Go to full page →

በቤትዎ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ነፍሳትን መጋበዝ ChSAmh 168

በቤትዎ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መርኅ ግብር ላይ ነፍሳትን በመጋበዝ የከበሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችንና እውነትን የሚያብራሩ መንፈሳዊ መጽሐፎችን አንብቡ፡፡ በመዝሙርም ሆነ በጸሎት ኅረት እንዲፈጥሩ ግብዣ አድርጉላቸው፡፡ ክርስቶስ ቃል በገባው መሰረት በእንደነዚህ ዓይነቶቹ አነስተኛ ስብሰባዎች ስለሚገኝ ልቦች በጸጋው የተነኩ ይሆናሉ፡፡ - -The Ministry of Healing, pp. 152, 153. ChSAmh 168.3

አጵሎስ በኤፌሶን እያለ “በምኵራብ በድፍረት ይናገር ጀመረ”፡፡ የወንጌልን ሙሉ ብርሃን አለመቀበሉን ያስተዋሉት ከአድማጮቹ መካከል የነበሩት ጵርስቅላ እና አቂላ “ወደ ቤታቸው ወስደው የእግዚአብሔርን መንገድ ይበልጥ አስተካክለው አስረዱት”፡፡ ይv ከእነርሱ ያገኘው ትምህርት ግልጽ ማስተዋል እንዲያገኝ ረድቶት በሳል ችሎታ ካላቸው የክርስትና እምነት ተሟጋቾች መሃል አንዱ ለመሆን በቃ፡፡The Acts of the Apostles p. 270. ChSAmh 168.4