የእውነት መልእክተኞች አዳዲስ የተለወጡ ነፍሳትን ለወንጌል አስተምህሮ እንዲያሸንፉ ጉልv አስተዋጾ ያደረገችው በየሩሳሌም የነበረችው ቤተ ክርስቲያን አወቃቀር በተለያዩ ስፍራዎች ለተመሰረቱ ቤተ ክርስቲያኖች በምሳሌነት አገልግላለች. . . ቆየት ባለው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ አያሌ አማኝ ቡድኖች በብዙዎቹ የዓለም ክፍሎች እየተዋቀሩ ሲመጡ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ኅብር ተጠብቆ እንዲቆይ የሚያስችለው አወቃቀርም ይበልጥ ፍጹም እየሆነ መጣ፡፡ እያንዳንዱ አባል የራሱን ድርሻ በጥንቃቄ የሚወጣ፣ የተሰጡትን መክሊቶች በማስተዋል የሚጠቀም ነበር፡፡--The Acts of the Apostles, pp. 91, 92. ChSAmh 102.4
እያንዳንዱን አባል ለአገልግሎት ገጣሚ ማድረግ እያንዳንዱ እውነትን ተቀብሎ ከወታደሮች እንደ አንዱ የሆነ ክርስቲያን አገልግሎት ሊሰጥ በሚችልበት እዝ ሥር ይመደባል፡፡ ማንም ቢሆን የተመደበበት የውጊያ ግንባር የሚጠይቀውን ለመፈጸም ፈቃደኛ ሊሆን ይገባል፡፡Testimonies, vol. 7, p. 30. ChSAmh 103.1
እግዚአብሔር የሚጠይቀን አያሌ ተቋሞችን፣ ግዙፍ ሕንፃዎችንና ሠርቶ ማሳያዎችን እንድንገነባ ሳይሆን በእርሱ ከተመረጡ የከበሩ ሕዝቦቹ ጋር ኅብር የሚፈጥሩ ተግባራትን እንድናከናውን ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ለአገልግሎት በተመደበበት ስፍራ ሆኖ በአስተሳሰቡ፣ በእነጋገሩና በተግባሩ ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር ኅብር ሲፈጥር ሥራው ሚዛኑን የጠበቀ ፍጻሜ ያገኛል-- Testimonies, vol, 6, p. 293. ChSAmh 103.2
ብዙውን ጊዜ የአንድ ሠራዊት ጥንካሬ በአዛዦች ብቃትና ቅልጥፍና ይለካል፡፡ሁሉም በተሰለፈበት ተዋረድ ከፍ ያለ ብቃት ባለቤት የሚያደርገውን አቅም የማጎልበት ሥራ ለሥራት ከሚኖረው ብርቱ ምኞት አኳያ ብልሁ የጦር ጀነራል ያንዳንዱ ወታደር ብቃት እንዲኖረው የሚያስችለውን ሥልጠና እንዲያገኝበቅድሚያ አዛዦች በቂ ትምህርትና የውጊያ ሥልት እንዲቀስሙ ያደርጋል፡፡ ጀነራሉ በአዛዦቹ ብቻ ቢተማመን ስኬታማውን ዘመቻ አደርጋለው ብሎ መጠበቅ አይችልም፡፡ የሠራዊቱ አካል ከሆነ ከእያንዳንዱ ወታደር ላገኘው ታማኝና ያላሰለሰ ጥረት ተገቢውን አጽንኦት ይሰጣል፡፡ ብርቱና ግዙፍ የሆነው ኃላፊነት በጦር አዛዦች ላይ ይወድቃል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 116. ChSAmh 103.3
ጌታ ለወንጌል ሠራተኞች ጥሪ ያቀርባል፡፡ ማን ይሆን ምላሽ የሚሰጠው? ሁሉም ሰው ለሌሎች ጥንቃቄ የማድረግና ኃላፊነት የመሸከምየመሪነት ስብእና ስለሌለው ሠራዊቱን የሚቀላቀል ሁሉ ጀነራል፣ ሻምበል፣ ሃምሳ _ አለቃ ወይም አሥር አለቃ አይሆንም፡፡ ነገር ግን መሠራት የሚኖርበት ሌላ አበይት ሥራ አለ፡፡ የተጠናከረ ምሽግ የሚቆፍሩ፣ ዘብ ሆነው የሚቆሙ እንዲሁም መልእክት የማስተላለፍ ሥራ የሚሠሩ መኖር አለባቸው፡፡ ምንም እንኳ የአዛዦች ቁጥር ጥቂት ቢሆንም ነገር ግን ወታደራዊውን ሰልፍ ለመሙላት ከፍተኛ ቁጥር ያለው _ ሠራዊት ያስፈልጋል፡፡ የሠራዊቱ ስኬት በእያንዳንዱ ወታደር ታማኝነት የሚለካ ሲሆን--የአንድ ሰው ፍርሃት ወይም ክህደት በመላው ሠራዊት ላይ ጉዳት ያስከትላል፡፡-- Gospel Workers, pp. 84, 85. ChSAmh 104.1
የስኬት ምስጢር የሕዝባችን ኅብር ኖሮት መሥራት የአምላካዊው አገልግሎታችን ስኬት ምስጢር ነው፡፡ ተግባራችን የተጠናከረ መሆን ይኖርበታል፡፡ እያንዳንዱ የክርስቶስ ቤተሰብ አባል እግዚአብሔር እንደሰጠው ችሎታና መክሊት ለአምላካዊው አገልግሎት የበኩሉን ድርሻ ማበርከት ይኖርበታል፡፡ እኛ ሁላችን ትከሻ ለትከሻ ተያይዘንና ልብ ለልብ ሆነን እያንዳንዱን መሰናክልና አስቸጋሪ ሁናቴ እየተጋፈጥን ወደፊት መግፋት ይኖርብናል፡፡ Review and Herald, Dec. 2, 1890. ChSAmh 104.2
ክርስቲያኖች በአንድ የበላይ አዛዥ እየተመሩ እንደ ሙሉ የሙዚቃ ኦርኬስትራ ባንድ ኅብር ፈጥረው ለአንድ ዓላማ ስኬት ቢሠሩ ዓለምን ማነቃነቅ በቻሉ ነበር፡፡- Testimonies, vol. 9, p. 221. ChSAmh 104.3
መላእክት በሥራቸው ሁሉ ኅብር አላቸው፡፡ በእነርሱ የሚስተዋለው ፍጹም የሆነው ሥርዓት የመላው እንቅስቃሴአቸው መገለጫ ነው፡፡ የመላእክት ሠራዊትን በኅብር የተሞሉ እንቅስቃሴዎች አብልጠን ስንተገብር እነዚህ ሰማያዊ ወኪሎች ስለ እኛ የሚያደርጓቸው ጥረቶች ስኬታማ ይሆናሉ፡፡ አንዳችን ከሌላው ጋር ኅብር ፈጥረን አገልግሎት የመስጠታችን አስፈላጊነት የማይታየን፣ የተበታተንን፣ የተመሰቃቀልንና ከሥርዓት ያፈነገጥን ከሆን በጥንቃቄ የተዋቀሩትና ፍጹም በሆነ ሥርዓት የሚመላለሱት መላእክት ስኬታማ አገልግሎት ሊሰጡን {ይችሉም፡፡ ግርታን፣ ጥርጣሬንና የተቃወሰውን ሁናቴ የማበረታታትና ቡራኬ የመስጠት ሥልጣን ያልተሰጣቸው መላእክት በከፍተኛ ሐዘን ፊታቸውን ያዞራሉ፡፡ የሰማያዊ መልእክተኞችን እርዳታና ትብብር ለማግኘት የሚመኙ ሁሉ ከእነርሱ ጋር ኅብረት ፈጥረው ሊሠሩ ይገባል፡፡ ከዚህ ውጪ ሥርዓትን ላልተከተለ፣ ለተቃወሰና ለተመሰቃቀለ አካሄድ ፈጽሞ ድጋፍ ሊያደርጉ አይችሉም: : Testimonies, vol. 1, pp. 649, 650. ChSAmh 104.4