Go to full page →

መዘግየት—ሞት ሊያስከትል የሚችል ስህተት ChSAmh 57

የእግዚአብሔር ሕዝቦች የሆነ ለውጥ እንዲመጣ እንዲጠባበቁ የሚያስገድዳቸው ኃይል እንዳለ ተመልክቼ ነበር፡፡ ሆኖም በመሳሳታቸው ወደ ተስፋ መቁረጥ ያመራሉ፡፡ ሥራውን ራሳቸው አጥብቀው በመያዝ ጊዜ ሳያባክኑ እውተኛውን ዕውቀት ያıኙ ዘንድ በጽኑ ወደ እግዚአብሔር ማልቀሳቸው የግድ ይሆናል፡፡ ከፊት ለፊታችን እያለፉ ያሉት ትዕይንቶች እኛን ለማነሳሳት በቂ ኃይል ያላቸውና ለማድመጥ ፈቃደኞች የሆኑትን ልቦች የእውነት መኖሪያ እንዲሆኑ የሚማጸኑ ናቸው:፡ የምድር መከር ወደ መድረሱ ተቃርቦአል፡:--Testimonies, vol. 1, p. 261. ChSAmh 57.4

በሌላ በኩል አንዳዶች ዛሬ እጆቻቸው ውስጥ የሚገኙትን ዕድሎች ጥበብ በተሞላው አካሄድ በማሻሻልና በማጎልበት ፋንታ በሌሎች ላይ ስርጸት ለመፍጠር ያስችሉናል፣ ብርቱ ኃይል እንቀበልባቸዋለን ያሏቸውን ልዩ የመንፈሳዊ መነቃቃት ወቅቶች እጆቻቸውን አጣጥፈው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በእነርሱ በኩል አንዳችም ጥረት ሳይኖርየተለየ በረከት ተቀባይ፣ የተለወጡና ለአገልግሎቱ ገጣሚ የሚሆኑባቸውን ጊዜያቶች አሻግረው እየተመለከቱ፤ ዛሬ ተግባር ላይ እንዲያውሏቸው የተሰጧቸውን ኃላፊነቶችና መልካም ዕድሎች ችላ እያሉ ብርሃናቸው እንዲደበዝዝ ይፈቅዳሉ፡፡--The Acts of the Apostles, p. 54. ChSAmh 58.1