Go to full page →

ሃሳበ ቆራጥነት ChSAmh 316

ነፍሳትን ለእግዚአብሔር በማሸነፍ ሥራ የተሰለፉ የጋለ ስሜትና ቆራጥነት ሊያሳዩ የግድ ነው፡፡ እኛ እንደ እግዚአብሔር መሣሪያነታችን ሃሳበ ቆራጥ ሆነን ሳንሰናከል በወኔ ካልሠራን በቀር ነፍሳት እየጠፉ መሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡—Testimonies, vol. 6, p. 418. ChSAmh 316.4

እግዚአብሔር ታላቅ ሥራ እንድንሠራ ጠርቶናል፡፡ ይህን ሥራ በትክክልና በቆራጥነት ከግብ በማድረስ እውነት ታላቅ ባለ ውለታችን መሆኑን በሕይወታችን እናሳይ፡፡Testimonies, vol. 6, p. 418. ChSAmh 316.5