Go to full page →

በእግዚአብሔር ምሪት የተሰጠን መልእክት አሳማኝ መረጃ ያጅበዋል Amh2SM 71

ጌታ ለሰው መልእክት ሲሰጥ መልእክቱ የሚሰጠው ከእሱ መሆኑን ሕዝቡ ከሚያውቁበት ከሆነ ነገር ጋር አብሮ ነው፡፡ ሕዝቡ መልእክት ይዞ ወደ እነሱ የሚመጣውን ሁሉ እንዲያምኑ እግዚአብሔር አይፈልግም፡፡ {2SM 71.2} Amh2SM 71.2

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ማስጠንቀቂያዎችን የሚልከው ሊያጠፋቸው ሳይሆን ስህተታቸውን ለማረም ነው፡፡... {2SM 71.3} Amh2SM 71.3

አደገኛ በሆነ ጊዜ ውስጥ እንኖራለን፡፡ ካለኝ ብርሃን በመነሳት ሰዎች ሊፈጽሙት ያለ አስደናቂ ሥራ እንዳላቸው እንዲያስቡ የሚያደርግ ነገር ለማምጣት ሰይጣን እየሞከረ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ለሰው መልእክት ሲሰጥ፣ ያ ሰው፣ በሚያሳየው የዋህነትና ትህትና፣ እግዚአብሔር በእሱ አማካይነት እየሰራ ለመሆኑ ማስረጃ ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔር ይኖራል ይነግሳልም፣ በፊቱ ራስን ዝቅ በማድረግ እንድንሄድ ይፈልግብናል፡፡ ይህ ኤን የተባለ ሰው በጉባኤ ፊት ራሱን በግድ እንዲያቀርብ አይፈልግም፡፡ ... {2SM 71.4} Amh2SM 71.4

የሚያስተላልፉት መልእክት እንዳላቸው በሚናገሩ ሰዎች ምክንያት በየጊዜው ስብሰባዎቻችን መደናቀፍ የለባቸውም፡፡ ባልተፈለገ ቦታ ራሱን በግድ የሚያስገባ ሰው የእግዚአብሔርን ሥራ እየሰራ አይደለም፡፡ በጦር ሰራዊት ውስጥ እንዳሉ ወታደሮች መሥራት አለብን፡፡ ከምድባችን ወጥተን በራሳችን መሥራት የለብንም፡፡ --Manuscript 30, 1901. {2SM 71.5} Amh2SM 71.5