Go to full page →

የኤፌሶናውያን ምሳሌ MYPAmh 180

የኤፌሶን ሰዎች በተለወጡ ጊዜ ባህሪያቸውንና ልምምዶቻውንም ለወጡ:: የእግዚአብሔር መንፈስ ባሳመናቸው ጊዜ ፈጣን ምላሽ በመስጠት የጥንቆላ ሚስጢሮቻቸውን በሙሉ አጋለጡ። መጥተው ኃጢአቶቻቸውን ተናዘዙ፣ ተግባራቸውንም አሳዩ፣ ይህን ያህል ለአስማት እራሳቸውን ሰውተው በመስጠታቸውና ሰይጣን የጥንቆላ ስራውን መሠረት ለመሠረተባቸው መጽሐፍት ከፍተኛ ዋጋ በመስጠታቸው ነፍሶቻቸው በቅዱሱ ቁጣ ተሞሉ። ክፉውን ላለማገልገል ከመወሰናቸው የተነሳ እነዚያን ውድ መጽሐፍት አመጡአቸውና በሕዝብ ፊት አቃጠሉአቸው። በዚህ ድርጊታቸው ከእውነተኛ ልባቸው ወደ እግዚአብሔር መመለሳቸውን አረጋገጡ…። MYPAmh 180.1

የኤፌሶን ሰዎች ወንጌልን ተቀብለው ከተለወጡ በኋላ ያቃጠሉአቸው መጽሐፍት አስቀድመው እጀግ የሚደሰቱባቸውና ሕሊናቸውን እንዲገዙና አእምሮአቸውን እንዲመሩ የፈቀዱላቸው ነበሩ ። መጽሐፍቱን ከማቃጠል ይልቅ ሊሸጡኣቸው ይችሉ ነበር፣ ነገር ግን ያን ቢያደርጉ ኖሮ ክፋት ቀጣይነትን ያገኝ ነበር። ከዚያ በኋላ የሰይጣንን ምስጢሮችና የጥንቆላ ስልቶችን ጠሉና ከእነርሱ ያገኙትን እውቀት እንደ ስህተት አዩት:: ዛሬ ከእውነት ጋር ግንኙነት ያላቸውን ወጣቶች የጥንቆላ መጽሐፎቻችሁን አቃጥላችኋልን? MYPAmh 180.2