈጥሮአዊና ዘላቂ ከሆነው ነገር በላይ ከፍ ከፍ ባለበት ዘመን ውስጥ እንኖራለን። አእምሮ ወደ ስህት አቅጣጫ ከሚመራ ነገር ሁሉ ነጻ መሆን አለበት። ለአእምሮ ኃይሎች ብርታት በማይጨምሩ ውዳቂ ታሪኮች መጨናነቅ የለበትም። አስተሳሰቦች ለአእምሮ ከምንሰጠው ምግብ ጋር ተመሳሳይ ባሕርይ ይኖራቸዋል። --5T 544. (CG 188.) {1MCP 357.3} 1MCPAmh 292.3
የአረመኔነት መጻሕፍት። [ምዕራፍ 12 ላይ ‹‹የአእምሮ ምግብ›› የሚለውን ይመልከቱ]።--በአረመኔዎች የተጻፉ መጻሕፍትን ማጥናት ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል። በዚህ ሁኔታ በተማሪዎች አእምሮና ልብ እንክርዳዶች ይዘራሉ። ብዙዎች ማስተዋል ስለሚገባቸው ከዘላለማዊ ፍላጎቶች ጋር የተገናኙ ርዕሶች ስላላቸው መጻሕፍት ያላቸው እውቀት ትንሽ ሆኖ ሳለ ብዙ ጊዜ ለአእምሮ እየተሰጠ ያለው ምግብ ይህ ነው። {1MCP 357.4} 1MCPAmh 292.4
የጊዜ መክሊት ውድ ነው። እያንዳንዱ ቀን የተሰጠን በአደራ ስለሆነ ስለ እርሱ ለእግዚአብሔር መልስ እንድንሰጥ እንጠራለን። ጥቅም ላይ መዋል ያለበት ለእግዚአብሔር ክብር ሲሆን ዕድሜያችን እንዲረዝም ከፈለግን፣ ከእግዚአብሔር ሕይወት ጋር የሚለካ ሕይወት ማግኘት ከፈለግን፣ ለአእምሮ ንጹህ ምግብ መስጠት አለብን። ለመልካም ነገር ጥቅም ላይ መዋል የሚችል ጊዜ መባከን የለበትም።--MS 15, 1898. {1MCP 358.1} 1MCPAmh 292.5
ተማሪዎች እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ሊማሩ ነው።--በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ በመለኮታዊ ምሪት መሰራት ያለበት ትልቅ ነገር እንዳለ አያለሁ። ነገር ግን ተማሪዎች መማር ያለባቸው አንድ ትልቅ ትምህርት ቢኖር በሙሉ ልባቸው፣ አእምሮአቸውና ኃይላቸው እግዚአብሔርን ማወቅንና በግልጽ መታዘዝን ነው። የሰብአዊ ነፍስ ድነት ሳይንስ የሕይወት የመጀመሪያው ትምህርት ነው። በመጽሐፍ እውቀት ውስጥ ያለ ማንኛውም የሥነ-ጽሁፍ ዘርፍ ወይም ትምህርት የበላይነትን ቦታ መያዝ የለበትም። ነገር ግን እግዚአብሔርንና እርሱ የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ የዘላለም ሕይወት ነው። {1MCP 358.2} 1MCPAmh 293.1
ተማሪዎች እግዚአብሔርን መውደድንና መፍራትን ከእነርሱ ጋር ወደ ትምህርት ቤት ሕይወታቸው ይውሰዱ። ይህ ቃላት ከሚገልጹት በላይ እጅግ የከበረ ጥበብ ነው። ከእግዚአብሔር ጋር ከተገናኙ እግዚአብሔር ለዳንኤል ምስጢርንና እውቀትን ሁሉ እንዲያውቅ ጥበብ ሰጠው እንደተባለለት ሁሉ ለእነርሱም ይባልላቸዋል። {1MCP 358.3} 1MCPAmh 293.2
መማር ጥሩ ነው። የሰለሞን ጥበብ ይፈለጋል፤ ነገር ግን ከሰለሞን ጥበብ የሚበልጥ ጥበብ አብልጦ የሚፈለግና ጠቃሚ ነው። በትምህርት ቤቶቻችን በመማር ክርስቶስን ልንደርስበት አንችልም፤ ነገር ግን በሳይንስ ውስጥ ክርስቶስ የመሰላሉን ላይኛውን ጫፍ ሲደርስ እንችላለን። በእግዚአብሔር ምሪት የተጻፈ ቃል እንዲህ ይላል፡- ‹‹በእርሱ ፍጹማን ናችሁ›› (ቆላ. 2፡ 10)። የመጀመሪያው ጉዳያችን መሆን ያለበት እግዚአብሔርን ማየትና መቀበል ሲሆን ያኔ እርሱ መንገዳችንን ይመራል።--Lt 120, 1896. {1MCP 358.4} 1MCPAmh 293.3