Go to full page →

የሚከፈለው በሰሩት መጠን ነው Amh2SM 181

የእግዚአብሔር መንገድ ቅንና እኩል ነው፡፡ በትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ ሰራተኞች መከፈል ያለባቸው ለትምህርት ቤቱ በታማኝነት ጠንክረው በሰሯቸው ሰዓታት ልክ ነው፡፡ ለማንኛውም ሰራተኛ ቢሆን ፍትህ መጓደል የለበትም፡፡ አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ለትምህርት ቤቱ ሙሉ ሰዓት ከሰራ/ች ትምህርት ቤቱ ሊከፍለው/ላት የሚገባው በተቀበለው አገልግሎት መጠን ነው፡፡ አንድ ሰው ያሉትን ሸክሞች ለመሸከም አእምሮውን፣ አቅሙንና ጉልበቱን ከሰጠ፣ ለትምህርት ቤቱ በሰጠው ጥቅም መሰረት መከፈል አለበት፡፡ ለትምህርት ቤቱ ለአሁንና ለወደፊት አቋም ብቻ ሳይሆን በጽድቅ ለሆነው ለራሳችን የግል ጥቅም አንጻር ፍትህና እውነት መጠበቅ አለበት፡፡ በጣም ትንሽ በሆነ ኢፍትሃዊነት ውስጥ እንኳን ቢሆን እግዚአብሔር ድርሻ የለውም፡፡--Manuscript 69, 1898. Amh2SM 181.4