Go to full page →

መክሊቶችን በተገቢ ሁኔታ መጠቀም MYPAmh 195

መክሊቶቻችንን በተገቢ ሁኔታ የምንጠቀም ከሆነ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለማቋረጥ ወደ በለጠው ብቃት ይመራናል። የተሰጡትን መክሊቶች በትክክል የነገደውን ታማኝ ባሪያ ጌታ እንዲህ ብሎት ነበር:- “አንተ መልካምና ታማኝ ባሪያ፣ በጥቂት ታምነሃልና በብዙ ነገር ላይ እሾመሃለሁ፣ ና ወደ ጌታህ ደስታ ግባ።” አንድ መክሊት የተሰጠው ሰውም የሚችለውን ሁሉ እንዲያደርግ ይጠበቅበት ነበር። የጌታውን መክሊት ነግዶበት ቢሆን ኖሮ ጌታ መክሊቱን ያበዛለት ነበር። MYPAmh 195.1

እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ሰው “እንደ ችሎታው መጠን” ሥራ ሰጥቷል። እግዚአብሔር የችሎታችን ልክ ስላለው ምን ሃላፊነት እንደሚሰጠንም ያውቃል:: ታማኝ ሆኖ ለተገኘው የበለጠ ሃላፊነት ስጡት ተብሎ ነው ትዕዛዝ የተሰጠው። አሁን በተሰጠውም ታማኝ ሆኖ ከተገኘ አሁንም ሌላ ጨምሩለት ተብሎ ትዕዛዝ ይሰጣል። ስለዚህ በክርስቶስ ፀጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ሙሉ ሰው ወደ መሆን ያድጋል። MYPAmh 195.2

ያለህ አንድ መክሊት ብቻ ነውን? ወደ ንግድ አስገባውና ጥበብ በተሞላ ኢንቨስትመንት ወደ ሁለት አሳድግ። እጆችህ ሊሰሩ የሚችሉትን ባለህ ኃይልህ ስራ። የተሰጠህ መክሊት የተመደበለትን ተግባር እንዲያሟላ በጥበብ ተጠቀመው:: በመጨረሻ “መልካም ሠርተሃል” የሚለውን ቃል መስጠት ከማንኛውም ነገር በላይ ነው። ነገር ግን ይህ “መልካም ሰርተሃል” የሚለውን ንግግር የሚባልለት ሰው በርግጥም መልካም የሰራ ሰው ነው። MYPAmh 195.3