Go to full page →

ለወላጆች መታዘዝ MYPAmh 216

ልጆች ልባቸውን ለእግዚአብሔር እንዲሰጡ ለማድረግ ወላጆች ለልጆቻቸው ሊሰጡ የሚችሉትን ጥቅምና ትምህርት ለመስጠት ለእነርሱ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ልጆቹ በብርሃን ለመሄድ እምቢ ሊሉና በራሳቸው ክፉ መንገድ በመሄድ በሚወስዱአቸውና ለደህንነታቸው በሚጉ ወላጆቻቸው ላይ የማይመች ጥላ ሊጥሉ ይችላሉ፡፡ MYPAmh 216.3

ልጆች የኃጢአትንና ያለመታዘዝን መንገድ እንዲከተሉ የሚፈትናቸው ሰይጣን ነው፡፡ ከተፈቀደለት እነርሱ ከነኃጢአታቸው እያሉ ከድነት ተስፋ ሊለያቸውና እግዚአብሔርን የሚፈሩ አባቶችንና እናቶችን ልብ በሰይፍ በመውጋት በልጆቻቸው የመጨረሻ አለመታዘዝና በእግዚአብሔር ላይ ማማጽ በሐዘን አንገታቸውን እንዲደፉ ለማድረግ ልጆቹን ሊገድላቸው ይፈልጋል፡፡ ልጆችና ወጣቶች፣ ስለ ክርስቶስ በማለት በብርሃን እንድትመላለሱ እለምናችኋለሁ፡፡ ፈቃዳችሁን ለእግዚአብሔር ፈቃድ አስረክቡ፡፡ MYPAmh 216.4

«ኃጢአተኞች ሲያጠምዱአችሁ አትቀበሉአቸው፡፡» ሕግን በመተላለፍ ሰላም ማግኘት ስለማትችሉ የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቁ፡፡ ክፉ መንገድን ስትከተሉ ወላጆቻችሁን ዋጋ ታሳጣላችሁ፣ የክርስቶስን ኃይማኖትም ታዋርዳላችሁ፡፡ በተሰበሰቡ ዓላማት ፊት ሊከፈት ሕይወታችሁ በሰማይ መጽሐፍት እንደተመዘገበ አስታውሱ፡፡ ለእናንተ የዘላለምን ሕይወት ማጣት ምን ዓይነት ውርደትና ሰቆቃ እንደሚሆን አስቡ፡፡ «ወደ ተግሣጼ ተመለሱ፣ እነሆ መንፈሴን በለያችሁ አፈሳለሁ፣ ቃሉንም አሳውቃችኋለሁ…፡፡ የዚያኔ ይጠሩኛል…፡፡ የሚሰማኝ ማንም ቢኖር በሰላም ይኖራል፣ ክፉንም አይፈራም፡፡” «ጨለማ ሳይመጣባችሁ ብርሃን እያለላችሁ ሂዱ፡፡» የሚለውን የክርስቶስን መመሪያ አድምጡ፡፡ The youth’s Instructor, August 10, 1893. MYPAmh 216.5