Go to full page →

የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ MYPAmh 170

የመዳናችን ሁኔታ የሚደገፈው በቃሉ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማወቅ ላይ ነው፡፡ እውነትን ለማግኘት መሻትንና መጠየቅን አታቋርጡ፡፡ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ማወቅ ያስፈልጋችኋል፡፡ ለመዳን ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ለእናንተ ያለላችሁን ነገር እንዲታውቁ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ ነገር ግን እምነትን መለማመድ አለባችሁ፡፡ ቅዱሳት መጽሐፍትን ስትመረምሩ እግዚአብሔር እንዳለና ተግተው ለሚሹትም ዋጋቸውን እንደሚሰጥ ማመን አለባችሁ፡፡ MYPAmh 170.7

መጽሐፍ ቅዱስን ለመንፈሳዊ ምግብ በተራበ ልብ መርምሩ፡፡ ማዕድን ቆፋሪዎች የወርቅን መስመሮች ለማግኘት ወደ መሬት ውስጥ እንደሚቆፍሩ ቃሉን ቆፍሩ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያላችሁን ግንኙነትና እርሱ ስለ እናንተ ያለውን ፈቃድ እስክትረዱ ድረስ መጽሐፍትን መመርመርን አታቋርጡ፡፡ The Youth’s Instructor, July 24,1902. MYPAmh 171.1