የሁሉም ጥናት መሰረት።--የእግዚአብሔር ቃል የሁሉም ጥናት መሰረት መሆን አለበት። እነዚህ የመገለጥ ቃላት በጥንቃቄ ከተጠኑ አእምሮንም ሆነ ልብን የሚስቡና የሚያጠናክሩ ናቸው። እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፈቃድ መገለጥ ማስተዋል እንድንችል አእምሮን በሥነ-ሥርዓት ማሳደግ አስፈላጊ ነው። ትዕዛዛቱን የሚታዘዙ ሰዎች ችላ ሊሉት አይችሉም። እግዚአብሔር የአእምሮ ኃይሎችን የሰጠን ርካሽና ከንቱ በሆኑ ነገሮች ላይ እንዲውሉ አይደለም። --MS 16, 1896. {1MCP 89.1} 1MCPAmh 73.1
የመርህ ጥንካሬ።--የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ተቀባይነት ሲያገኝ አእምሮንና ነፍስን ከፍ ከፍ ያደርጋል። የእግዚአብሔር ቃል መደነቅ የሚገባውን ያህል ተደንቆ ቢሆን ኖሮ ወጣቶችም ሆኑ አዛውንት በውስጣቸው ፈተናን መቋቋም የሚያስችላቸው ትክክለኛ የሆነ አስተሳሰብ፣ የመርህ ጥንካሬ ይኖራቸው ነበር። --MH 459 (1905). {1MCP 89.2} 1MCPAmh 73.2
ብቸኛው እውነተኛ መመሪያ።--ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር በደንብ መተዋወቅ ነገሮችን የመገንዘብ ኃይልን የሰላ እንዲሆን በማድረግ ነፍስ የሰይጣንን ጥቃት እንድትከላከል ምሽግ ይሆናታል። መጽሐፍ ቅዱስ ጠላትን የሚያሸንፍ የመንፈስ ሰይፍ ነው። በሁሉም የእምነትና የተግባር ጉዳዮች ላይ ብቸኛው እውነተኛ መመሪያ እርሱ ነው።ሰይጣን የብዙ ሰዎችን አእምሮና ልብ በከፍተኛ ሁኔታ እየተቆጣጠረ ያለበት ምክንያት የእግዚአብሔርን ቃል አማካሪያቸው ስላላደረጉና መንገዶቻቸው በሙሉ በእውነተኛ መፈተኛ ስላልተፈተኑ ነው። የክብር መንግስት ወራሾች ለመሆን መከተል ያለብንን መንገድ እንድንከተል መጽሐፍ ቅዱስ ያሳየናል። --RH Jan 4, 1881. (HC 31.) {1MCP 89.3} 1MCPAmh 73.3
ከፍተኛ ትምህርት ትርጉም ተሰጠው።--ለቀደምት ደቀ መዛሙርት ከተሰጠውና ለእኛ በእግዚአብሔር ቃል አማካይነት ከተገለጠው የበለጠ ሊገኝ የሚችል ትምህርት የለም። ከፍተኛ ትምህርት ማግኘት ማለት ይህን ቃል በውስጠ ታዋቂነት መከተል ማለት ነው፤ የክርስቶስን ዱካ እና መልካም ባሕርያት መከተል ማለት ነው። ራስ ወዳድነትን በመተው ሕይወትን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ቀድሶ መስጠት ማለት ነው።{1MCP 90.1} 1MCPAmh 73.4
ከፍተኛ ትምህርት ዝም ብሎ ከመጽሐፍት ከሚገኝ እውቀት የበለጠና መለኮታዊነት ጎልቶ የሚታይበትን ነገር ይጠይቃል። ይህ ማለት ስለ ክርስቶስ በግል፣ በተግባር ተሞክሮ የተረጋገጠ እውቀት ማግኘት ማለት ነው። ይህ ማለት በጨለማው ልዑል ትምህርት ቤት ከተገኙትና ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆንን ከሚቃወሙት ሀሳቦች፣ ልማዶችና ልምምዶች ነጻ መውጣት ማለት ነው። ከፍተኛ ትምህርት ማለት ትዕቢትን፣ ኩራትን፣ ራስ ወዳድነትን፣ ዓለማዊ ፍላጎትን እና አለማመንን ማሸነፍ ማለት ነው። ከኃጢአት ነጻ የመውጣት መልእክት ነው። --CT 11, 12 (1913). {1MCP 90.2} 1MCPAmh 73.5
አእምሮን ለመልካም ነገር ያነሳሳል።--በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ አእምሮ ጠለቅ ያለ ሀሳብን የሚጠይቁና ከፍ ያሉ ፍላጎቶችን የሚያነሳሱ ርዕሰ ጉዳዮችን ያገኛል። በዚህ ቦታ ከአበውና ከነቢያት ጋር ግንኙነት እንፈጥራለን፣ ዘላለማዊ የሆነው ለእነርሱ ሲናገር ድምፁን እንሰማለን። በዚህ ቦታ የሰማይ አምላክ ከጨለማ ኃይላት ጋር ብቻውን ለመጋፈጥና በእኛ ፋንታ ድል ለማድረግ፣ የእኛ ምትክና ዋስትና ለመሆን ራሱን ዝቅ አድርጎ እናያለን። እንደ እነዚህ ባሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ አክብሮት በተሞላ ሁኔታ ማሰላሰል ልብን ሳያለሰልስ፣ ሳያነጻ እና የከበረ ሳያደርግ፣ በአእምሮ ውስጥም አዲስ ጥንካሬንና ብርታትን ሳይፈጥር አይቀርም።---CT 52, 53 (1913). {1MCP 90.3} 1MCPAmh 74.1
የሕይወትን ዓላማ ይገልጣል።--ከሌሎች ጥቅሞች ሁሉ ይልቅ ለመጽሐፍ ቅዱስ የበለጠ ዋጋ እንድንሰጥ የሚያደርገን ነገር ቢኖር በእርሱ ውስጥ ለሰዎች የእግዚአብሔር ፈቃድ መገለጡ ነው። በዚህ ቃል ውሰጥ የመፈጠራችንን ዓላማና እንዴት ከዚህ ዓላማ ላይ መድረስ እንደምንችል እንማራለን። የአሁኑን ሕይወት እንዴት በጥበብ እንደምናሻሽልና የወደ ፊት ሕይወትን እንዴት ማግኘት እንደምንችል እንማራለን። ማንኛውም ዓይነት ሌላ መጽሐፍ የአእምሮ ጥያቄዎችን ወይም የልብ ጉጉትን ማርካት አይችልም። የእግዚአብሔርን ቃል እውቀት በማግኘትና ትኩረት በመስጠት ሰዎች እጅግ ዝቅ ካለው የውድቀት አዘቅት የእግዚአብሔር ልጆች ወደመሆንና ኃጢአት ከሌላቸው መላእክት ጋር ሕብረት ወደ መፍጠር ከፍታ ይነሳሉ።---CT 53, 54 (1913). {1MCP 90.4} 1MCPAmh 74.2
አእምሮን ለመንካትና ለማንቃት የተሰጡ ምሳሌዎች።--የእግዚአብሔር እቅድ አእምሮዎቻችን ቅዱስ በሆኑ ምሳሌዎች እንዲነኩ፣ እንዲነቁ፣ እና ትምህርት እንዲያገኙ ነው። ሳይንስን ከመጽሐፍ ቅዱስ ክርስትና ለማፋታት የሚደረጉ ጥረቶችን ተፈጥሮ ይቃወምለታል። እርሱ ስሜቶቻችንን የሚሳለሙ በተፈጥሮ ውስጥ ያሉ ነገሮች ትኩረታችንን በመሳብ ሰማያዊ እውነቶችን በአእምሮአችን ውስጥ እንዲቀርጹ ይፈልጋል። --YI, May 6, 1897. {1MCP 91.1} 1MCPAmh 74.3
መጽሐፍ ቅዱስ (ተወዳዳሪ)ተቀናቃኝ የሌለው መጽሐፍ።--እንደ ማስተማሪያ ኃይል መጽሐፍ ቅዱስ ተወዳዳሪ የለውም። በመገለጥ ውስጥ ያሉትን ግዙፍ እውነቶች እንዲገነዘቡ ተማሪዎችን ከመጠየቅ የበለጠ ለሁሉም የአካል ኃይሎች ብርታት የሚሰጥ ምንም ነገር የለም። አእምሮ ትኩረት እንዲያደርግባቸው በተፈቀደለት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ራሱን ቀስ በቀስ ያለማምዳል። ትልልቅና ከፍ ያሉ ነገሮችን ወደ ጎን በመተው ተራ በሆኑ ነገሮች ብቻ የሚያዝ ከሆነ ቀጫጫና ደካማ ይሆናል። ከባድ ከሆኑ ችግሮች ጋር በፍጹም እንዲታገል ካልተጠየቀ ወይም አስፈላጊ እውነቶችን እንዲገነዘብ ካልተገደደ፣ ከጊዜ በኋላ የእድገት ኃይል ያጣል።--5T 24 (1882). {1MCP 91.2} 1MCPAmh 75.1
በቀላል እምነት ተቀበል።--እግዚአብሔር ሰው የማገናዘብ ኃይሉን እንዲጠቀም የሚፈልግ ሲሆን ማንኛውም ሌላ ጥናት ከሚያደርገው የበለጠ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አእምሮን ያበረታል ከፍ ከፍም ያደርጋል። ለሰብአዊ አእምሮ ከሁሉ የተሻለ አእምሮኣዊና መንፈሳዊ እንቅስቃሴ ነው። ነገር ግን ለሰብአዊነት ድክመትና ጉድለት ተገዥ ከሆነውና ከሚመለክ ምክንያት ተጠንቀቁ። {1MCP 91.3} 1MCPAmh 75.2
ግልጽ የሆኑ እውነቶችን መረዳት እስከማንችል ድረስ ለአእምሮአችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንዳይጋረዱብን፣ ለመማር ተዘጋጅተንና የመንፈስ ቅዱስን እርዳታ እየጠየቅን የትንሽ ሕፃን ዓይነት ራስን ዝቅ ማድረግና እምነት ሊኖረን ይገባል። ስለ እግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ ስሜት ሲኖረንና የእርሱን ታላቅነት ለማስተዋል የእኛ አለመቻል ስሜት ሲሰማን ራሳችንን ዝቅ የማድረግን ስሜት ስለሚፈጥሩብን በእርሱ ፊት ስንገባ ቃሉን ቅዱስ በሆነ ፍርሃት መክፈት አለብን። ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ስንመጣ የእኛ የማሰብ ችሎታ ከእርሱ በላይ የሆነውን ባለሥልጣን መቀበልና ልብና የአእምሮ ችሎታ ለታላቁ ‹‹እኔ ነኝ›› መስገድ አለባቸው።--5T 703, 704 (1889). {1MCP 91.4} 1MCPAmh 75.3
የእግዚአብሔር ቃል በደመና እንዲሸፈን የሚያደርግ ምንም ነገር መጠናት የለበትም።--ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈሳዊ ማነጻጸሪያችን ነው። አብን ይገልጥልናል። የእግዚአብሔርን ቃል በተመለከተ በአእምሮአችን ውስጥ ጭጋግን ወይም ደመናን የሚያመጣ ምንም ነገር እንደ ምግብ መሰጠት የለበትም። የልብን አፈር መኮትኮትን በተመለከተ ምንም ዓይነት ግድ የለሽነት ወይም ትኩረት አለመስጠት መታየት የለበትም። ክርስቶስ ፍላጎትን ለመቀስቀስና ለመንፈሳዊ እውቀት ለሚራቡ ሁሉ የሕይወትን እንጀራ ለመስጠት ከሰማይ ስለመጣ አእምሮ የእርሱን ሥራና ቃላት ለማድነቅ መዘጋጀት አለበት። --MS 15, 1898. {1MCP 92.1} 1MCPAmh 75.4
ቅዱሳት መጻሕፍት ለሰው የሞራል ምርጫ እውቅና ይሰጣሉ።-- የእግዚአብሔርን ቃል በምንመረምርበት ጊዜ መላእክት በእነዚያ ቅዱስ ገጾች ላይ ብሩህ የሆኑ የብርሃን ጨረሮችን እያንጸባረቁ በጎናችን ናቸው። እነዚያ ጥቅሶች ሰው ትክክል በሆነውና ባልሆነው መካከል ለመምረጥ ኃይል እንዳለው በማሳየት ተማጽኖአቸውን ያቀርባሉ፤ በማስጠንቀቂያ፣ በተግሳጽ፣ በማግባባትና በማደፋፈር ይናገሩታል። አእምሮ ቅዱስ የሆኑ የእግዚአብሔርን ቃል እውነቶች መለማመድ አለበት፣ እንደዚህ ካልሆነ ደካማ ይሆናል።…ለራሳችን መመርመርና ጥቅስን ከጥቅስ ጋር በማወዳደር የእምነታችንን ምክንያቶች መማር አለብን። መጽሐፍ ቅዱሳችሁን ውሰዱና በጉልበታችሁ ተንበርክካችሁ እግዚአብሔር አእምሮአችሁን እንዲያበራ ጠይቁት።--RH, Mar 4, 1884. {1MCP 92.2} 1MCPAmh 76.1
አእምሮዎች እጅግ የተከበረውን እድገት ያገኛሉ።--መጽሐፍ ቅዱስ መጠናት እንደሚገባው ተጠንቶ ቢሆን ኖሮ ሰዎች በአእምሮ ችሎታዎቻቸው ጠንካራ ይሆኑ ነበር። በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተነበቡ ጉዳዮች፣ የቃሎቹ ቀላልና ክብር ያላቸው መሆን፣ ለአእምሮ የሚያቀርቡአቸው የከበሩ ርዕሰ ጉዳዮች፣ በሰው ውስጥ በሌላ መንገድ ሊያድጉ የማይችሉ የአእምሮ ኃይሎችን ያሳድጋሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለአእምሮ ገደብ የለሽ መስክ ተከፍቷል። ተማሪው ዝም ብሎ ሰብአዊ መነሻ ያላቸውን ማናቸውንም ሥራዎች በማንበብ ከማሳለፍ ይልቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ትልልቅ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በማሰላሰል፣ ከእርሱ የከበሩ ምስል ከሳች (ስዕላዊ) አነጋገሮች ጋር ሕብረት ቢፈጥር ኖሮ በሀሳብና በስሜት የበለጠውን ነጽቶና ከፍ ብሎ ይወጣ ነበር። {1MCP 92.3} 1MCPAmh 76.2
የወጣትነት አእምሮዎች ከፍተኛ የጥበብ ምንጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ችላ ሲሉ መድረስ ወደ ሚገባቸው የከበረ እድገት ደረጀ ሳይደርሱ ይቀራሉ። ዛሬ ጥሩ አእምሮ፣ የተረጋጋና ጠንካራ አቋም ያላቸው ጥቂት ሰዎች ያሉበት ምክንያት እግዚአብሔር ስላልተፈራ እና ስላልተወደደ፣ የኃይማኖት መርሆዎች በሕይወት ውስጥ መተግበር የሚገባቸውን ያህል ስላልተተገበሩ ነው። --CTBH 126, 1890. (FE 165.) {1MCP 93.1} 1MCPAmh 76.3
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተሰወረ ሀብትን ፈልጉ።--መጽሐፍ ቅዱስ የተሰጠን፣ ልክ እንዳለ ሲነበብ፣ መመሪያችን እንዲሆን ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አእምሮን ለማስፋትና የማሰብ ችሎታን ለማጠንከር ተሰልቶ የተዘጋጀ ሌላ ጥናት የለም። ሕያው የሆኑ ትዕዛዛት እንደሚያደርጉት ሌላ ማንኛውም ጥናት ነፍስን ከፍ ሊያደርግና ለአካል ኃይሎች ብርታትን ሊሰጥ አይችልም። በሺሆች የሚቆጠሩ የወንጌል አገልጋዮች አእምሮዎች የቀጨጩበት ምክንያት ተራ በሆኑ ነገሮች ላይ እንዲያርፉ በመደረጋቸውና በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያለውን የተደበቀ ሀብት መፈለግን ስላልተለማመዱ ነው። አእምሮ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ ማጥናት ሲመጣ የአእምሮ ማስተዋል ይሰፋና ከፍ ያሉ የአእምሮ ኃይሎች ከፍ ያለውንና የከበረውን እውነት ለመረዳት ያድጋሉ። {1MCP 93.2} 1MCPAmh 76.4
አእምሮ ሊቀጭጭ ወይም ሊሰፋ የሚችለው ብዙ ጊዜውን ከሚያሳልፍባቸው ነገሮች ባሕርይ አንጻር ነው። አእምሮ እውነትን ለመረዳት በመፈለግ፣ ጥቅስን ከጥቅስ ጋር በማነጻጸር፣ ጠንካራና የማያቋርጥ ጥረት ለማድረግ ካልተነሳሳ በቀር በእርግጠኝነት ይኮማተርና ኃይሉን ያጣል። አእምሮዎቻችንን ላይ ላዩን በማንበብ የማናገኛቸውን እውነቶች በመፈለግ ሥራ ላይ በቀጥታ እናሰማራቸው። --RH, Sept 28, 1897. {1MCP 93.3} 1MCPAmh 77.1
መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወትን በትክክል ይመራል።--መላው መጽሐፍ ቅዱስ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ክብር መገለጥ ነው። ከተቀበሉት፣ ካመኑበት፣ ከታዘዙት፣ ባሕርይን ለመለወጥ ከፍተኛ መሳሪያ ነው። አካልን፣ አእምሮንና መንፈሳዊ ኃይሎችን የሚያንቀሳቅስና ሕይወትን በትክክለኛ መስመር የሚመራ ትልቅ ማነሳሻና አስገዳጅ ኃይል ነው። {1MCP 93.4} 1MCPAmh 77.2
ወጣቶችም ሆኑ በእድሜ የበሰሉ ሰዎች በቀላሉ ወደ ፈተናና ኃጢአት እየተመሩ ያሉበት ምክንያት የእግዚአብሔርን ቃል ስለማያጠኑና በእርሱ ላይ በጥልቀት ማሰብ የሚገባቸውን ያህል ስለማያስቡ ነው። በሕይወትና በባሕርይ ላይ የሚታይ ጽኑና ቁርጠኛ የሆነ የፈቃድ ኃይል ማጣት የሚመጣው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ያለውን ቅዱስ መመሪያ ችላ ከማለት የተነሣ ነው። ልባዊ በሆነ ጥረት ንጹህና ቅዱስ ሀሳብን ወደሚፈጥር ነገር አእምሮአቸውን በመምራት ንጹህ ካልሆነውና ስህተት ከሆነው ነገር አእምሮአቸውን አይመልሱም። --MH 458 (1905). {1MCP 94.1} 1MCPAmh 77.3
ለተቀደሰ አኗኗር የሚያስፈልጉ ደንቦችን ይገልጣል።--እግዚአብሔር፣ በታላቅ ምህረቱ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ለተቀደሰ አኗኗር የሚሆኑ ደንቦቹን፣ ትዕዛዛቱንና ሕግጋቱን ገልጦልናል። መተው ያለብን ኃጢአቶች እንዳሉ ይነግረናል፤ የድነት እቅድን በማብራራት ወደ ሰማይ የሚመራውን መንገድ ያመላክተናል። ሰዎች ‹‹መጽሐፍትን እሹ›› የሚለውን የእርሱን ትዕዛዝ ቢታዘዙ ኖሮ እነዚህን ነገሮች የማያውቅ ማንም አይኖርም ነበር። {1MCP 94.2} 1MCPAmh 77.4
ነፍስ በመልካም ጠባይና በመለኮታዊ እውቀት የምታሳየው ትክክለኛ እድገት የድምር እቅድን የተከተለ ነው፤ ይህ ማለት ክርስቶስ ሁሉም ሊደርሱበት እንዲችሉ ለማድረግ ዘላለማዊ መስዋዕት በመሆን ያስገኛቸውን ጸጋዎች ያለማቋረጥ መደመር ማለት ነው። እኛ ውስን ነን፣ ነገር ግን ውስን ስላልሆነው ነገር ስሜት ሊኖረን ይገባል። {1MCP 94.3} 1MCPAmh 77.5
አእምሮ ስለ እግዚአብሔርና ለድነታችን ስላለው አስደናቂ እቅድ በማሰላሰል ሥራ መጠመድ አለበት። እንዲህ ሲሆን አእምሮ ተራ ከሆኑ ነገሮች ከፍ ይልና ዘላለማዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ያተኩራል። {1MCP 94.4} 1MCPAmh 78.1
በእግዚአብሔር ዓለም እና ሰውን በመልኩ እንደ ምሳሌው በፈጠረው በታላቁ የዩኒቨርስ ፈጣሪ ፊት መሆናችንን ማሰባችን አእምሮን ከማንኛውም ልበ-ወለድ ታሪክ ይልቅ ሰፊና ከፍ ባሉ መስኮች ላይ ለማሰላሰል ገጣሚ ያደርጋል። የእግዚአብሔር ዓይን እያየን መሆኑን ማወቃችን፣ እንደሚወደንና በአሳዛኝ ሁኔታ እንዳንጠፋ ሊያድነን ብሎ ለወደቀው ሰው የከበረውን አንድቀያ ልጁን መስጠቱን ማሰባችን ትልቅ ነገር ሲሆን እነዚህን ታላላቅ ርዕሰ ጉዳዮች ለመቀበልና በእነርሱ ላይ ለማሰላሰል ልቡን የሚከፍት ማንም ቢሆን በማይረቡና ስሜትን በሚያነሳሱ ነገሮች አይረካም።--RH, Nov 9, 1886. {1MCP 94.5} 1MCPAmh 78.2
አዲስ ልብ ማለት አዲስ አእምሮ ማለት ነው።--‹‹አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ›› የሚሉት ቃላት ትርጉም ‹‹አዲስ አእምሮ እሳጣችኋለሁ›› ማለት ነው። ሁል ጊዜ ይህን የልብ ለውጥ ተከትሎ የሚመጣው ለክርስቲያን ተግባር ጥርት ያለ አስተሳሰብና እውነትን መረዳት ነው። ለእውነት ያሉን አመለካከቶች መጥራት ለእግዚአብሔር ቃል ካለን መረዳት ጋር ተመጣጣኝ ነው። ለቅዱሳት መጻሕፍት የቀረበና በጸሎት የታጀበ ትኩረት የሚሰጥ ሰው ወደ እግዚአብሔር ከመመለሱ የተነሣ በአእምሮ ችሎታው ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደ ደረሰ ሰው ጥርት ያለ ግንዛቤና ትክክለኛ የሆነ ውሳኔ አሰጣጥ ይኖረዋል። -RH, Nov 10, 1904. {1MCP 95.1} 1MCPAmh 78.3
ያለ እቅድ (በዘፈቀደ) መነበብ የለበትም።--የቅዱሳት መጻሕፍትን ገጾች አልፎ አልፎ በማንበብ ብቻ ከእነርሱ መራቅ ከአደጋ የጸዳ አይደለም።…መለኮታዊ እውነትን ማስተዋል እንድትችሉ፣ በፊታችሁ ለተቀመጠው ከፍተኛ ሥራ ብቁ መሆን እንድትችሉ፣ ለአእምሮአችሁ ልጓም አድርጉና በጽኑ ፍላጎት አጥኑ። ይህን የሚያደርጉ ሰዎች አእምሮ ሊደርስበት የሚችለውን ነገር በማወቃቸው ይደነቃሉ።--YI, June 29, 1893. (HC 35.) {1MCP 95.2} 1MCPAmh 78.4
የማስታወስ ችሎታን ማሰልጠን አእምሮን ይረዳል።-- አእምሮ ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል፤ እንዲባዝን መፈቀድ የለበትም። በቅዱሳት መጻሕፍትና በከበሩና ከፍ ከፍ በሚያደርጉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንዲያርፍ መሰልጠን አለበት። ሰይጣን ፈተናዎቹን ይዞ ሲመጣ መድገም እንዲቻል የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፣ ጠቅላላ ምዕራፎችም ቢሆኑ፣ በአእምሮ መያዝ አለባቸው። የኢሳይያስ አምሳ ስምንተኛው ምዕራፍ ለዚህ ዓላማ ጠቃሚ ነው። ነፍስን በእግዚአብሔር መንፈስ መገለጥ በተሰጡ ገደቦችና መመሪያዎች እጠሩ። {1MCP 95.3} 1MCPAmh 78.5
ሰይጣን አእምሮን በምድራዊና ስሜታዊ ነገሮች ላይ እንዲያርፍ ሲመራ ‹‹ተጽፏል›› በሚል ቃል በተሳካ ሁኔታ መቋቋም ይቻላል።…እግዚአብሔር በእርግጥ እየመራው ያለ ሕዝብ ስለመሆናችን፣ በፈተናዎችና በችግሮች አማካይነት በታላቁ ቀን እንድንቆም እያዘጋጀን ስለመሆኑ የጥርጣሬ አስተያየት ሲያቀርብልን፣ ይህ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቅና የኢየሱስ ኃይማኖት ያለው የቅሬታ ሕዝብ ስለመሆኑ ከእግዚአብሔር ቃል ግልጽ የሆነ ማስረጃ በማቅረብ የእርሱን ክፉ አስተያየቶች ለመጋፈጥ ተዘጋጁ። --RH, Apr 8, 1884. {1MCP 95.4} 1MCPAmh 79.1
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሚዛናዊ የሆነ አእምሮን ይፈጥራል።--በመንፈስ ቅዱስ ስልጠና ሥር ያሉ ሰዎች ቃሉን በማስተዋል ማስተማር ይችላሉ። ለመንፈስ ምሪት ልባዊ የሆነ ተማጽኖን በማቅረብና ልብ በእውነት እንዲቀደስ ሙሉ በሙሉ አሳልፎ በመስጠት መጽሐፍ ቅዱስ የጥናት መጽሐፍ ተደርጎ ሲወሰድ ክርስቶስ ቃል የገባውን ነገር ሁሉ ይፈጽማል። {1MCP 95.5} 1MCPAmh 79.2
የዚህ ዓይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የአካል፣ የአእምሮና የሞራል ኃይሎች በተጣጣመ ሁኔታ እንዲያድጉ ስለሚያደርግ ውጤቱ ሚዛናዊ የሆነ አእምሮ ነው። በመንፈሳዊ እውቀት ሽባነት አይኖርም። ማስተዋል ይነቃቃል፣ የስሜት ክፍሎች ይነሳሳሉ፣ ህሊና ንቁ ይሆናል፣ ለነገሮች ያለው ድጋፍና አስተያየቶች ይነጻሉ፣ የተሻለ የሞራል አከባቢ ይፈጠራል፣ ፈተናን ለመቋቋም አዲስ ኃይል ይሰጣል። --SpTEd 27, June 12, 1896. (FE 433, 434.) {1MCP 96.1} 1MCPAmh 79.3
መርዘኛ ለሆኑ አስተያየቶች ማርከሻ።--በአእምሮ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ሲከማቹ፣ መርሆዎቹ በነፍስ ውስጥ ሥር ይሰዱና ምርጫችንና ፍላጎታችን ከእውነት ጋር ጋብቻ ስለሚፈጥሩ የሞራል ኃይሎችን ደካማ ለሚያደርግና እግዚአብሔር ለጠቃሚነት የሰጣቸውን የአካል ኃይሎች ለሚያዋርድና ለሚያበላሽ ቀስቃሽ ሥነ-ጽሁፍ ያለው ፍላጎት ይጠፋል። ቁጥጥር ባልተደረገበት ንባብ አማካይነት ለተወሰዱ መርዘኛ አስተያየቶች የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ትክክለኛ ማርከሻ ነው። --RH, Nov 9, 1886. (HC 202.) {1MCP 96.2} 1MCPAmh 79.4
ከጥንቆላ ይከላከላል።--የዚህ ቃል ትምህርት በሕይወታችን ውስጥ የሚቆጣጠረን ተጽእኖ ቢሆን ኖሮ፣ አእምሮና ልብ በእርሱ የመቆጣጠር ኃይል ሥር ቢሆኑ ኖሮ፣ ዛሬ በቤተ ክርስቲያናትና በቤተሰቦች ውስጥ ያሉት ክፋቶች ቦታ አያገኙም ነበር።…የቤት ሕይወት የእግዚአብሔርን ፀጋ ኃይል ያሳይ ዘንድ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርቶች አእምሮንና ልብን መቆጣጠር አለባቸው። . . . {1MCP 96.3} 1MCPAmh 80.1
ያለ መጽሐፍ ቅዱስ በውሸት መላምቶች ግራ እንጋባለን። አእምሮ ለጥንቆላና ለውሸት ጭካኔ ተገዥ ይሆናል። ነገር ግን የዓለምን አጀማመር የሚገልጽ ሥልጣን ያለው ታሪክ በእጃችን እያለ በሰብአዊ ግምት (ማስረጃ በሌላቸው አስተያየቶች) እና ተአማኒነት በሌላቸው መላምቶች ራሳችንን ማደናቀፍ የለብንም። --RH, Nov 10, 1904. {1MCP 96.4} 1MCPAmh 80.2
የማገናዘብ ኃይሎችን ያሻሽላል።--አእምሮ መረጃን ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናት ሥራ ላይ ከተሰማራ የማገናዘብ ኃይሎች ይሻሸላሉ። የቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት አእምሮን ያሰፋል፤ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ግንኙነት ከሌላቸውና ጥቅም ላይ ከሚውሉ መጻሕፍት አጠቃላይ እውቀትን ለማግኘት ከሚጠመድ አእምሮ የበለጠ ሚዛናዊ ይሆናል። የእግዚአብሔርን ቃል በማጥናት እንደሚገኝ እውቀት ጽኑ የሆነ፣ የማይለዋወጥና ዘለቄታ ያለው ሌላ እውቀት የለም። {1MCP 97.1} 1MCPAmh 80.3
መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ምንጭ ነው። አብዝታችሁ ስትመለከቱት እጅግ ጥልቅ ሆኖ ይታያል። የቅዱስ ታሪክ አስደናቂ እውነቶች አስገራሚ ብርታትና ውበት ያላቸው ሲሆን የዘላለምን ያህል ዘለቄታ ያላቸው ናቸው። የእግዚአብሔርን ባሕርይ ከሚገልጽ ሳይንስ ጋር እኩል የሚሆን ሳይንስ የለም። {1MCP 97.2} 1MCPAmh 80.4
ሙሴ የግብጻውያንን ጥበብ ሁሉ የተማረ ቢሆንም እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እነሆ እናንተ ገብታችሁ በምትወርሱአት ምድር ውስጥ እንዲህ ታደርጉ ዘንድ አምላኬ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ ሥርዓትንና ፍርድን አስተማርኋችሁ። ጠብቁአት አድርጉአትም፤ ይህቺን ሥርዓት ሁሉ ሰምተው በእውነት ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው በሚሉ በአህዛብ ፊት ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና›› --RH, Feb 25, 1896. (FE 393.) {1MCP 97.3} 1MCPAmh 80.5
ለአካል ኃይላት ብርታትን ይሰጣል።--ይህ መጽሐፍ፣ ይህ የከበረ ሀብት ከፍ ከፍ የማይደረገውና ዋጋ እንደሚሰጠው ወዳጅ የማይታየው ለምንድን ነው? ማዕበላማ በሆነው የህይወት ባሕር ላይ አቅጣጫ እንደሚያሳይ ካርታችን ነው። ወደ ዘላለም ቤታችን የሚወስደውን መንገድ እና በዚያ ቤት ውስጥ ለመኖር ሊኖረን የሚገባውን ባሕርይ ለማወቅ የምንመራበት መጽሐፍ ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አእምሮን ከፍ የሚያደርግና የሚያበረታ ሌላ የመጽሐፍ ዓይነት የለም። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አእምሮ ኃይሎቹን ሥራ ላይ ለማዋል እጅግ የከበሩ ርዕሰ ጉዳዮችን ያገኛል። መላ የአካል ክፍሎቻችንን አስደናቂ ከሆነው የራዕይ እውነቶች ጋር ከማገናኘት የበለጠ ብርታት የሚሰጥ ምንም ነገር የለም። እነዚህን ታላላቅ ሀሳቦች ለመጨበጥና ለመለካት የሚደረግ ጥረት አእምሮን ያሰፋል። የእውነትን ማዕድን አጥልቀን በመቆፈር ነፍስን የሚያበለጽጉ ውድ ሀብቶችን መሰብሰብ እንችላለን። በዚህ ቦታ ለመኖር እውነተኛ መንገድን፣ ለመሞት አስተማማኝ መንገድን መማር እንችላለን። --RH, Jan 4, 1881. (HC 31.) {1MCP 97.4} 1MCPAmh 80.6
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አእምሮን ያሰፋል (ያሳድጋል)።--መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ዘላለም ሕይወት በሚመራው መንገድ በደህና የሚመራን መሪያችን ነው። እግዚአብሔር የሚስበንን እና ተግባር ላይ ከዋለ ተቀባዩ እጅግ በጣም ከፍተኛ ትምህርት ከተማሩት ጋር ተወዳዳሪ የሆነ የሞራል ኃይል እንዲኖረው የሚያደርገውን እውነት የሚያቀርብልንን ነገር እንዲጽፉ ለሰዎች ገልጦላቸዋል። የእግዚአብሔርን ቃል የሚያጠኑ ሰዎች አእምሮዎች ሁሉ ይሰፋሉ። ከማንኛውም ትምህርት (ጥናት) የበለጠ የመገንዘብ ችሎታን ለመጨመርና እያንዳንዱን የአካል ክፍል በአዲስ ኃይል ለመሙላት የበለጠ ተጽእኖ አለው። አእምሮን ሰፊ ከሆኑና ከከበሩ የእውነት መርሆዎች ጋር እንዲገናኙ ያደርጋል። ሰማይ በሞላ ጥበብን፣ እውቀትንና ማስተዋልን በመስጠት ከሰብአዊ አእምሮዎች ጋር በቅርበት እንዲገናኝ ያደርጋል። --YI, Oct 13, 1898, (SD 70.) {1MCP 98.1} 1MCPAmh 81.1
መጽሐፍ ቅዱስ የያህዌ ራዕይ።--ይህ መጽሐፍ በዘመናት ሁሉ እንደ ያህዌ መገለጥ ሆኖ ይቆማል። መለኮታዊ ሕግጋት ለሰብአዊ ፍጡራን የተሰጡት የእግዚአብሔር ኃይል እንዲሆኑ ነው። የእግዚአብሔር ቃል እውነቶች ተራ የሰው አስተያየት አይደሉም፣ ነገር ግን ኃያሉ አምላክ የተናገራቸው ቃላቶች ናቸው። እነዚህን እውነቶች የሕይወቱ አካል የሚያደርግ ሰው በሁሉም መልኩ አዲስ ፍጥረት ይሆናል። አዳዲስ የአእምሮ ኃይሎች አይሰጡትም፣ ነገር ግን ካለማወቅና ከኃጢአት የተነሣ የመረዳት ችሎታን ጋርዶ የነበረው ጨለማ ይወገዳል። --RH, Nov 10, 1904. {1MCP 98.2} 1MCPAmh 81.2