Go to full page →

ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች እና ምቾት Amh2SM 187

ነፍሳትን ለማዳን ሥራ ጊዜያቸውን ቀድሰው ለሚሰጡ ሰዎች በቂ ድጋፍ ለመስጠት በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት ውስጥ በቂ ገንዘብ መኖር አለበት፡፡ ፍትሃዊ ደሞዛቸው ሊነፈጋቸው አይገባም፡፡ ለጌታ ለመስራት ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ለኑሮ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ማጣት የለባቸውም፡፡ ተመችቷቸው እንዲኖሩ መደረግ አለባቸው፣ አብዛኛውን ጊዜ ስጦታ ሲሰጥ እነርሱ ግንባር ቀደም እንዲሆኑ ስለሚጠበቅባቸው ለእግዚአብሔር ሥራም መለገስ እንዲችሉ በቂ ገቢ ሊኖራቸው ይገባል፡፡--Manuscript 103, 1906. Amh2SM 187.2