Go to full page →

የኅትመት ውጤቶችን በቅንነት ማሰራጨት ChSAmh 211

ለሕዝብ የሚያስፈልጉ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶችን የያዙ የኅትመት ውጤቶች--ማለትም ከመጻሕፍት፣ በራሪ ጽሑፎች፣ ጋዜጦችና መጽሔቶች ውጪ የአገልዩ ድምጽ ሊደመጥባቸው የማይችሉ አያሌ ስፍራዎች አሉ፡፡ የኅትመት ውጤቶቻችን በየትኛውም ስፍራ ሊሰራጩ ይገባል፡፡ ይህ ወይም ያየትኛው እንደሚያብብ የማናውቅ እንደመሆናችን የእውነት ዘር በቂ ውሃ ከሚገኝበት ስፍራ አጠገብ ሊዘራ ይገባል፡፡ እውነትን ለመቀበል በቂ ፍላጎትና ዝግጅት ያላቸው ለሚስሉ ነፍሳት የኅትመት ውጤቶቻችንን የመስጠቱ አላስፈላጊነት እምብዛም ላይታየን ይችላል፡፡ ይህ የተሳሳተው ሰብዓዊ ውሳኔ ነው፡፡ ወቅታዊውን እውነት የያዘውን በራሪ ጽሑፍ መስጠታችንን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን መልካም ውጤት ማወቅ አንችልም፡፡Southern Watchman, Jan. 5, 1904. ChSAmh 211.1