Go to full page →

ትምህርት ቤት በሚዘጋበት ወቅት ChSAmh 91

ትምህርት ቤት በሚዘጋበት ወቅት ብዙዎች የወንጌላውያን ድጋፍ ሰጭ ሆነው ለአገልግሎት የሚወጡባቸው ዕድሎች አሉ፡፡ ታማኙ መንፈሳዊ መጽሐፍ ሻጭ አያሌ ቤቶችን በሚያካትት ጉዞው የዚህን ዘመን እውነት የያዙ ጽሑፎችን ያድላል፡፡ ተማሪዎቻችን መንፈሳዊ መጻሕፍትን የርስቲያን አገልግሎት እንዴት መሸጥ እንደሚኖርባቸው ሊማሩ ይገባል፡፡ በዚህ የሥራ ዘርፍ የሚሰማሩ ሁሉ ጥልቅ የክርስትና ተሞክሮ ያላቸው፣ የሚዛናዊ አስተሳሰብ ባለቤት የሆኑ፣ ጠንካራ ስብዕና የተላበሱና ዘመናዊ ትምህርት የቀሰሙ ሊሆኑ ይገባል፡፡ አንዳንዶች አሁን እየተሠራ ካለው የበለጠ ክንውን ወደፊት መገኘት እንደሚችል አመላካች የሆነ ለወጣቶች የረዳትነት ዕውቀት ለማስጨበጥ የሚያስችል ችሎታ፣ ትምህርትና ተሞክሮ አላቸው፡: የዚህ ተሞhሮ ባለቤት የሆኑ ሁሉ ሌሎችን የማስተማር ልዩ ተልዕኮ አላቸው::Counsels to Teachers, pp. 546, 547. ChSAmh 91.4