Go to full page →

የዘመቻ ትእዛዛት ChSAmh 107

ክርስቲያኖች ተሰባስበው ወንጌልን ወዳልሰሙ ሕዝቦች እንዴት በስኬት መድረስ እንዳለባቸው ውይይት ያደርጉ በነበረበት ወቅት የዊሊንግቶኑ መስፍን በመካከላቸው ተገኝተው ነበር፡፡ የወንጌል ጥረቱን በማድረግ ሊገኝ የሚችለው ስኬት ከሚፈሰው ጉልበትና ገንዘብ ጋር ተመጣጣኝ እንደሆነ መስፍኑን ለመጠየቅ ሲሞክሩ በመሃል አንድ ሸምገል ያሉ ወታደር ብድግ አሉና “ወንድሞች ሆይ! ለመሆኑ የዘመቻ ትእዛዛችሁ ምን ይላል? ስኬት ቁጭ ብላችሁ የምትወያዩበት ጥያቄ ሊሆን አይችልም፡፡ የተሰጣችሁን ትእዛዝ ሳነበው ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ’ ይላል፡፡ ወንድሞች-የተሰጣችሁን የዘመቻ ትእዛዝ ታዘዙ”፡፡ Gospel Workers, p. 115. ChSAmh 107.1