Go to full page →

የክርስቲያን ቤተሰብ MYPAmh 210

ልክ እንደጥንቱ አባቶች እግዚአብሔርን እንወዳለን የሚሉ ሁሉ ድንኳናቸውን በተከሉበት ቦታ ሁሉ መሰውያዎቻቸውን መስራት አለባቸው። እያንዳንዱ ቤት የፀሎት ቤት መሆን ያለበት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው። አባቶችና እናቶች ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ትሁት በሆነ ልመና ልቦቻቸውን ወደ እግዚአብሔር ማንሳት አለባቸው:: አባት እንደ ቤተሰብ ካህን በመሆን በእግዚአብሔር መሰውያ ላይ የጧቱንና የምሽቱን መስዋዕት ሲያቀርብ ሚስቶችና ልጆች በፀሎትና በውዳሴ ይተባበሩ። በእንደዚህ ዓይነት ቤተሰብ ውስጥ ኢየሱስ ለማረፍ ይወዳል። MYPAmh 210.1

ከእያንዳንዱ የክርስቲያን ቤት ቅዱስ ብርሃን መብራት አለበት። ፍቅር በተግባር መገለጥ አለበት። በእያንዳንዱ የቤተሰብ ግንኙነት ውስጥ ግንዛቤ በተሞላ ርህራሄ፣ በጭምትነትና ራስ-ወዳድነት በሌለው ትህትና ይህ ብርሃን ራሱን በመግለፅ መፍሰስ አለበት። ይህ መርህ ተፈፃሚ የሚሆንባቸው ቤቶች አሉ። በእነዚህ ቤቶች እግዚአብሔር ይመለክባቸዋል! እውነተኛ ፍቅርም ነግሶባቸዋል። ከእነዚህ ቤቶች የጠዋትና የምሽት ፀሎት እንደ ጣፋጭ እጣን ወደ እግዚአብሔር ይወጣል! የእርሱ ምህረትና በረከቶችም በፀላዮች ላይ እንደ ማለዳ ጤዛ ይወርዳል። MYPAmh 210.2

በደንብ ሥርዓት ያለው ክርስቲያን ቤተሰብ የክርስትና ሃይማኖት እርግጠኛነትን ለመደገፍ ጠንካራ መከራከሪያ፣ ያውም ከሀዲዎች ሊቋቋሙት የማይችሉት መከራከሪያ ነው። የልጆቹን ሕይወት መለወጥ የቻለ ተፅእኖ በቤተሰብ ውስጥ እየሰራ መሆኑንና የአብርሃም አምላክ ከእነርሱ ጋር መሆኑን ሁሉም ማየት ይችላሉ። Patriarchs and prophets, P.144. MYPAmh 210.3