Go to full page →

በመከራ ቀናት ውስጥ በጥልቀት ማሰላሰል Amh2SM 235

ጸሎትና ዘይት መቀባት - ነገር ግን ቅጽበታዊ ፈውስ አልነበረም

ቀኑ ግንቦት 21 ቀን 1892 ዓ.ም ነበር፡፡ ፈታኝ የነበረው እንቅልፍ የለሽ ሌሊት አልፏል፡፡ ትናንት ከሰዓት በኋላ በእኔ ጥያቄ ሽማግሌው ጂ ሲ ቴኒ እና ባለቤቱ፣ እንዲሁም ወንድም እስቶክተን እና እስሚዝ ጌታ እንዲፈውሰኝ ሊጸልዩልኝ ወደ ቤታችን መጡ፡፡ እጅግ ልባዊ የሆነ የጸሎት ጊዜ ስለነበረን ሁላችንም በጣም ተባረክን፡፡ ባልድንም ተሽሎኝ ነበር፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን ለመከተል በእኔ በኩል ማድረግ የምችለውን ሁሉ ስላደረግኩ ጌታ በራሱ መልካም ጊዜ እንደሚፈውሰኝ በማመን እሱ እንዲሰራ እጠብቃለሁ፡፡ እምነቴ «ጠይቁ ይሰጣችኋል» (ዮሐ. 16፡ 24) በሚለው ተስፋ ላይ ተመስርቷል፡፡ Amh2SM 235.1

ጌታ ጸሎታችንን እንደሰማ አምናለሁ፡፡ ወዲያውኑ ምርኮዬ ይመለስልኛል ብዬ ተስፋ አደረግኩ፣ ውስን በሆነው አመለካከቴ በዚህ ጌታ የሚከበር መሰለኝ፡፡ በጸሎት ወቅት እጅግ ተባርኬ ስለነበር «እኔ ፈዋሽህ ነኝ እፈውስህማለሁ» ተብሎ የተሰጠኝን ተስፋ አጥብቄ ያዝኩ፡፡ Manuscript 19, 1892. Amh2SM 235.2