Go to full page →

መጽሐፍ ቅዱስን ለራሳችሁ መርምሩ MYPAmh 169

ወጣቶች ለራሳቸው ቅዱሳን መጽሐፍትን መመርመር አለባቸው፡፡ እውነትን መሻት በእድሜ ላረጁና ልምድ ላላቸው እንደሆነና ወጣቶች ከእነርሱ እንደ ባለ ሥልጣናት መቀበል (መስማት) እንዳለባቸው ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡ አይሁዳውያን እንደ ሕዝብ የጠፉት በገዦቻቸው፣ በካህናቶቻቸውና በሽማግሌዎቻቸው አማካይነት ከመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ስለ ራቁ ነው፡፡ የኢየሱስን ትምህርቶች አድምጠው ቢሆንና ቅዱሳት መጽሐፍትን ለራሳቸው መርምረው ቢሆን ኖሮ አይጠፉም ነበር፡፡ MYPAmh 169.1

ለማንኛውም አእምሮ ቢሆን ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ውስጥ አንዱን እንኳን ብልጽግናውንና ታላቅነቱን ሙሉ በሙሉ ማስተዋል የማይቻል ነው፡፡ አንድ ሰው ካየው ነገር የአንዲቱን ነጥብ ክብር ሲገነዘብ ሌላኛው ደግሞ በሌላኛው አቅጣጫ ጸጋውንና ውበቱን ያስተውላል፤ በዚህ ሁኔታ ነፍስ በሰማያዊ ብርሃን ይሞላል፡፡ ክብሩን ሁሉ አይተን ቢሆን ኖሮ መንፈሳችን ይዝል ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ካሉን የበለጡ መገለጦችንና ከእግዚአብሔር የተትረፈረፉ ተስፋዎችን ማግኘት እንችላለን፡፡ ለእኛ የተዘጋጀውን የበረከት ሙላት ማየት አለመቻላችን ያሳዝነኛል፡፡ በየቀኑ በእርሱ መገኘት ብርሃን መመላለስ ስንችል ለአንድ አፍታ በሚሆኑ መንፈሳዊ መገለጥ ብልጭታዎች እንረካለን፡፡.—Testimonies to Ministers, 109-111 MYPAmh 169.2