Go to full page →

የጤናን ደንብ እንዲት ማስተማር እንዲማቻል GWAmh 147

እግዚአብሔር ሐክምቻችን፣ ወኪሎቻችን፣ ወንላዊያኖቻችንና የቤተ ክርስቲያን አባሎችን ባመጋገባቸው ድንገተኛ ለውጥ አንዲያደርጉ በመጠየቅ ያላመኑትን እንዲያደናግሩአቸው አይፈቅድም፡፡ የጤናን ደንብ ትምህርት ሲከታተሉ እግዚአብሔር ልባቸው የቀናውን ይመራቸዋል፡፡ ሰምተው ያምናሉ:: GWAmh 147.4

በተጨማሪም የጤና ደንበ ትምህርትን አቀራረብ በተመጻዳቂነት መንፈስ መሆን የለበትም:: ባለትወቅ ጨለማ ለሚራመዱት ሰዎች ማንም አንቅፋት መሆን የለበትም፡፡ መልካምን ነገር ከሚገባው በላይ ማሞገስ የቀረቡትን ሊያርቅ ይችላል፡፡ የመሻትን መግዛት ትምህርትን በሚስብ አቀራረብ አቅርቡ፡፡ GWAmh 148.1

መሆን አለበት በሚል ሀሳብ-ግትርነት መነሳት የለብንም፡፡ አዲስ የሥራ ቦታ የሚከፍቱ ወንጌላዊያን በአንድ ጊዜ ስለምግብ በመናገር ችግር ማስነሳት የለባቸውም፡፡ በችኮላ ምክንያት መንገዱን አጣበው የሜቀርቡትን እንዳይክለክሉ ይጠንቀቁ፡፣ ሰዎችን ከኋላ ሆናችሁ ከመገፋፋት ይልቅ በፊታቸው በኩል ሆናችሁ ምሩአቸወ፡፡ GWAmh 148.2

በየትኛውም የማስተማሪያ ቦታ የጤናማ ምግብ አሠራር ትምህርት ሊሰጥ ይገባል፡፡ እያንዳንዱ ማህበር በአካባቢው የሚያገኘውን ለምግብ የሚያገለግል ሀብት በጠቀሚ ሁኔታ እንዲጠቀምበት በመልካም መምህር አማካይነት ይማር ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ ድሀም ሆነ ሀብታም ጤናማ ኑሮን መኖር ይችላል፡፡ GWAmh 148.3