Go to full page →

ትዕግሥት ChSAmh 318

ከየሱስ ጋር አብረው የሚሠሩ ሠራተኛ እንደመሆንዎ አገልግሎት ለሚሰጧቸው ሁሉ የተለየ ትዕግሥት ሊኖርዎ ይገባል፡፡ ውስብስብነትየሌለውን ይህን ሥራ ሳይንቁ ወደ ተባረከው ውጤት አሻግረው መመልከት ይኖርቦታል፡፡ አገልግሎት የሚሰጡት ሰው አእምሮዎ በሚፈልገው አቅጣጫ አልጣ ሲል “እንዲህ ያለው ዳነ-አልዳነ እንደፈለገው ይሁን” ብለው በልብዎ የሚያጉተመትሙት ሊሆን አይገባም፡፡ ክርስቶስ ለአፈንጋጮች ከዚህ ተመሳሳይ አካሄድ ቢጠቀም ምን ሊከሰት ይችል ነበር? ነገር ግን ውጤቱን ለእግዚአብሔር ትተው ምስኪን ነፍሳትን ለማዳን የሞተው ክርስቶስ እንዲከተሉት በተወልዎ ምሳሌና ምግባር መሰረት የእርሱን መንፈስ ተላብሰው ቢሠሩ በዚህ vይወት ሊከናወንልዎ የሚችለውን የመልካም ነገር ብዛት በምንም መስፈሪያ ሊለኩት አይችሉም፡፡-- Testimonies, vol. 4, p. 132. ChSAmh 318.1

በአካል ለተገናኗቸው ሁሉ በቅን ልብ፣ _ በፍቅርና _ በትዕግሥት ይሥሩ፡፡ ትዕግሥት የማጣት መንፈስ አይታይብዎ፡፡ ደግነት የጎደላት አንዲትም ቃል ብትሆን hአንደበትዎ አትውጣ፡፡ የክርስቶስ ፍቅር በልብዎ ይስፈን—በደግነት ስለ ተሞላው መልካም ሕጉ ሁሌም ከመናገር ወደ ኋላ አይበሉ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 41. ChSAmh 318.2