Go to full page →

በድርጅቱ ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች የሚከፈል ደሞዝ Amh2SM 191

የህትመት ሥራ የተመሰረተው በመስዋዕትነት ነው፤ የተጠበቀውም ልዩ በሆነ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ የጀመርነው በታላቅ ድህነት ነበር፡፡ ለመብላትም ሆነ ለመልበስ የሚበቃ ነገር አልነበረንም፡፡ የድንች እጥረት ከመኖሩ የተነሳ ዋጋቸው ከፍተኛ በሆነባቸው ጊዜያቶች በእነርሱ ፋንታ ታርኒፕ የሚባል ሥራ ሥርን እንመገብ ነበር፡፡ በሥራ ላይ በነበርንበት የመጀመሪያ ዓመት የሳምንት ገቢያችን ስድስት ዶላር ብቻ ነበር፡፡ ትልቅ ቤተሰብ ነበረን፤ ነገር ግን ወጪዎቻችንን ከገቢያችን እንዳይበልጥ አደረግን፡፡ የፈለግነውን ሁሉ መግዛት አልቻልንም፤ ፍላጎቶቻችንን መገደብ ነበረብን፡፡ ነገር ግን ዓለም የወቅቱን እውነት ብርሃን እንዲያገኝ ለማድረግ ወስነን ስለነበር መንፈስ፣ ነፍስና አካል ከሥራው ጋር ተጠላልፈው ነበር፡፡ ያለ እረፍት፣ ያለ አንዳች የደሞዝ ማበረታቻ አስቀድመን ወደ ሥራ በመግባትና አርፍደን በመውጣት ሰራን፡፡… እግዚአብሔርም ከእኛ ጋር ነበር፡፡ የሕትመት ሥራን ብልጽግና ሲከተለው መሆን እንደሚገባው የደሞዝ ጭማሪ ተደረገ፡፡ Amh2SM 191.2