Go to full page →

ወጣቶች በቤተ hርስቲያን ሥራ ChSAmh 39

በጥሩ ሁኔታ የተደራጀና የሠለጠነ የወጣት መክሊት በቤተ ክርስቲያናችን ይፈለጋል፡፡ ወጣቶች ሞልቶ እየፈሰሰ ባለው አፍላ ጉልበታቸው አንዳች ነገር እንዲያደርጉበት ይጠበቃሉ፡፡ እነዚህ አፍላ ጉልበቶች በትክክለኛው መስመር ካልተገሩየገዛ መንፈሳዊነታቸውን ሊጎዱ በሚችሉ አካሄዶች ተጠምደው በተጎዳኙአቸው ላይ ጉዳት እንዲደርስ መንስኤ ይሆናሉ፡፡-- Gospel Workers, P. 211. ChSAmh 39.4

ለወጣቶች ያለን ኃላፊነት ልቦቻቸውን ለእግዚአብሔር ሲሰጡ ሊያበቃ አይችልም፡፡ ወጣቶች ለጌታ ሥራ ፍላጎት ያደረባቸውና ለሥራው ግስጋሴ የሚጠብቅባቸውን ለመሥራት የሚገፋፉ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ምን ያህል መሠራት እንደሚኖርበት ማሳየትና እያንዳንዱ ወጣት የድርሻውን እንዲያበረክት ማነሳሳት ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ ይልቁንም ለጌታ እንዴት መሥራት እንደሚኖርባቸው ሊማሩ ይገባል፡፡ ነፍሳትን ለክርስቶስ ማሸነፍ የሚያስችላቸውን ምርጥ ዘዴ ጥቅም ላይ በማዋል ሥልጠና ሊሰጣቸው፣ ሥነ ሥርዓት ሊማሩና ልምምድ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ፍጹም ከማስሰል በጸዳ አካሄድ ወጣት የዕድሜ እኩዮቻቸውን ለመርዳት እንዲሞክሩ አስተምሯቸው፡፡ እነርሱን የሥራው ተካፋይ የሚያደርጉ በሥርዓት የተቀረጹ ልዩ ልዩ የወንጌል አልግሎት ዘርፎች ይዘጋጁ፤ እርዳታና መመሪያም ይሰጣቸው፡፡ ይህ ሲሆን እንዴት ለጌታ መሥራት እንዳለባቸው ትምህርት ያገኛሉ፡፡— Gospel Workers, P. 210. ChSAmh 40.1