Go to full page →

«ተጠንቀቁ» GWAmh 64

ጳውሎስ ለጢሞቴዎሥስ የሰጠው ምክር ለማንኛውም ጠጣት ወንጌላዊ ይጠቅማል፡፡ «ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፡፡› ፤፲ ጢሞ. 4፡16 «ለራስህ” የሚለው ሐረግ የመጀመሪያውን ደረጃ ይይዛል፡፡ መጀመሪያ ጌታ አንዲያነጻህና አንዲቀድስህ ራስህን አስረክበው፡፡ ከማይገለጽ ከማራኪ ንግግር ይልቅ የተቀደሰ ሕይወት ታላቅ ምሣሌነት (አብነት) አለው፡፡ የነፍስህን ፋኖስ ወልውልና በመንፈስ ቅዱስ ዘይት ሙላው፡፡ የተሳካ ሥራ ሊያሠራ የሚችለውን የማስተዋል ፀጋ ከክርስቶስ ዘንድ: ሕይወቱን ለለወጠላቸው መሥራት ምን ማለት መሆኑን ከእርሱ ተማር፡፡ GWAmh 64.2

መጀመሪያ ለራስህ፤ ከዚያም ለትምህርትህ «ተጠንቀቅ» ልብህን በኃጢዓት አታደንድን:: ልምድህንና ጠባይህን ተመራመር፡፡ በእግዚአብሔር ቃል አየመዘንህ የማይገጥመውን ጠባይህን አስወግድ፡፡ ቃሉ እንዲስተዋልህ በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክከህ በፀሎት ተማጸነው፡፡ እውነትን ከልብህ የምትከተል ከሆንህ ተከራካሪ ሲያጋጥምህ መላዕክት በአፍህ ላይ ሆነው የምትመልሰውን ያቀብሉሃል፡፡ - ቀን በቀን የሱስን ከተገናኘህ ቃልህና ሥራህ ታላቅ አብነት ይኖረዋል፡፡ GWAmh 64.3