Go to full page →

ጨዋነት ChSAmh 334

ከማንኛውም ኃይለኛ ክርክር ይልቅ ስለ እውነት የበለጠ ጠቃሚ የሆነነገር መናገር የሚቻለው የሚያናድድ ሁኔታ ሲፈጠር የተረጋጋ መንፈስ የኖረ እንደሆነ ነው፡:The Desire of Ages, p. 353. ChSAmh 334.1

ጤዛና ዝናብ በጠወለገው ተክል ላይ እንደሚወርድ--የሰዎችን ልብ ከስህተት ለማሸነፍ የሚጥሩ ቃላት በነፍሳት ላይ ተለሳልሰው ይውረዱ፡፡ ወደ ሰዎች ልብ መድረስ የእግዚአብሔር ቀዳሚ ዕቅድ ነው፡፡ እውነትን በፍቅር በመናገር በሕይወት ላይ ተሐድሶ ማምጣት በሚችለው የእርሱ ኃይል መታመን ይኖርብናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ በፍቅር የሚነገረው ቃል በአድማጩ ነፍስ ፍሬ እንዲያፈራ ያደርጋል፡፡—The Ministry of Healing, p. 157. ChSAmh 334.2

በርኅራኄ የተሞላው መንፈስና የሰዎችን ልብ ማሸነፍ የሚችለው የተረጋጋ ምግባር በስህተት ውስጥ ያለውን ነፍስ በማዳን እጅግ በርካታ ኃጢአት መሸሸግ ይችላል፡፡ በእርስዎ ጸባይ ውስጥ የሚገለጠው የክርስቶስ ማንነት የተገናኟቸውን ሁሉ መለወጥ የሚችል ኃይል አለው፡፡ ክርስቶስ በየቀኑ በሕይወትዎ ሲታይ ሰብዓዊውን ተፈጥሮ ዳግመኛ ማበጃጀት የሚችለው፣ ንቁና ሁሌም በሥራ ላይ የሚገኘው፣ ነፍሳት ላይ ረጋ ያለ፣ አሳማኝና ብርቱ ተጽእኖ የሚያሳድረው የቃሉ ኃይል የጌታችንንና የአምላካችንን ውበት እንደያዘ በእርስዎ ይገለጣል፡፡Thoughts from the Mount of Blessing, p. 129. ChSAmh 334.3