ኤለን ኋይት ከሞተች ከአስርተ ዓመታት በኋላ የታተመው የተለያዩ ምክሮችን የያዘው ቅጽ (ቮሊዩም) ሲዘጋጅ ሳለ ሊመጣ ስላለው አስጨናቂ ክስተትና ወደ ክርስቶስ ዳግም ምፃት በምንቃረብበት ጊዜ ስለምትኖረው ቤተ ክርስቲያን ልምምድ የተወሰኑ ገጾች እንደሚሰጡ መጠበቅ አለበት፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ የተካተቱት ምክሮች በተለያዩ መጽሔቶቻችን ውስጥ እንደታዩት ሁሉ ከኤለን ጂ ኋይት አጫጭር ጽሁፎችና በማስታወሻ ደብተር ገጾች ውስጥ ከተጻፉት ነገሮች የተወሰዱ ናቸው፡፡ Amh2SM 366.1
እነዚህ ቀስቃሽ የሆኑ መልእክቶች ክፍተኛ የሆነ መደጋገም ስላለባቸው ይህ ነው የሚባል አስገራሚ የሆነ አዲስ ነገር አያቀርቡም፤ ነገር ግን ጌታውን በቅርቡ ለመገናኘት እየተጠባበቀ ባለ ሕዝብ ከፊታችን ካለው አስጨናቂ ሁኔታ ጋር ግንኙነት ያለው እያንዳንዱ አረፍተ ነገር በታላቅ ፍላጎት ይነበባል፡፡ Amh2SM 366.2
«ለጄኔራል ኮንፍረንስ የተሰጠ የመጨረሻ መልእክት” የሚለው የመደምደሚያ ምዕራፍ ሚስስ ኋይት ገና በሕይወት እያለች በ1913 ዓ.ም በተደረገው የጄኔራል ኮንፍረንስ ስብሰባ ላይ እንዲያነቡ አዘጋጅታ የላከችላቸውን ሁለት መደበኛ የሆኑ አረፍተ ነገሮችን ይወክላል፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱ ዓረፍተ ነገሮች የተወሰዱ ንባቦች በሌላ ቦታ በሕትመት መልክ ቀርበዋል፡፡ ሚስስ ኋይት በቤተክርስቲያን መሪዎች ላይ የነበራትን መታመንና የቤተክርስቲያንዋን የመጨረሻ አሸናፊነት በማመልከት የጻፈቻቸውን ሙሉ ዓረፍተ ነገሮች እዚህ ላይ ማካተት ተገቢ ይመስላል፡፡ Amh2SM 366.3
የኋይት ባለአደራዎች