Go to full page →

የድራማው የመጨረሻ ክፍል ChSAmh 69

ይህ መልእክት ከመቼውም ጊዜ ይልቅ እንደዚህ ዘመን በብርቱ ኃይል መቅረብ አስፈልጎት አያውቅም፡፡ ዛሬ ዓለም የእግዚአብሔር የመሆኗን ስሜት አብልጣ እያጣችና ሰዎች አምላካዊውን ሕግ በድፍረት እየተላለፉ ይገኛሉ፡፡ የምድር ነዋሪዎች ርክስና ጽዋ እየሞላ ነው፡፡ ምድር አጥፊው የጥፋት ምኞቱን እንዲፈጽም ወደ ሚፈቀድለት ሁናቴ ላይ ተቃርባለች፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ሰንበት ወደ እሁድ ለውጦ የእግዚአብሔርን ሕግ በሰው ሕግ በመተካት የሰብዓዊውን ሥልጣን ከፍታ የሚያሳየው የድራማው ክፍል የትዕይንቱ የመጨረሻ አካል ነው፡፡ ይህ ለውጥ ዓለማቀፋዊ ገጽታ ሲላበስ እግዚአብሔር ራሱን ይገልጣል፡፡ ምድርን ክፉኛ ያናውጥ ዘንድ በንጉሣዊ ግርማው ይነሳል፡፡ የምድርን ነዋሪዎች ስለ ኃጢአታቸው ሊቀጣ ይወጣል፡፡ ምድርም ያፈሰሰችውን ደም ትገልጣለች ከዚv በኋላ አትሸፋፍንም፡፡-Testimonies, vol. 7, p. 141. ChSAmh 69.1