Go to full page →

የፈተናው ሂደት ChSAmh 266

እግዚአብሔር የተለመደውን የዕለት ከዕለት ሕይወታችንን አካሄድ ተከትሎ በመፈተን እውነተኛውን ማንነታችንን ያረጋግጣል፡፡ እጅግ ትናንሽ የሆኑት ነገሮች በልብ ጓዳ ውስጥ ያሉትን ነገሮች ይገልጻሉ፡፡ አነስተኛም እንኳ ቢሆን ለሰዎች የምንሰጠው ትኩረት፣ በተደጋጋሚ የምናሳያቸው መልካም ምግባሮችና ጥቂት እርዳታዎች አጠቃላይ ድምር በሕይወት ውስጥ ያለውን ደስታ ይገልጻል፡፡ በተቃራኒው ደግነትን፣ ማበረታታትን፣ በፍቅር የተሞሉ ቃላትንና እጅግ አነስተኛውን በጎ ተግባር ከማድረግ ችላ የማለት ድምርሕይወት በሥቃይና በሐዘን የተሞላ መሆኑን ያሳያል፡፡ በዙሪያችን ለሚገኙ ነፍሳት ደስታና በጎ ስንል ራሳችንን በመካድ የምንከፍለው መሥዋዕትነት በሰማይ መዝገብ ከፍ ያለውን ስፍራ እንደሚይዝ በስተመጨረሻ ይታወቃል፡፡Testimonies, vol. 2, p. 133. ChSAmh 266.1

አምላካዊውን ጣልቃ ገብነት ተከትሎ መበለቶች፣ ወላጅ ዐልባ ህጻናት፣ አካል ጉዳተኞችና በተለያየ መንገድ ሥቃይና ሐዘን የደረሰባቸው ወገኖች በመልካም ክርስቲያናዊ ዝምድና ከቤተ ክርስቲያኑ ጋር በቅርበት እንዲመላለሱ መደረጉን ጌታ አሳይቶኛል፡፡ ይህ ተግባር የሕዝቡን እውነተኝነት በማረጋገጥ እውነተኛውን ጸባይ እንዲያጎለብቱ ይረዳል፡፡ የእግዚአብሔር መላእhት የእኛን የድጋፍ ስሜት፣ ፍቅርና ሚዛናዊ አመለካከት ለሚሹ ወገኖች ምን ዓይነት ምላሽ እየሰጠን እንደሆነ እየተመለከቱ ነው፡፡ ይህ እግዚአብሔር ጸባያችንን የሚፈትንበት መንገድ ነው፡፡ የእውነተኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ኃይማኖት ባለቤቶች ከሆንን ክርስቶስ ስለ ወንድሞች የሰጠው ፍቅርና በጎነት ባለ ዕዳዎች መሆናችን ይሰማናል፡፡ እኛ ከምንገኝበት እጅግ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ወንድሞች ያለንን ጥልቅ ፍላጎት ስናሳይና ራስ ወዳድ ያልሆነውን ፍቅር ስንገልጽ—ጢአተኞችና ጸጋው የማይገባን ሆነን ሳለ ለእኛ ላሳየን በማንኛውም መስፈርት መለካት ለማይችል ፍቅሩ ያለንን ምስጋና እናሳያለን፡፡ Testimonies, vol. 3, p. 511. ChSAmh 266.2