Go to full page →

የሥራ ዘርፎች ChSAmh 44

ወጣቶች ጠቃሚ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሏቸው አያሌ የሥራ ዘርፎች አሉ፡፡ ነርሶችን፣ የጉብኝት ቡድኖችን፣ የቤት ለቤት አገልግሎት ሰጪዎችን፣ የወንጌል አገልጋዮችን እንዲሁም የሕhምና አገልግሎት ሰጪ ወንጌላውያንን የሚያሰለጥኑ ተቋማት በብቃት ሊደራጁ ይገባል፡፡--Counsels to Teachers, p. 546. ChSAmh 44.1

ወጣቶች ወጣቶችን ለመርዳት የሚያስችላቸውን ትምህርት እንዲያገኙ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ይህን ሥራ ለመሥራት መሻታቸው ሰፊ በሆነ የአገልግሎት መስh የተቀደሰ ሥራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ልምድ ለማካበት ይረዳቸዋል፡፡-- Testimonies, vol. 6, p. 115. ChSAmh 44.2

ወጣት ወንዶችና ሴቶች በመኖሪያ አካባቢያቸው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸውን ተምህርት ሊያገኙ ይገባል፡፡ ሁሉም ለሥራው ብቁ የሚያደርጋቸውን ተገቢ ሥልጠና በመውሰድና ራሳቸውን ከሁናቴዎች ጋር በማስማማት በአንድ ልብና ሐሳብ ለዚህ ጊዜ ገጣሚ የሆነውን ሥራ በጥልቅ ያስተውሉ፡፡Testimonies, vol. 9, pp. 118, 119. ChSAmh 44.3