Go to full page →

ከፍ ያለውን አhሊል ማለም ChSAmh 150

ደካሞች ወይም ፈሪዎች ልንሆን አይገባም፡፡ አብሮን የሚኖረውን አምላካዊ ክብር በምድራዊ ምቾት፣ ተድላ፣ ደስታ ወይም ለሥጋ ፍላጎት ማርኪያ መሸቀጥ ውጤቱ እጅግ አስከፊ ይሆናል፡፡ ከእግዚአብሔር እጅ የሚቸረው ስጦታ አሸናፊውን ይጠባበቃል፡፡ ይህ ለአንዳችንም የማይገባን ስጦታ--ያለ ምንም ክፍያ ከእርሱ በነፃ የሚሰጥ ነው፡፡ ስጦታው እጅግ ድንቅና የከበረ ቢሆንም “አንዱ ኮከብ ከሌላው ኮከብ በክብር እንደሚለይ” ማስታወስ ይኖርብናል፡፡ ከፍ ላለው ችሎታና ዕውቀት ብርቱ ጥረት እንድናደርግ እየተበረታታን በየሱስ ኃይል ወደ ምንቀዳጀው አክሊል እናነጣጥር፡፡ “ጥበበኞች እንደ ሰማይ ጸዳል፤ ብዙዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ከዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ”፡፡ Review and Herald, Oct. 25, 1881. ChSAmh 150.1