Go to full page →

ልባዊ የሆነ ጸሎት መልስ ያገኛል MYPAmh 163

በልባችን ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት እንችላለን፤ ከክርስቶስ ጋር በጓደኝነት አብረን መጓዝ እንችላለን፡፡ በዕለቱ ሥራችን ላይ ተሰማርተን እያለን የማንም ጆሮ ሳይሰማ የልባችንን መሻት ለእርሱ መተንፈስ እንችላለን፡፡ ያ ሰው ሳይሰማን የምንተነፍሰው ቃል አይሞትም፣ አይጠፋምም፡፡ የነፍስን መሻት አስምጦ የሚያስቀር ምንም ነገር የለም፡፡ ከመንገድ ዋካታና ከማሽኖች ጩኸት ከፍ ብሎ ይወጣል፡፡ የምንናገረው ለእግዚአብሔር ስለሆነ ጸሎታችን ይሰማል፡፡ MYPAmh 163.5

ጠይቁ ይሰጣችሁማል፡፡ ለትህትና፣ ለጥበብ፣ ለድፍረት፣ ለእምነት መጨመር ጠይቁ፡፡ ለእያንዳንዱ ልባዊ ለሆነ ጸሎት መልስ ይመጣል፡፡ እንደምትፈልጉት ወይም በፈለጋችሁት ሰዓት ላይመጣ ይችላል፣ ነገር ግን ፍላጎታችሁን ሊሞላ በሚችልበት ሁኔታና ጊዜ ይመጣላችኋል፡፡ በብቸኝነት፣ በድካምና በፈተና ውስጥ ሆናችሁ የምትጸልዩአቸውን ጸሎቶች እግዚአብሔር መልስ የሚሰጠው ሁልጊዜ እናንተ በምትጠብቁበት ሁኔታ ሳይሆን ለእናንተ በሚጠቅም ሁኔታ ነው፡፡— Gospel Workers, 254-258. MYPAmh 163.6