Go to full page →

ከፍ ያለውን ደረጃ ጠብቆ መጓዝ ChSAmh 330

ደረጃውን የጠበቀ ከፍ ያለ አገልግሎት የመስጠት ብቃት ያላቸው የብዙዎች እንቅስቃሴ ኢምንት በመሆኑ ሥራቸውም የዛኑ ያህል እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ ነፍሳት ታላቅ የሕይወት ዓላማና—ሊቆናጠጡት የሚገባ ከፍ ያለ ደረጃ የሌላቸው ይመስል በሺ የሚቆጠሩ ወገኖች በከንቱ ይመላለሳሉ፡፡ ለዚህ እንደ አንድ ምክንያት መጠቀስ የሚችለው ለራሳቸው የሚሰጡት አነስተኛ ግምት ነው፡፡ ክርስቶስ ለእያንዳንዳችን የመጨረሻውን ዋጋ ከፍሎአል፡፡ ስለዚv በተከፈለልን ዋጋ መሰረት ከፍ ያለውን ግምት ለራሳችን እንስጥ፡፡— Gospel Workers, p. 291. ChSAmh 330.1

ምድራዊ ህይወቱን ሙሉ ጽኑና የማይታክት ሠራተኛ የነበረው የሱስ ከፍ ያለ አገልግሎት ለመስጠት ይጠባበቅና ያላሰለሰ እንቅስቃሴ ያደርግ ነበር፡፡The Desire of Ages, p. 72. ChSAmh 330.2

ለጌታ ለመሥራት በአገልግሎት የተሰማሩ ብዙዎች ከሚያስቡት የላቀ፣ ጥልቅና ሰፊ ተሞክሮ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ የታላቁ አምላካዊ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ብዙዎች ወደ hብሩ መመልከትም ሆነ ከክብር ወደ ክብር ስለመለወጥ ያላቸው ዕውቀት አነስተኛ ነው፡፡ ብዙዎች ክርስቶስ ስለ ሠራው ሥራ ያላቸው ግንዛቤ ደብዛዛ ቢሆንም ነገር ግን ልባቸው በእርሱ ሐሴት ያደርጋል፡፡ የአዳኙ ፍቅር በሙላትና በጥልቀት እንዲኖራቸው ይናፍቃሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች እግዚአብሔርን ለማወቅ የሚገፋፋቸውን እያንዳንዱን የነፍሳቸውን ምኞት አጥብቀው ይያዙ፡፡Gospel Workers, p. 274. ChSAmh 330.3

ለአገልጋዮች፣ ለሐኪሞች፣ ለመምህራንና በሌሎች የጌታ አገልግሎት ማዕቀፍ ውስጥ ላላላችሁ የምሰጣችሁ መልእክት አለኝ፡፡ ጌታ ከፍ ወዳለው የቅድስና ደረጃ እንድትመጡ ጥሪ ያቀርብላችኋል፡፡ እስካሁን ከተመላለሳችሁበት በበለጠ እንደርስበት ይሆን? ብላችሁ አስባችሁ እንኳ የማታውቁት ዓይነት ጥልቅ ተሞክሮ - ላይ ልትደርሱ የግድ ነው፡፡ ብዙዎቻችሁ የአዳኙ ፍቅር በሙላትና በጥልቀት እንዲኖራችሁ ብርቱ ናፍቆት አላችሁ፡፡ ውስጣችሁ የእርካታ ስሜት የማይሰማው ቢሆንም ነገር ግን ተስፋ አትቁረጡ፡፡ ምርጥ የሆነውንና የተቀደሰውን የልባችሁን ፍቅር ለየሱስ ስጡት፡፡ የእያንዳንዱ የብርሃን ጨረር ባለጸጎች ሁኑ፡፡ እያንዳንዱ የነፍሳችሁ ምኞት የእግዚአብሔርን ፈቃድ አጥብቆ የያዘና የሚከተል ይሁን፡፡ የቅድስናን ህይወት የተጋሩና ራስዎን መንፈሳዊነትን ማዕከል ላደረገው አስተሳሰብ አሳልፈው የሰጡ ይሁኑ፡፡ ቀደም ባለው ሕይወትዎ የመጀመሪያዎቹን የአምላካዊ ክብር የብርሐን ጨረሮች ተመልክተው ነበር፡፡ ጌታን ለማወቅ በተከተሉት መጠን አምላካዊው መንገድ ከማለዳ አንስቶ እየጨመረ እንደሚሄድ የብርሃን ጸዳል መሆኑን ያስተውላሉ፡፡ “የጻድቃን መንገድ ሙሉ ቀን እስኪሆን ድረስ ብርሃኑ እየጎላ እንደሚሄድ የማለዳ ውጋገን ነው፡፡” ኃጢአታችንን ከተናዘዝን፣ ንስሐ ከገባንና ይቅርታ ከተቀበልን በኋላ ፍጹም የሆነው የወንጌል እምነታችን እንደ ቀትር ብርሃን ወለል እስኪል ስለ ክርስቶስ መማራችንን እንቀጥላለን፡፡--Testimonies, vol. 8, p. 318. ChSAmh 330.4