Go to full page →

ምዕራፍ 27—አገልግሎታችን የሚያስገኝልን ሽልማት ChSAmh 368

በዋጋ ሊተመን የማይችል ChSAmh 368

እግዚአብሔርን ማገልገል ዋጋ የሌለው ከንቱ ሥራ አይደለም፡፡ vይወታቸውን ለእርሱ _ አገልግሎት ላዋሉ በዋጋ ሊተመን የማይችል ሽልማት ተዘጋጅቶአል፡፡—Testimonies, vol. 4, p. 107. ChSAmh 368.1

ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚውል ማንኛውም ዓይነት መሥዋዕትነት “ወደር በሌለው የጸጋው ባለጠግነት” መጠን ይከፈለዋል፡፡ The Desire of Ages, p. 249. ChSAmh 368.2

በዚህ ምድር ከክርስቶስ ጋር መሥራታችን ለሚመጣው ዓለም ታላቅ ኃይል በመሆን ልዩ መብትና ጥቅም ያስገኝልናል፡፡Christ’s Object Lessons, p. 361. ChSAmh 368.3