Go to full page →

ለሥራው የሚደረግ ዝግጅት ChSAmh 196

የየሱስ ተከታዮች በዝቅተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ዕውቀት መመላለሳቸው ደስታ የሚሰጣቸው ከሆነ እርሱ እንደ ግብ ካስቀመጠው አምላካዊ አስተሳሰብና ፈቃድ ላይ መድረስ አይችሉም፡፡ ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ሊሆኑ ይገባል፡፡ “በእነርሱ የዘላለም ሕይወት የምታገኙ እየመሰላችሁ መጻሕፍትን ትመረምራላችሁ፤ እነዚሁ መጻሕፍት ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው”፡፡ ጴጥሮስ እንዲህ ሲል ያደፋፍረናል “hርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት፡፡ እናንተ ስላላችሁ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትህትናና በአክብሮት አድርጉ፡ ፡”- Testimonies, vol. 2, pp. 633 634. ChSAmh 196.1

በእውነት የተለወጡ ሁሉ የብርሐን ቃላት የሚናገር፣ በጨለማ ለሚኖሩና በኃጢአታቸው እየጠፉ ላሉ ደኅንነት የሚያመጣ--በአምላካዊው ቃል ላይ እያደı የሚሄድ በሳል ዕውቀትና ማስተዋል ይኖራቸዋል፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 121. ChSAmh 196.2

የመጨረሻውን ማስጠንቀቂያ ለሰዎች የምንሰጥበት ጊዜ ላይ የምንገኝ እኛ የእግዚአብሔር ሕዝቦች መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናት ትጋታችንና ብርሃንን የማስተላለፍ ቅንአታችን እንዴት ሊሆን ይገባል! መለኮታዊውን ብርሃን የተቀበለ እያንዳንዱ ነፍስ ለሌሎች የማጋራት ምኞት ይደርበት፡፡ የወንጌል ሠራተኞች የቤት ለቤት ጉብኝት እያደረጉ፣ አምላካዊውን ቃል ለሕዝቦች እየከፈቱና በራሪ ጽሑፎችን እያደሉየገዛ ነፍሳቸውን የባረከውን እውነት ለሌሎች ይንገሩ፡፡-Gospel Workers, p. 353. ChSAmh 196.3

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጠና የሚሰጡ ሠራተኞች በመልካም እንቅስቃሴ ላይ ሲገኙ ሚዛኑን የጠበቀ አገልግሎት መስጠት ይቻላል፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጠና ከሚሰጡ አካላት ወይም ከከተማው የወንጌል ስርጭት ዘርፍ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ጉባዔ ሲካሄድ ሠራተኞች ለመጽሐፍ ቅዱስ አገልጋዮች በየዕለቱ መመሪያ የሚሰጡና ከሚካሄደው ጉባዔ ጋር በሙሉ ልባቸው ሕብረት መፍጠር የሚችሉ፣ ጥልቅ መንፈሳዊ ማስተዋልና ተሞክሮ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡-- Testimonies, vol. 9, p. 11. ChSAmh 197.1