ለተከተልከው መንገድ ማብራሪያ እንድትሰጠኝ አልጠይቅም፡፡ ወንድም [ሲ.ደብሊዩ.] ስቶን ደብዳቤህን ሊያነብልኝ ፈልጎ ነበር፡፡ ለመስማት እምቢ አልኩት፡፡ የጥርጣሬ፣ ብሶት የመናገርና ያለማመን ትንፋሽ ተላላፊ ነው፤ አእምሮዬን ቆሻሻ ምንጭ የሚፈስበት ቦይ ካደረግኩ፣ ከሰይጣን ምንጭ የሚወጣ የደፈረሰ በካይ ውኃ የሚፈስበት መተላለፊያ ካደረግኩ፣ አንዳንድ አስተያየቶች በአእምሮዬ ውስጥ በመቆየት ይበክሉታል፡፡ ብኩርናህን ለማይረባ ምግብ ማለትም ከጌታ ጠላቶች ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር እንድትሸጥ የመምራት ኃይል ካላቸው ከጥርጣሬዎችህ መካከል አንዱንም መስማት አልፈልግም፣ ሌሎች አእምሮችንም እንዳትበክል እንደምትጠበቅ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አንተ የምትናገራቸውን አረፍተ ነገሮች ለመናገር የሚደፍርን ሰው የሚከበው ከባቢ አየር እንደ መርዘኛ የአየር ፀባይ ያለ ነው፡፡ {2SM 166.4} Amh2SM 166.4
እውነትን ከሚያምኑ ሰዎች ሙሉ በሙሉ እንድትርቅ እለምንሃለሁ፤ ዓለምንና የዓለምን ጓደኞች ከመረጥክ ከመረጥካቸው ጋር አብረህ ሂድ፡፡ የሌሎችን አእምሮ አትመርዝ፣ የነፍሳትን ጥፋት ለማምጣት ራስህን የሰይጣን ልዩ ወኪል አታድርግ፡፡ አቋምህን ሙሉ በሙሉ ካላስተካከልክ ለዘላለም ጊዜው ሳያልፍብህ ሰይጣንን ለመቋቋም ፍጠን፡፡ ወደ ጨለማ የሚመራ ሌላ እርምጃ አትውሰድ፣ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ሰው አቋምህን ያዝ፡፡ {2SM 166.5} Amh2SM 166.5
በምርጫህ ሳትሳሳት ወይም ውድቀትን ሳትፈራ የተከበረ ዓላማ ወይም ተግባር ማግኘት ከፈለግክ በእያንዳንዱ እቅድ፣ ሥራና ሀሳብ እግዚአብሔርን የመጀመሪያ፣ የመጨረሻና ከሁሉ የተሻለ ማድረግ አለብህ፡፡ ቀጥታ ወደ ጨለማ የሚመራውን መንገድ ከፈለግክ ማድረግ ያለብህ የእግዚአብሔርን ብርሃን ከኋላህ መጣልና ያለ እግዚአብሔር መኖር ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር መንገድህን እያሳየ «የደህንነትህና የሰላምህ መንገድ ይህ ነው» ሲል ፊትህን ከእግዚአብሔር መንገድ በተቃራኒ አቅጣጫ ስታደርግ እግርህ በሲኦል ይጸናል፡፡ የእግዚአብሔር በግ ድምፅ እንዲህ ብሎ ሲናገረን ተሰምቷል፣ «ተከተሉኝ፣ ከተከተላችሁኝ በጨለማ አትሄዱም፡፡” {2SM 167.1} Amh2SM 167.1