Go to full page →

ቀለል ያለ አለባበስ MYPAmh 230

“ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናፀፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ።” MYPAmh 230.1

1ኛ ጴጥ የሰው ሐሳብ ሁል ጊዜ ቀላልና ቀጥተኛ የሆነውን የእግዚአብሔር ቃል መመሪያዎች ወደ ጎን ለመተው ይፈልጋል። በየዘመኑ አብዛኞቹ የክርስቶስ ተከታይ ነን ባዮች ራስን መካድንና ዝቅ ማድረግን እንዲሁም በአነጋገር፣ በባሕርይና በአለባበስ ጨዋነትንና ራስን ዝቅ ማድረግን የሚያዙትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ችላ ብለዋል። ውጤቱም ሁል ጊዜም ተመሳሳይ ነበር! ያውም ከወንጌል አስተምሮዎች መለየት የዓለምን ፋሽን፣ ወግና መርህ ወደ መቀበል ይመራል። አስፈላጊ የሆነ አምልኮ ሙት ለሆነ የወግ አምልኮ ቦታ ይለቃል። ከእነዚያ ዓለም ወዳድ ከሆኑት አካባቢ የእግዚአብሔር መገኘትና ኃይል ይነሣና የተቀደሰው የእግዚአብሔር ቃል የሚያስተምረውን ትምህርት ለመታዘዝ ፈቃደኛ ከሆኑት ትሁታን ጋር ይገኛል። ተከታታይ ትውልዶች ይህንን መንገድ ሄደውበታል። ተራ በተራ የተለያዩ የኃይማኖት ድርጅቶች በመነሣት የነበራቸውን ትህትና በመተው መጀመሪያ የነበራቸውን ኃይል በከፍተኛ ደረጃ አጥተዋል። MYPAmh 230.2