Go to full page →

በሳላማንካ የተሰጠ ማስጠንቀቂያ Amh2SM 193

በህዳር ወር 1890 ዓ.ም በኒው ዮርክ በነበረው ሳላማንካ ሳለሁ ብዙ ነገሮች ቀርበውልኝ ነበር፡፡ በቢሮ ውስጥ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት የሌለው መንፈስ እየመጣ እንደሆነ እንዳይ ተደርጌ ነበር፡፡ አንዳንዶች ከፍተኛ የሆነ ደሞዝ ሲከፈላቸው፣ ሌሎች በተሰጣቸው ቦታ ለዓመታት በታማኝነት ሲሰሩ የኖሩት እጅግ በጣም አነስተኛ የሆነ ደሞዝ የሚቀበሉ አሉ፡፡ የእግዚአብሔር ትዕዛዝ መጣስ እንደሌለበትና ሚስዮናዊ መንፈስ መጥፋት እንደሌለበት በተደጋጋሚ እንዳይ ተደርጌያለሁ፡፡. . . . Amh2SM 193.3

ለእግዚአብሔር ሥራ አስራታቸውን ለመክፈልና ስጦታዎቻቸውን ለመስጠት ከፍተኛ የሆነ ራስን የመካድ ሥራ የሚለማመዱ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ በሥራው ውስጥ በመሪነት ላይ ያሉ ሰዎች ሳያፍሩ «በመሰዋዕትነት ተጀምሮ ቀጣይነት ባለው ራስን በመካድ ተግባር እየተደገፈ ባለው ሥራ ውስጥ በጋራ ለመስራት ኑ” ማለት የሚያስችላቸውን መንገድ መከተል አለባቸው፡፡ ቁጠባን በመለማመድና ፍላጎቶቻቸውን በመቆጣጠር ረገድ በተቋሞቻችን ውስጥ በመሪነት ቦታ የተቀመጡት ሰዎች በሕዝብ መበለጥ የለባቸውም፡፡--Manuscript 25a, 1891. Amh2SM 194.1