Go to full page →

ለአገልግሎት መዘጋጀት ChSAmh 45

ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሆይ-እንደ ክርስቶስ ምልምል ወታደርና ሠራተኝነታችሁ ነፍሳትን ከውድመት ለማዳን የሚያስችላችሁን አደረጃጀት ፈጥራችሁ ብልህና ጥንቁቅ የሆነውን ችሎታችሁን ለጌታ አገልግሎት ማዋል አይኖርባችሁ ይሆን? ይህን ሥራ ለመሥራት በእያንዳንዱ ቤተ ክርስቲያን የተዋቀሩ አካላት ይኑሩ. . . . የሱስን በእርግጥ የሚወዱ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሰንበትን ለሚጠብቁ ወገኖች ብቻ ሳይሆን ከእምነታችን ውጪ ለሆኑም ጭምር ራሳቸውን ለአገልግሎት እንደ አንድ አካል ማደራጀት አይኖርባቸውም? Signs of the Times, May 29, 1893. ChSAmh 45.1

... ወጣት ወንዶች፣ ሴቶችና ታዳጊዎች በየሱስ ስም ወደ አገልግሎት ይግቡ፡፡ ሕብረት ፈጥረው ዕቅድና የድርጊት መርኅ ግብር ያውጡ፡፡ የአንድነት የጸሎት ጊዜ መድበው ጌታ ጸጋውን እንዲሰጣቸው በመጠየቅ በተባበረ አንድነት ወደ ድርጊት የሚገባ የሥራ ጓዶችን ያቀፈ አካል መመሰረት አይችሉምን? -Youth’s lnstructor, Aug 9, 1894. ChSAmh 45.2